July 22, 2023
13 mins read

የአማራው የወቅቱ አማራጫ የለሽ አቋም (እውነቱ ቢሆን)

የአማራው ህዝብ ትግል የህልውና ነው፡፤ የመኖር ወይንም ያለመኖር፡፡ በአሁኑ ሰአት አማራው በታሪኩ አይቶትና አጋጥሞት በማያውቀው አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቋል፡፡ የአማራው እልቂትና የኢትዮጵያ ውድቀት እየተመራ ያለውም ጨካኝም ፈሪም በሆነው አብይ አህመድና የኦሮሙማ መንጋ በሚመራው  የዘረኝነትና የተረኝነት አገዛዝ ነው፡፡ ይህ የታሪክ አተላ የሆነ ሰው ኢትዮጵያን ይዞ ወደ ገደል እየገባ ባለበት በዚህ ወቅት አማራው ቀዳሚ ጠፊ እንዲሆን ተፈርዶበታል፡  የእልቂት ድግሱ የተቀመረው በተረኞቹ ኦሮሙማወችና  በባንዳወቹ ወያኔወች ጸረ አማራ ጥምረት ሲሆን አፈጻጸሙ በሆዳሙ ብአደን አማካይነት ነው፡፡ ጥምረታቸውም መሰረት ያደረገው አማራን በጋራ ካዳከሙ ከቻሉም ካጠፉት በኋላ ወያኔ ወልቃይትንና ራያን ወደ ትግራይ በመጠቅለል ታላቋ ትግራይን ሲመስርት ኦሮሙማም በቀረችው ኢትዮጵያ መቃብር ላይ ታላቋን ኦሮሚያ በኦሮሙማ አምሳል ቀርጾ ኢትዮጵያ በሚል ስም (ታላቋ ኦሮሚያ በምል ስምም ሊሆን ይችላል) ቀሪውን ኢትዮጵያ ጠቅልሎ መግዛት ነው፡፡

እጅግ ዘግይቶ ምለትም ብዙ ሚሊዮኖች አማራወች ከታረዱ፣ ከተሰደዱና ከተፈናቀሉ በኋላ ቢሆንም ዛሬ በህይወት ያለው አማራ ይህንኑ የወያኔና የኦሮሙማ ጸረ አማራ ጥምረት ነቄ ብሎታል፡፡ ጥምረታቸው ብዙም ተራምዶ አማራውን ከማመናመኑ በፊት በአጭር ወራቶች ውስጥ የአማራው ተጋድሎ ተደራጅቶ፣ ጥርስ አውጥቶና ጎልብቶ ወደ ትግሉ ሜዳ ገብቷል፡፡

በአሁኑ ሰአት አማራው በአማራነቱ በቁጭት በህዝብ ደረጃ ከጫፍ እሰከጫፍ እየተናበበና እየተደራጀ ነው፡፡ በአማራ ላይ የተሰሩት ግፎችና የተፈጸሙት ሰቅጣጭ ግዲያወች በውጭም በውስጥም ባለው አማራ ህሊና ውስጥ ለደቂቃወችም ሳያቋርጥ እያቃጨሉ ነው፡፡ ስለሆነም አማራው ወስኗል፡፡ መደምደሚያው ያደረገውም አስቀድሞ የክልሉን አመራርና አስተዳደር ከብአደን የአብይ አህመድ አሽከሮችና ከወራሪው የኦሮሙማ ጦር ነጻ ማድረግ ነው፡፤ ተጋድሎውንም ሳያቋርጥ በአገር ደረጃ በሚዘረጋ ኢትዮጵያን ከጅቦች መንጋጋ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያላቅቅ ከሌሎች በኦሮሙማ እየተዋጡ ካሉ ወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በተጠናና በተቀናጀ የትግል ስልት ኦሮሙማንና ወያኔን ከአገሪቱ ውስጥ ጠራርጎ በማስወገድ አርቆ መቅበር ነው፡፡ ለዚህ የማይታጠፍ የአማራ ህዝብ የተጋድሎ ዉሳኔ ተግባራዊነት 46 ሚሊዮኑ አማራ በበኩሉ ቆርጦ ተነስቷል፡፡

የአማራው የህልዉና ትግል ሊቀለበስበማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡  አብይም ሆነ የክልሉ ጅላንፎወች አሁን እየሞከሩ እንዳሉት በቄስ፣ በቃልቻ፣በሽማግሌ፣ በድርድር፣ወዘተ ተማጽኖወች ትግሉ ነጻነትን ሳያረጋግጥ አይቆምም፣ አይቀለበስም፣፡

የአማራውን የህልዉና ተጋድሎ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የኦሮሙማን ድብቅ አላማ ተሸክመው ለመሸምገልና ጊዜ ለመግዛት ለሚጥሩ ማንም ይሁኑ ማን ሀይሎች አማራው መልሱ መሆን ያለበት <<የህልዉናየ መረጋገጥ ወይንም ሞቴ>> ብቻ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ትግሉ አብይ አህመድ በሚልካቸው የተለያዩ ሀይማኖቶች መሪወች፣ ታውቂ ሰዎች፣ ሽማግሌወች ወዘተ ወጥመድ ውስጥ በመግባት መልሶ ጭቃ ውስጥ ሊነከር የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡  አማራውን ለዚህ የማይቀለበስ የትግል ቃልኪዳን ያበቃው 32 አመታት በላይ ከክልሉ በውጡ በራሱ ልጆች ከሀዲነት፣ በወያኔና በኦሮሙማ የደረሱበት ቁጥር፣ ስፍር ፣ ልክና መጠን የሌላቸው መራር ግፎች፣መከራወችና ምንጊዜም ከህሊና የማይረሱ እልቂቶች ናቸው፡፡

በዚህ የትግል ጉዞው ውስጥ አንመከርም፣ ወደህዝቡ ትግል አንቀላቀልም ያሉ የብአዴን የየወረዳም ሆነ የየዞንና ክልል የፖሊስ አመርሮችና አባላቱ ላይ፣ የደህንነት አመራርና አባላቱ  ላይ፣ የመስተዳድር ሀላፊወችና የየመስሪያ ቤቶች አመራሮች ላይ፣ በድምሩ ከመንደሮችና ከተሞች እስከ ክልል ድረስ በተዘረጋው የገዳዩ የብልግጽና አመራሮች ላይ የማያዳግም፣ መራርና አስተማሪ የሆኑ እርምጃወችን እያጣሩ በፍጥነት መውሰድና ለሌሎች ሆዳሞች አስተማሪ እንዲሆኑ እያደረጉ መሄዱ ምትክ የለሽ የወቅቱ የትግል ስትራቴጅ ነው፡፡

ላለንበት ወቅት ይህ አይነቱ ወሳኝ የትግል ስትራቴጅ የተጠና የተሻለና ተመራጭም ነው፡፤ የነጻነት ጉዞው ኤላ አማራጭም የለውም፡፡ የዚህ አይነቱ የተቀነባበረ እርምጃ በየእለቱና በየግንባሩ እየተጠናከረ መሄድ አለበት፡፤ ለደቂቃም ቢሆን መቆም የለበትም፡፡

በአሁኑ ለአማራው የሞት ወይንም የሽረት በሆነበት አንገጋቢ ወቅት አማራው ከምንም ነገር በላይ ክልሉን ከኦሮሙማና ከወያኔ ወረራና አገዛዝ በተጋድሎው ነጻ ከማድረግ ውጭ ቅድሚያ የሚሰጠው ሌላ አጀንዳ ፈጽሞ ሊኖረው አይችልም፡፡

ዲያስፖራው በዚህ ታሪካዊ ወቅት ሊያደርጋቸው የሚችሉና እያደረጋቸውም ያሉ የትግሉ አጋዥ እንቅስቃሴወች አሉ፡  ከነዚህም ውስጥ አንዱ  ተአማኒና ለትግሉ በሚደርስ መንገድ የሚመራ የገንዘብ መዋጮ ነው፡፡ ዲያስፖራው ይህ አይነቱን እገዛ እስከነጻነት ድረስ ቋሚ በማድረገ ትግሉን መደገፍ አማራ የመሆኑ ግዴታው ነው፡፡ በልዩ ልዩ ህቡእና ግልጽ  እንቅስቃሴወች (እዚህ የማይገለጹ) ውስጥም ተሳትፎ ማድረግ በዲፕሎማሲና በመረጃ ስርጭት፤ በምክርና በቅስቀሳ   ብዙ ስራወች የተጀመሩ ሲሆን ተጠናክረውና ወጥና ዘላቂነት ባለው አደረጃጀት  መቀጠል አለባቸው፡፡

ስለሆነም ለዚህ ላይታጠፍ ለተጀመረው የትግል ጉዟችን በውጭ ያለው የአማራ ዲያስፖራ በገንዘብ እርዳታ በሎጅስቲክስና በድፕሎማሲው መስክም የውጭውን አለም በማስረዳትና  ቅስቀሳ በማድረግ  በኩል የበኩሉን ማድረግ ይቀጥል፡፡

በአገር ውስጥ ያለው አማራ በሙሉ በአንድ ወጥ አሰላለፍ ብአደንን፣ ኦሮሙማንና ወያኔን ለመደምሰስ በተሰለፈው ፋኖ የአማራ ህዝባዊ ሀይልና አመራሩ ጎን በጽናትና በቁርጠኝነት መቆም አለበት፤ ፋኖን መንከባከብ፣ ለፋኖ ከለላ መስጠት፣ የፋኖ ጥሪወችንና ተልእኮወችን ተቀብሎ መፈጸም፣  ፋኖን  አለኝታው አድርጎ መውሰድና በተጋድሎው ሂደትም አብሮ መሰለፍ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡

አብይ አህመድ ከሁነቶችና ከሚታዩ ከሚዳሰሱ መሬት ላይ ካሉ እውነታወች የሚማር ሰው አይደለም፡፡ ስብእናው በእብሪት፣ በጥላቻና በክፋት የተሞላ ፈሪና ጨካኝ (ፍራትና ጭካኔ ጀግንነትና ሩህሩነት ይወራረሳሉ) ሰው ነው፡፡ ግለሰቡ የሚሰለጥንም የሚታመንም ፍጡር አይደለም፡፡ መቀደድ፣ መዋሸት መበጥረቅ መለያወቹና ማንነቶቹ  ናቸው፡፡ ይህ ሰው አሁን ላይ የአማራን አይቀለበሴ ተጋድሎ ለማጨናገፍ አውጥቶ አውርዶ ከመንጋውና ከተጣማሪው ወያኔ ጋር መክሮ የደረሰበት አንድ ጉዳይ አለ፡፤ ይህም የአማራን የተጋድሎ ግስጋሴ ሊያስቆመው ስላልቻለ የማጨናገፍ  ሙከራ ማድረግ ነው፡፡

ውድ አማራ ወገኖቼ ሆይ፦ በዚህ የሚታለል የትግሉ አማራር ይኖራል ብዬ ሳይሆን በበኩሌ ይህንን አብይ የዘረጋውን የማታለያና የማዘናጊያ ወጥመድ ልደግምላችሁ ወደድኩ፡፡

አብይ አህመድ ለማዘናጊያ የዘረጋውን የሽማግሌ፣ የቄስ፣ ቃልቻ ምናምን  እርቅ፣ ሽምግልናና የመሳሰሉ የመደለያም ጊዜ የመግዣም ወጥመዶች ጭራሹን አለማዳመጥና አለመቀበል ብቻ ሳይሆን በማስጠንቀቂያ አሳፍሮ መመለሰ ትግሉ ያለበት ሁነታ ግድ ይላል፡፡

የብአደን ተላላኪወችን አስቀድሞ በማስጠንቀቂያ አደብ ማስገዛት ካላቆሙም በያሉበት እርምጃ በመውሰድ ሌሎችን ማስተማሪያ ማድረጉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በዚሁ መንፈስ ትግሉን እስከነጻነት ማድረስ አማራው ለህልውናው መቀጠል ወይንም አለመቀጠል ምር

የብአደን ተላላኪወችን አስቀድሞ በማስጠንቀቂያ አደብ ማስገዛት ካላቆሙም በያሉበት እርምጃ በመውሰድ ሌሎችን ማስተማሪያ ማድረጉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ በዚሁ መንፈስ ትግሉን እስከነጻነት ማድረስ አማራው ለህልውናው መቀጠል ወይንም አለመቀጠል ምርጫየለሽ አቋም ነው፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop