October 16, 2013
3 mins read

በአዲስ አበባ የዳቦ እጥረት ተከሰተ

በአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ በበቂ ሁኔታ እየቀረበ እንዳልሆነ ተገለፀ፡፡ የከተማው ነዋሪዎች በየዳቦ ቤቱ ዳቦ ለመግዛት ሲሄዱ ዳቦ አለመኖሩ እየተነገራቸው በተደጋጋሚ እየተመለሱ መሆኑንና ችግሩም እስካሁን እንዳልተቀረፈ ሰንደቅ ጋዜጣ በጥቅምት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. እትሙ ዘግቧል፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ አንዳንድ ዳቦ መሸጫ ሱቅ የሥራ ኃላፊዎችና ባለቤቶች በተገኘው መረጃ መሰረት በዳቦ መሸጫ መንግሥት ከተመነው ዋጋ አንፃር ሲታይ
አንድን ዳቦ ለገበያ በማቅረብ የሚገኘው የትርፍ መጠን አነስተኛ በመሆኑ ዘርፉ አበረታች አለመሆኑ ተገልፁዓል፡፡
እጥረቱን በተመለከተ ጋዜጣው ያነጋገራቸው በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ሰይድ፤ የዳቦ ዋጋ ትርፍን በተመለከተ መንግስት ተመኑን ሲያስቀምጥ ያሉትን ወጪዎች ታሳቢ
አድርጎ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተፈጠረውንም የዳቦ እጥረት በተመለከተ ስንዴ በእህል ንግድ በኩል ተገዝቶሀገር ውስጥ ሲገባ መንገድ ላይ በተፈጠረው መዘግየት የተፈጠረ መሆኑን ኃላፊው አመለክተዋል፡፡ ያም ሆኖ እህል ንግድ ከመጠባበቂያ ክምችቱ በማውጣት ለአዲስ አበባም ሆነ ለክልል የዱቄት ፋብሪካዎች እንደተቀመጠላቸው ኮታ እንዲያከፋፍል መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሚል በ 2003 ዓ.ም. በበርካታ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ከጣለ በኋላ በስተመጨረሻ የሌሎች ተመን ሲነሳ የስኳር፣ የዘይትና የስንዴ ምርቶችን የማከፋፈል ስራ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሎ እስከ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ይሁን እስካሁን በስርጭቱ ረገድ በስኳር ላይ ተደጋጋሚ ችግር እየታየ ሲሆን አሁን ደግሞ በዳቦ ስንዴ ላይ ችግሩ እየተንፀባረቀ መሆኑን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

Go toTop