August 25, 2013
7 mins read

በርካታ ቻይናውያን ሞባይል ስልኮችን በሕገወጥ መንገድ አስገብተው ሲሸጡ እየተያዙ ነው

(ሪፖርተር) ከግንባታ ሥራቸው እኩል በተለያዩ የማጭበርበርና የሙስና ወንጀሎች ስማቸው የሚነሳው ቻይናውያን፣ አሁን ደግሞ በኤርፖርቶች በኩል ቀረጥ ሳይከፍሉባቸው የሚያስገቧቸውን ልዩ ልዩ የቻይና ስሪት ሞባይል ስልኮችን ሲሸጡ በአደባባይ እየተያዙ በመታሰር ላይ መሆናቸው ተሰማ፡፡
ከአዲስ አበባ እስከ ክልል ከተሞች መንሰራፋቱ የሚነገርለት የቻይናውያኑ ሕገወጥ ድርጊት ከውጭ የሚገባበት መንገድ ብቻ ሳይሆን የሚሸጥበት ስልትም አስገራሚ እየሆነ መጥቷል፡፡ በአውሮፕላን ተጓጉዘው በየሻንጣው የሚገቡ የሞባይል ስልኮች የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ኪስ እያራቆቱ መሆኑን ለቻይናውያኑ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ባልደረቦችም ሞባይል ስልኮቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት በአውሮፕላን ተጓጉዘው በመሆኑ፣ የኤርፖርቶች ሠራተኞችን በተባባሪነት እንደሚጠረጥሩ ተናግረዋል፡፡ በእንዲህ ያለው ሁኔታ የሚገቡትን የሞባይል ስልኮች ስትሸጥ እጅ ከፍንጅ የተያዘች ቻይናዊትን ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባደልረቦች ያስረከበው የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ፣ በወቅቱ ከቻይናዊቷ ከተያዙት ጥቂት ሞባይል ስልኮች ባሻገር፣ በከተማው ውስጥ የተደበቁና አመቺ ጊዜ የሚጠብቁ በርካታ ቀጥር ያለው የኮንትሮባንድ ሞባይል ስልኮች እንደሚኖሩ ጥርጣሬ አለው፡፡
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ስለድርጊቱ ማብራርያ ተጠይቆ ማብራሪያ ለማግኘት ባይቻልም፣ ቁጥራቸው 30 የሚገመት ቻይናውያን ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ታስረው እንደነበርና አብዛኞቹም የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ታውቋል፡፡ በርካቶችም ከሜክሲኮ በታች በቀድሞው ላጋር ጉምሩክ ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አንዳንዶቹም በገንዘብ ዋስትናና በገደብ ሲለቀቀሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የሚቀርቡ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቻይናውያን ለሙስና እንዲጋለጡ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች ውስጥ ቋንቋ ባለማወቃቸው ሳቢያ በአስተርጓሚዎች በሚካሄድባቸው ጫና እንደሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ ከዚህ ቀደም እዚህ ቆይታ የነበራቸው ቻይናውያንና አንዳንድ ሐበሾች እንግሊዝኛ ቋንቋ የማያውቁ ኢንቨስተሮች ሲመጡ፣ በእጅም በእግርም ካላሉ በስተቀር በአብዛኛው የመንግሥት መሥርያ ቤቶች ዘንድ ጉዳያቸው ሊፈጸምላቸው እንደማይችል ስለሚነግሯቸው ይህንኑ ለማድረግ እንደሚገደዱ ይገልጻሉ፡፡ ሆኖም የሞባይል ስልክ አጭበርብረው ከሚያስገቡት ቻይናውያን ግን እነዚህ የተለዩ ናቸው፡፡
የተጭበረበሩ የሞባይል ስልክ ቸርቻሪዎቹ ቻይናውያን ያስገቡዋቸው የሞባይል ስልኮች ከሚሸጡባቸው ዘዴዎች ውስጥ ደግሞ በአለባበሳቸው ደህና ሆነው ያገኟቸውን ኢትዮጵያውያን መንገደኞች በመቅረብ፣ ለአገሩ እንግዳ በመሆናው ንብረቶቻቸው ድንገት የጠፉባቸው መሆኑን ይነግራሉ፡፡ በእጃቸው የቀረውን ‹‹ውድ ዋጋ ያለው የሞባይል ስልክ›› ለመሸጥ መገደዳቸው አስተዛዝነው በመግለጽ ያግባባሉ፡፡ ልቡ የተነካና የኋላውን ያልጠረጠረ መንገደኛም በዋጋ መደራደር ይጀምራል፡፡ ስምንት ሺሕ ብርና ከዚያም ላቅ የሚል ገንዘብ ሊጠራለት ይችላል፡፡ ሆኖም መክፈል የሚችለው ሁለት ወይም ሦስት ሺሕ ብር ብቻ እንደሆነ የሚገልጸው የአገሬው አዛኝ፣ በያዘው ገንዘብ እንዲገዛ ያግባቡትና ሽያጩ ይጠናቀቃል፡፡ የተሸጠለት የሞባይል ስልክ ግን ግፋ ቢል ከ500 ብር ላይበልጥ እንደሚችል ምንጮች ይናገራሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጎዳና ላይ ነጋዴዎች ሕጋዊ የገበያውን ሒደት እያወኩ በማስቸገራቸው ዕርምጃ ሊወስድባቸው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በቁጥጥር ሥር ማዋል መጀመሩን በሚታይባት አዲስ አበባ፣ ቻይናውያን ከውጭ በሕገወጥ መንገድ ያስገቡዋቸውን ልዩ ልዩ የሞባይል ስልኮች ሲሸጡ በአደባባይ መታየታቸው አስገራሚ እንደሆነባቸው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ
እኛ የዘ-ሃበሻ ጋዜጣ አዘጋጆች ደግሞ ከአራት አመት በፊት አብዱ ኪያር ስለ ቻይናዎች በበሰለ ቅኔ ያዜመውን
ቻይና ቻይና የሚለውን ዘፈን እንድታደምጡት እየጋበዝን በቸር ያሰንብተን እንላችኋለን::

2 Comments

  1. Abdu kiar my best artist.
    He knew that the Chinese are coming to our land to do the modern colonization.
    Bravo abdu kiar i like the kine (the wax and gold).

  2. Abdu kiar is very good in his Amharic language. I didn’t even expect this kind of lyrics from a young generation. He touch my heart. God bless you Abdu kiar.

Comments are closed.

Previous Story

የሌላውን ትግል ለማዳፈን መሯሯጥ ለውድቀት!

Next Story

ሕወሐት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop