December 24, 2016
19 mins read

ለኦርቶዶክስ ስኖዶስ

ቀን፡ 08/04/09 ዓ.ም

አሜሪካ

ጉዳዩ፦ ሀሳብን ስለማጋራት ይሆናል፡፡

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዶ አምላክ ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት እናንተ ወንድሞቸቼና እህቶቼ እያደረጋችሁ ያላችሁት ከፍተኛ ትግል ቅድስት ቤተክርስትያንን ከሌሎች ዘመን አመጣሽ ሃይማኖቶች ወረራ ለመጠበቅ በታላቁ እግዚአብሔር ከፍተኛ ዋጋ ያሰጣችኋል፡፡ እኔም ወንድማችሁ ክርስቲያን እንደመሆኔ መጠን ይህንን ትግል ለመቀላቀል ያስችለኝ ዘንድ ጥቂት ሃሳቦቼን ከናንተ ጋራ ለመጋራት ስል ከታች በዘረዘርኩት መሠረት ለመጥቀስ እሞክራለሁ፦

  1. የቤተክርስቲያን በዓላት ዝግጅቶች ላይ አልኮል( ጠጅ፣ አረቄ፣ ቢራና ውስኪ) ፈፅሞ እንዶይኖር በተለያዩ መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች ማስደረግ ቢቻል……………ብዙዎች አልኮልን ከዚህ ይለምዳሉ
  2. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሰሜኑ ህዝብ ሀይማኖት ነው ተብሎ የመታመን ነገር ስላለ ከሌሎች ክልሎች ካሉ ምዕመናን ዲያቆናትን፣ ቄሶችንና ሰባኪያን በመመልመል ማብቃት ቢቻል
  3. የምዕመናን ክትትል ኮሚቴ በማቋቋም የምዕመናን የዕምነት ሁኔታ ክትትል በማድረግ በዕምነቱ ለሰነፈና አላስፈላጊ ሱሶች ዉስጥ ለገባ ምዕመን አስፈላጊዉን እርዳታ ማድረግ ቢቻል
  4. የቤተክርስቲያን አባቶች መደበኛ የምዕመናን የቤት ለቤት ፀበል የመርጨትና የምክር አገልጎሎት የመስጠት ፕሮግራም እንዲያከናውኑ ማስቻል፡፡ ምዕመናኑ ለቤተክርስቲያን አባቶች የታከሲ ወጪ እንዲከፍሉ ማመቻቸት
  5. Orthodox School: የምዕመናን ልጆች ከህፃንነታቸው ጀምሮ ተመዝግበው የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲከታተሉ ማስቻል፡፡ በዕውቀት የዳበረ ትውልድ በመፍጠር ወደፊት ለሚከሰቱ የሃይማኖት ወረራዎች ከወዲሁ ለመዘጋጀት እንዲያስችል ማድረግ
  6. የክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር የሚያንስባቸው አከባቢዎች ለዩ ትኩረት በመስጠት በየቋንቋቸው ማስተማርና መፅሐፍ ቅዱስን በመተርጎም በሰፊው ማዳረስ ቢቻል፡፡ ደቡብና አንዳንድ የኦሮሚ ያአከባቢዎች
  7. ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ አባላትን በመለየት በልዩ መልኩ ማስተማር ቢቻል የፋብሪካሰራትኞች፣ ዲያስፖራዎች፣ ተማሪዎች፣ ምሁራንና ህፃናት ልዩ ትኩረት ቢያገኙ
  8. የዘመኑ ማህበራዊ ጉዳዮችን ከመፅሐፍ ቅዱስ አኳያ በሰፊው ማብራራት ቢቻል፡፡ ሱሰኝነት፣ ፍቺ፣ ከጋብቻ በፊት ወሲብ፣ አግባብ ያልሆነ ወሲብ ሥርዓት፣ ሀሜት፣ዉሸት፣ ሙስና፣ የአለባበስ ሁኔታ፣ ፊልሞች፣ ሙዚቃ፣ የመገናኛ ብዙሀንና የምሽት ከለቦች ቢዳሰሱ
  9. ለዘብተኛ ምዕመናን ከወጣቱና ከተማ ነዋሪ ከሆነው ክፍል እየተበራከተ ስለሆነ ልዩ ትኩረት ቢሰጠው፡፡ ለዘብተኞች ከእውቀት ማነስና ከግድ የለሽነት የተነሳ ሀይማኖት ወደ መቀየር፣ ሱሰኝነት፣ ለአጥፊ ዘመን አመጣሽ ድርጊቶች አና ለተበላሸ የግል ህይወት የተጋለጡ በመሆናቸው ትኩረት ቢሰጣቸው
  10. ንቁ ምዕመናን ለዘብተኞችን ማበረታታት እንዲችሉ ማስደረግ፡፡ ለምን አትፆምም? ለምን አታስቀድስም? ለምን አታነግስም? ለምን መዝሙርና ስብከት አታዳምጥም? ለምን ቤተክርስቲያን አብረን አንሄድም? የሚሉ ግሰፃዎች ጠቃሚ ስለሆኑ ቢደረጉ ይጠቅማሉ
  11. የቤተክርስቲያን አስራት ማጠራቀሚያ ሣጥኖች በተለያዩ ሆቴሎችና ቦታዎች የሚገኙት በሐጥያት ከሚሰበሰብ ገንዘብ የተገኘ ስለሆነ ከቅድስት ቤ/ን መተዳደርያ ደንብ አንፃር ተገቢ ባለመሆኑ ህብረቱ ከየትኛውም ቦታ የሚሰበሰቡ አስራቶች ዝሙት፣ ሥካርና ወንጀል መሠረት ባላደረገ መሰረት መሆኑን እስካልተረጋገጠ ድረስ ገቢ እንዳይሆን ማድረግና ሣጥኖችን ከነዚህ ቦታ ማንሳት
  12. ጠጣ አትስከር ከሚለው ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ጋር በተያያዘ ክርስቲያን አልኮል ጠጣ ወይም አልኮል መጠጣት አለብህ/አለብሽ ተብሎ ልክ አንደ ትዕዛዝ የተላለፈ በሚመስል መልኩ ምዕመናኑ ኦርቶዶክሳዊ መገለጫ በማድረግ እየተጠቀሙ ይገኛል፡፡ አንድ ክርስቲያን ፈፅሞ መጠጣት አልፈልግም ማለት ይችላል ወይም ከጠጣ መጥኖ መጠጣት አለበት፡፡ እህልነት ያላቸው መጠጦችና ሆን ተብለው የሰው ልጅን አዕምሮ በስካር በመቆጣጠር ላልተፈለገ ሐጥያት የሚዳርጉ በፋብሪካ የተሰሩ መጠጦች ላይ ውይይት ቢደረግ
  13. ጠንካራ የምዕመናን ማህበራትን ከሚሰሩት ሥራና አኗኗር አኳያ እውቅና በመስጠት ማቋቋም፡፡ የመንግስት ሠራተኞች ተዋህዶ ማህበር፣ የተማሪዎች ተዋህዶ ማህበር፣ የፋብሪካ ሠራተኞች ተዋህዶ ማህበር፣ የዲያስፖራዎች ተዋህዶ ማህበር፣ የደላላዎች ተዋህዶ ማህበር፣ የሾፌሮች ተዋህዶ ማህበር፣ የእስፖርተኞች ተዋህዶ ማህበር፣ የነጋዴዎች ተዋህዶ ማህበር፣ የአርቲስቶች ተዋህዶ ማህበር፣ የግል ድርጅት ሠራተኞች ተዋህዶ ማህበር
  14. የዘመኑ ትውልድ አለማዊ ትምህርት ላይ ብቻ በማተኮሩ የተነሳ ወደፊት የዲያቆናት፣ ቄሶች እና ሰባኪያን ቁጥር ማሻቀብ ስለሚገጥም ከወዲሁ መፍትሄ ቢመቻች፡፡ ደምወዝ ጭማሪ ማድረግና ሌላ ስራ እየሰሩ በትርፍ ሰዓታቸው ቤ/ንን የሚያገለግሉ ምዕመናንን መፍጠር
  15. የመረጃ ማዕከል ጽ/ቤት በማቋቋም የተጠናከረ የምዕመናን ምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት (Orthodox Statistics)……ሥም፣ ዕድሜ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ሥራ፣ የዕምነት ሁኔታ (ንቁ/ለዘብተኛ)፣ አድራሻ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የልጆች ቁጥር፣ ክርስትና የተቀበሉበት ጊዜ፣ የማህበራት ተሳትፎ፣ የሱስ ሁኔታ……..
  16. Orthodox ID: ለምዕመናን እንዲዘጋጅ በማድረግ የምዕመናን የተዋህዶ መለያ መታወቂያ ካርድ ማዘጋጀት……ምዕመናኑ በ10 ብር መታወቂያ ካርዱን እንዲገዙ ማስደረግ
  17. Orthodox Financing: ከብሄራዊ ባንክ ጋር በመነጋገር ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ማስጀመር….ገንዘብን ከስራ አንጂ ገንዘብን ከገንዘብ በወለድ መልክ ማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ ስለሚከለከል
  18. International Orthodox Alliance (IOA) በማቋቋም ከተመሳሳይ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያናት ጋር ጥንቃቄ የተሞላበት በልዩነት የአጋርነት ድርጅት በመፍጠር የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ባለው አንጋፋነት ለሌሎች ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ድጋፍ በማድረግ ተቀራርቦ መስረት…..አዲስ አበባን የአሊያንሱ መቀመጫ ማድረግ
  19. International Preachers፡ ብዙ ቋንቋ የሚናገሩና ጠንካራ እውቀትና ፀጋ ያላቸው ዓለም አቀፍ ሰባኪዎችን በመፍጠር በአለማቀፍ ደረጃ የሀይማኖት ማስፋፊያ ስራ መስራት…..የስበከት አገልግሎት በአብዛኛው ኢትዮጲያዊያን ላይ መሰረት ያደረገ ስለሆነ
  20. አንዳንድ የቤተክርስቲያን አባቶች| ቄሶችና ዲያቆናት የኑሮ ውድነትበማሳበብና አለማዊ ዲሎትን በማሰብ በንግድና በተለያዩ ተጨማሪ ስራዎች ላይ ተሠማርው ስለሚገኙ ለኑሮ በቂ የደምወዝ ጭማሪ ማድረግና ጥብቅ የሆነ የስነ ምግባር ደንብ (Ethical Code for Servicemen) በማውጣት ለዚህና ለሌሎች እንደ ስካርና ዝሙት ላሉ የባህሪ መሰል ግድፈቶች ማስተራረሚያ ማድረግ
  21. እድሳትና ጥገና የሚያስፈልጋቸው ቤተ-ክርስቲያናትና ገዳማት በተለይ በሀገራችን ሩቅ አካባቢዎች የሚገኙ እርዳትና ጥገና ሳያገኙ በችግር ውስጥ ስላሉ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ተለይተው በአፋጣኝ እድሳት ቢደረግ
  22. በምዕመናን የክትትል ኮሚቴ አማካኝነት አንዳንድ ምዕመናን በአጥፊና አሰናካይ የስራ ዘርፎች ለምሳሌ የምሽት ክበብ | አደንዣዥ ዕፅ| ዝሙት| ሰው ማዘዋወርና ለመሳሰሉት ተሠማርተው ስለሚገኙ ኮሚቴው አነዚህን ምዕመናን በማማከር ሌላ ተቀያሪ ሥራ እንዲሠሩ ወይም ሌላ መፍትሔ ተፈልጎ ምዕመናኑ ኦርቶዶክሳዊ ባህሪያት እንዲላበሱ ማስደረግ
  23. የኦርቶዶክስ ተራድዖ ድርጅት(Orthodox Charity Org.) በማቋቋም በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች ችግርተኛ ለሆኑ የገንዘብና ነፃ የማህበራዊ አገልግሎት ዕርዳታ እንዲያገኙ በማስቻል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት የመልካም ተምሳሌትነትን ማጠናከር … በዚህ ተራድዖ ድርጅት ስር አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ በገንዘብ ሀብታም የሆኑ ምዕመናን ችግርተኛችን በምግብ| በገንዘብ| በህክምና ወጪ| በአልባሳትና በሌሎች አገልግሎቶች እንዲረዱ ማስቻል
  24. የኦርቶዶክስ አስተዳደር ጽ/ቤት| ማህበረ ቅዱሳን| ሐገረ ስብከትና የመሳሰሉት በተዋህዶ ስር የሚገኙ ጽ/ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በቋሚ ቅጥር ሠራተኞች እንዲሠሩ ቢደረግ የተሻለ ነው ምክንያቱም አሁን አየሠሩ ያሉት በአብዛኛው በመንግስት ወይም በግል ሥራ ላይ ተሠማርተው ስለሚገኙ በብዛት የጊዜ መጣበብ ስለሚገጥማቸው
  25. Orthodox Research Foundation: የኦርቶዶክስ ምርምር ማዕከል በማቋቋም የክርስትና አስተምሮትን በተጠናከረ መልኩ ማስተማር…..በየጊዜው የሚከሰቱ ማህበራዊ ችግሮችን በማጥናት መንፈሳዊ መፍትሄ አንዲፈጠር ማስደረግ
  26. በአብዛኛው የጋብቻ ስነ ሥርዓች በቤተ-ክርስቲያን አባቶች ቅደሳ አስጀማሪነት ተጀምሮ ወደ አለማዊ ገፅታ እየተቀየረ ስለሆነ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጠንካራ አቋም በመያዝ ምዕመናኑ መንፈሳዊና አለማዊ ጋብቻን ለይቶ እንዲያከብር ማስደረግ ቢቻል……….ሀይማኖት የባህልን ተፅዕኖ ተቋቁሞ በከፍታ ደረጃ ላይ መቀመጥ ስላለበት
  27. ሥርዓተ ለቅሶ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ተከትሎ ባህላዊ ደንብ በምዕመናን ስለያዘ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጠንካራ አቋም በመውሰድ ከምዕመናን ጋር በሰፊው የምክክር ጉባኤ በማድረግ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ብቻ ተከትሎ እንዲተገበር ቢደረግ…አንድ ምዕምን በአምላክ ተፈጥሮ በአምላክ ስለሚወሰድ የምዕመናን ከመጠን ያለፈ የሐዘን ስርዓት አምላክን ማማረርና መፈታተን ስለሆነ
  28. የቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ደንቦችን በማውጣት ምዕመናን በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የተለየና የተስተካከለ ምግባር እንዲከተሉ ማስድረግ…..ሙሉ ገላን የሚሸፍንና የሰውነት አካላትን በግላጭ የማያሳይ አለባበስ፣ የመዋቢያ ማቴሪያሎችን ማሰወገድ፣ ከጎን ካለ መዕምን ጋር አለማውራትና አለማማት፣ በረጅም ነጠላ መከናነብ፣ መንፈሳዊ ፕሮግራሙን ሳይጨርሱ ማቋረጥ፣ በፆታ የተከለሉ ቦታዎችን መከተል፣ ፆታዊ ትንኮሳ አለማድረግ፣ አልኮል አለማስገባት፣ የራስ ፀጉርን አለማንጨባረር ንፅህናን መጠበቅ
  29. የቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ንፅህና የሚያስጠብቅ መንፈሳዊ ኮሚቴ በማቋቋም ምዕመናንን ፕሮግራም ወጥቶላቸው ተራ በተራ እንዲያፀዱ በማድረግ ምዕመናን ከአምላከቸው በረከት እንዲያገኙ ማስቻል…በእኔ ስም ማንም ንፁህ ውሃ እነኳን ቢያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም ጌታ አምላካችን ስለሚል
  30. በመልዓክትና በፃድቃን ስያሜ የተለያዩ አንዳንድ የንግድ ደርጅቶች ተሰይመው የሚገኙ አለማዊ የስያሜ ለውጥ እንዲያደርጉ ማድረግ…የቤ/ን አልባሳት መሸጫና መዝሙር ቤቶች ሲቀሩ የፃድቃን ስያሜ መሰጠት ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ተግባር ስለሆነ
  31. ምዕመናን ኦርቶዶክሳዊ አኗኗር ዘይቤ እንዲከተሉ ማስቻል…አለመቃም፣ አለማጬስ፣ አለመጠጣት/አለመስከር፣ አለመዘመት፣ አለመስረቅ፣ አለማማት፣ አለመግደል፣ አለመዋሸት፣ አለመሳደብ፣ ባለእንጀራን ማክበርና እንደራስ መውደድ፣ ቤተሰብን ማክበር…….ከመደበኛው ህዝብ የተለየና የተስተካከለ ባህርያት መላበስ አለባቸው…………ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ባህርያት ሊወገዱ ይገባል፡፡
  32. የስብከት አገልግሎት ከሌሎች አገልግሎቶች አብላጫ ትኩረት ቢሰጠው…….መንፈሳዊ ዕውቀት ክፍተት ሀይማኖት ለመቀየርና ለለዘብተኝነት ዋነኛ መንስዔ ስለሆነ
  33. የሀይማኖት ተቋማት አስተዳደር ብልሹነት ለምዕመናን ሽሽት ሲለሚዳርግ ብልሹ አሰራር ማስወገጃ መደበኛ መንፈሳዊ ውይይት ስርዓት ቢፈጠር
  34. ሌሎች ሀያማኖቶች በዓለማዊው ክንፍ ዝነኛ የሆኑ ግለሰቦችን እየተጠቀሙ የምዕመናን ዝርፊያ እያካሄዱ ስለሆነ የስብከት አገልግሎታችን ዓለማዊ ዝናን ማውገዝ ላይ ቢያቶክር……ሀይማኖት አለማዊ ነገሮችን ድል ማድረግ ስላለበት
  35. የደናግል ጋብቻን በማበረታታት ከፍተኛ ዕውቅና በሁሉም የስብከትና መንፈሳዊ አገልግሎቶች መስጠት…..የኢ-ደናግል ጋብቻ ለትዳር ፍቺ ዋነኛ መንስዔ በመሆኑ

“ከእግዚአብሔር ሠላምታ ጋር”

ከወንድማችሁ በላይ አበራ

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop