አሟሟታቸው “ሆድ ይፍጀው” የተባለው የኦቦ ዓለማየሁ ቀብር ቅዳሜ ይፈጸማል፤ አስቴርና ሙክታር አስከሬኑን ለማምጣት ባንኮክ ናቸው

(ዘ-ሐበሻ) በባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ያረፉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ዓለማየሁ አቶምሳ የቀብር ስነ ሥርዓት የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ እንደሚፈጸም ታወቀ። አስከሬናቸውን ከባንኮክ ለማምጣትም ወ/ሮ አስቴር ማሞና አቶ ሙክታር ከድር ባንኮክ የገቡ ሲሆን ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በ45 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኦቦ ዓለማየሁ የክልሉን ፕሬዚዳንትነት ከተቀበሉ በኋላ መርዝ እንደተሰጣቸውና ለበርካታ የአልጋ ቁራኛ እንዲሆኑ አድርጓቸው፤ በህክምና ላይ የሰነበቱ ሲሆን አሟሟታቸውም ሆድ ይፍጀው ሆኗል ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ የቀብር ስነ ሥርዓት የፊታችን ቅዳሜ በቅድስት ስላሴ ቤ/ክ እንደሚፈጸም የታወቀ ሲሆን አስከሬናቸውን ለማምጣትም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ኦቦ ሙክታር ከድር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቀው ወ/ሮ አስቴር ማሞ ባንኮክ ተጉዘዋል። እነዚህ ሁለት ባልስልጣናትም አስከሬኑን ይዘው ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከባለስልጣኑ ጋር የቀረበ ግንኙነት ነበረን ያሉ ሁለት አስተያየት ሰጪ ጋዜጠኞች በፌስቡክ ገጻቸው ከፕሬዚዳንቱ አሟማት ጀርባ ምስጢር አለ እያሉ ነው። የሁለቱንም አስተያየት ያንብቡት፦

በቅድሚያ የጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ አስተያየት

” የ3 ልጆች አባት የነበሩትን አቶ አለማየሁ አቶምሳን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እንደተሾሙ ሰሞን ለዘገባ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርጌላቸው ነበር – አዳማ ላይ፡፡ ሰውየው በሙስናና ሙሰኞች ላይ የመረረ አቋማቸውን ሲነግሩኝ ‹‹ቆራጥነት›› ባዘለ ቃና ነበር፡፡
ይህንን በተግባርም አሳይተዋል ብዬ አምናለሁ፡፡
ግን ብዙ ሳይቆዩ መታመማቸው ተሰማ፤ የህመማቸው ምክንያቱ ደግሞ የሌባ ጠላት መሆናቸው ነው ተባለ፡፡ ‹‹ድሮስ አሰለጥ ሌባ መች ለጠላቱ ይተኛል›› … በሚል ነገሩ ወዲህና ወዲያ ተነዛ፡፡ ተጨባጭና ሁነኛ መልስ ግን ያገኘ አላጋጠመኝም፡፡
እንደ ጥላሁንን ገሰሰ ሆድ ይፍጀው ሁላችንም የህመማቸው ምክንያቱን ብንጠብቅም ‹‹በየጊዜው ደም እየቀየሩ ነው ከህመማቸው የሚያገግሙት›› ከሚል ወሬ በቀር ሀቁን ይሄ ነው ያለ የለም፡፡ ከእሳቸው አንደበትም የተሰማ ነገር የለም – እስከማውቀው ድረስ፡፡
ይህ በእንጥልጥል እንዳለ ሰሞኑን ስልጣናቸውን በህመም መልቀቃቸውን ሰምተን ብዙ ሳንቆይ ዛሬ ደግሞ ‹‹ከዚህ ዓለም መለየታቸውን›› አደመጥን፡፡ አቶ ሙክታር ከድርና ወ/ሮ አስቴር ማሞ እየታከሙ ከነበረበት ‹‹ባንኮክ›› ከቤተሰባቸው ጋር ‹‹አስከሬናቸውን›› ሊያመጡ እዚያው መገኘታቸውም ተነግሯል፡፡
ያሳዝናል፡፡ በዚህ ዕድሜ መሞታቸው ብቻ ሳይሆን የአገርን ሙስና ‹‹አፈር ድሜ›› ለማብላት ቁርጠኛነትን ‹‹ለሌሎቹ ሳያሳዩልን›› ሞት ስለቀደማቸው ያሳዝናል፡፡
ከአቶ አለማየሁ አቶምሳ ያጣነው አለ – የሌባ አዳኝ መሆንን!
!”

ተጨማሪ ያንብቡ:  ታዋቂው የአረና አመራር አብርሃ ደስታ በወያኔ ታጣቂዎች እየተደበደበ ወዳልታወቀ እስር ቤት መወሰዱ ተሰማ

የሰንደቅ ጋዜጣ አዘጋጅ ፍሬው አበበ በበኩሉ እንዲህ ብሏል፦

“የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት የአቶ አለማየሁ አቶምሳ ዜና ዕረፍት ስሰማ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ አቶ አለማየሁን በአካል የማውቃቸው በ2002 ዓ.ም ወሩን በማላስታውሰው ጊዜ ለስራ የቢሮአቸውን ደጃፍ በረገጥኩበት ወቅት ነበር፡፤ ያኔ አቶ አለማየሁ የማስታወቂያ ቢሮ ኃላፊ ነበሩ፡፡ ለቀጠሮ በቢሮአቸው ድንገት ስገኝ ምናልባት ቢያናግሩኝ በሚል ቀቢጸ ተስፋ በመሰነቅ ነበር፡፡ በአጋጣሚ አቶ አለማየሁ በቢሮአቸው ውስጥ ነበሩና እንድገባ ፈቅደውልኝ በጨዋ ደንብ ከመቀመጫቸው ተነስተው በአክብሮት ያደረጉልኝ አቀባበል ምናለ ሌሎቹም ሹማምንት ከሳቸው ቢማሩ የሚያሰኝ ዓይነት ነበር፡፡ ተግባቢ ሰው በመሆናቸው ከሄድኩበት ርዕሰ ጉዳይ ውጪ ስለግሉ ፕሬስ ላይ ላዩን ለመነጋገር ችለናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አቶ አለማየሁ የግሉ ፕሬስ መኖርና መጠናከር ለስርኣቱ ግንባታ ወሳኝ ነው ብለው የሚያምኑ ቀና ሰው መሆናቸውን ለመረዳት ችያለሁ፡፡ በወቅቱ ፍጹም ጤነኛ እና የተረጋጉ፣ ትልቅ የመሪነት ካሪዝማ ያላቸው ሰው እንደሆኑ በአጋጣሚ መታዘብ ችዬ ነበር፡፡
እናም የክልሉ ፕሬዚደንትና የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው ከተሾሙ ጥቂት ወራት ግዜ በኃላ ከባድ ሕመም ላይ መውደቃቸው በእርግጥም ከጀርባቸው የተሸረበባቸው ተንኮል (ሴራ) ስለመኖሩ በብርቱ እንድንጠረጥር በር የሚከፍት ነው፡፡ ነፍስ ይማር!!”

እውነት እየቆየ መውጣቱ አይቀርም፤ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎችስ ምን ትላላችሁ?

6 Comments

  1. This is quite clear! He has become victim of OPDO’s cadre mafia circle! So regreatable! This mafia group is a great menance for the country. U know his first step while taking office was, he denied the 2000 government constructed appartments that the shameless OPDO cadres had been waiting for. The cadres were living in a government house, were constructing their own houses, but still claim another one. The Arsi mafia cliche of OPDO cadres are behind his intoxication and apparent death. May the wrath of God be upon them for generations.

    • You are not far from the truth. By chance I am from Arsi and I was also in Arsi the day he was elected. I witnessed how they felt when they here the news. It wasn’t about region but more of about religion. Some may try to cover it but i am telling the truth because that was what local cadres were talking. I have a brilliant cousin who finally become opdo because he couldn’t be able to get any promotion however hard he works. Now he is a county or so Astedadary. My cousin who was counties finance employ at the time was about to enter the meeting of opdo he saw other cadres walking away, pissed off. When he ask them, they said ” why do we need to attend for? They took away ‘siltan’from us again. Now you will be promoted too.” Although they are all the same to me, some time it is good to defferenciate between a hayna, and fox. The fox get full fast.RIP

  2. Alemayehu got what he deserved. Such an idealistic and determined man stood on the wrong side of the politics. If he was set for change and cleaning the corruption, he should have parted from OPDO or EPRDF for that matter. How can you work for them and clean them? Impossible. If he was such a charismatic leader, he should have joined the opposition and then by now he could have been a renowed opposition figure.

  3. I am sorry for this victim of Muktar and TPLF conspiresy. Yesterday I saw PM Hailemariyam and his shele wife of Bergude in Aligarh Muslim University, India, in1999.

  4. As it was the case with Dr. Asrat , artist Eyasu Brehe and many others TPLF feeds you poison when you become a threat to their existence. Sadly, the OPDO Chief is a victim of TPLF’s elimination policy. He was an independent thinker and not corrupt to share from their table.

  5. ለካ ኦሮሞም ወንድሙን ይገድላል። ምኒሊክ ብቻ ይመስሉኝ ነበረ ጡት ይቆርጣሉ የሚባሉት። ኦሮሞ የኦሮሞን ነፍስ በመርዝ ሲቆርጥ እጅ ከፍንጅ ያዝነው። 23 አመት ሙሉ የጠገበው ጅቡ ኦህዴድ እንዲህ ካደረገ የተራበው ኦነግ ደግሞ ስልጣን ቢያገኝ ሳያላምጥ እንደሚውጥ ታየኝ (የአርሲው ጅብ ከወለጋው ነብር፣ የወለጋው ነብር ከባሌው አርጃኖ፣ የባሌው አርጃኖ ከኢሊባቦሩ አዞ፣ የኢሊባቦሩ አዞ ከሸዋው ዘንዶ፣ የሸዋው ዘንዶ ከሐረርጌው ተኩላ ሲባሉ ታየኝ)። ከህወሓት የዋለች ጊደር ሙስና ተምራ ትወጣለች አይደል ተረቱ።

    ጋሽ አለማየሁ ፣ እርስዎስ በሰላም ወደሚያርፉበት ላይመለሱ ሄደዋል። ፀፀትም የለብዎት። ይብላኝ እንጂ ለደደብና ሰው አራጅ ለሆኑ የቀድሞ ጓደኞችዎ! ኢትዮጵያ ውስጥ የፈጠረዎት አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው። ደግ ባይበረክትም ስምዎ በርክቷል። በብዙ እንክርዳድ መሐከል የበቀሉ ስንዴ ነበሩ። ዘርዎን ያብዛልን። አሜን።

Comments are closed.

Share