አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ሰሞኑን አብይ አህመድ በሀሰት ፈጠራና ስያሜ ‘የአማራ ሸኔ’ በሚል ስም የተናገረው የህዝብ ፍጅትን ለማካሄድ የሚያስችል ቅድመ ሁኔታን የሚፈጥር፣ የጥፋት ስነ ልቦናን የሚያዘጋጅ ጸረ አማራ ንግግር አደገኛ በመሆኑ አጥብቀን እናወግዛለን።
ላለፉት አራት አመታት የአገራችን ኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና ከእለት እለት እይተሸረሸረ፣ በርካታ የአማራ ህዘብ በገዛ አገሩ እንዳይኖር ጭካኔ ለተሞላበ የዘር ጥቃትና እልቂት መዳረጉ እይተባብሰና እይከፋ መምጣቱ መራራ እውነታ ነው። በመንግስት የጦር ሃይልና በኦንግ/ሸኔ ሽፋን በዘመናዊ መሳሪያ በታጠቁ ሀይሎች ያልታጠቀውን ሰላማዊ ህዝብን ሴቶችና ልጆችን መግደልና ማፈናቀሉም እንደቀጠለ ነው። በአብይ አህመድ ግልጽና ስውር መሪነት በሙሉ ሀይል የአማራ ህዝብን ለመፍጀትና ለማስፈጀት የዘር ጥላቻና ጦርነትን በማፋፋም ላይ እንደሚገኝ የዘውትር ተግባሩና ንግግሩ ይገልጻል፤ ዛሬም በወለጋ ሆነ በሌሎች አካባቢ አማራን ለማስጠቃት የስነ ልቦናዊና የቃላት ቅስቀሳና ዝግጅት በማደረግ ላይ ይገኛል። ይህን እኩይ ተግባር ለማስፈጸሚያ ከሚጠቀምባቸው ዘዴውች መካካል አንዱ የሃሰት ማንነንትን ሊያጠቁት ለሚፈለጉትን ህበርተሰብን በመጥፎና ባልሆነ ነገር በመሰየምና በመፈረጅ ሲሆን ሰሞኑን አብይ ‘የአማራ ሸኔ’ የሚለው ቅጥያን መጠቀሙ የዚህ መገለጫ ብቻ ሳየሆን ከኦሮሞ ሸኔ ጋር ለማመሳሰል መሞከሩ መጪው አስከፊ ተግባሩን የሚያመላክት ሲሆን አማራውን ሆነ ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚሄድበት የጥላቻ እርቀት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል።
የወያኔ/ኦነግ መሰርታዊ አላማና ግብ ለማሳካት ብልጽግና ፓርቲ፣ (የኦነግ የዳቦ ስም) የሚመራው አብይ አህመድ በስልጣን ለመቆየት ማንኝውንም አረመናዊ ተግባር ሁሉ እንድሚያድርግ በተደጋጋሚ አሳይቶል፣አስመስክሮል። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በአጠቃላይ ሆነ በኢትዮጵያዊነቱ አልበገር ባለው በአማራ ህዝብ ላይ በየእለቱ የሚፈጸመው ግፍና አረመናዊ ተግባር የዘመናችን ሂትለር የኦንጉ አብይ አህመድ መንግስት እውቅና እና ትእዛዝ መሆኑን በትክክል መገንዘብ ይኖርብናል። ይህንን ተጨባጭ እውንታ በደንብ መገንዘብ ለምንሰጠው መፍትሄ ወሳኝ ሃይል ይሆናል።
የአብይ መንግስትና መሰሎች ለኢትዮጵያውያን ሆነ ለአማራው ህዝብ ደህንነት ጠባቂ ሳይሆኑ አጥፊ ሃይል መሆናቸው መዘንጋት የለበትም፣ እንደ መንግስት ህግ ያስጠብቃል ብሎ መጠብቅና ተስፋ ማድረግ እንደሚባልው ሁሉ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዲፈለፈል መጠበቅ ማለት ነው። የወያኔን አመራር በኦነጋዊ የጎሳ አስተሳሰብ መተካት ለኢትዮጵያ ህዝብ እውነትኛ ለወጥ አለመሆኑ በተግባር በተደጋጋሚ ተረጋግጧል፤ እንዳወም ከእሳት ወደ ረመጥ ሆኖል እንጂ። አብዘህኛውን ህዝብ ለዚህ ሰቆቃ የዳረገው ዋናው የችግሩ ምንጭ ወያኔ/ኦነግ/ብልጽገና የሚመሩበት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ፖሊቲካዊ አስተሰስብና የሀሰት የጎሳ ትርክት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ የጎሳ ክልል ስርአት ወገንን ከወገን የሚለያይ፣ አገርን የሚከፋፍል የርስ በርስ ጦርነት የሚጋብዝ፣ ህዝብን ለእልቂት፣ ለድህነት፣ ለመፈናቀልና ለባርነት የሚዳርግ ሁላ ቀር ስለሆነ ባስቸኳይ መወገድ አለበት። የጎሳ መለያ ሰባዊነትን ሰለሚያጠፋና ጭካኔን ስለሚያጠናክር እንዲሁም የጎሳ አራዊትነትን ስለሚፈጥር፣ ( በኦነግ ሸኔ እንደሚታየው) ይህን የጥፋት መንገድ ማስወገድና መከላከል የዘመናችን ወቅቱ የሚጠይቀው ስልጡን ሃላፊነት ስለሆነ፣ ተግባራዊ እናደርገው ዘንድ የትብብር ጥሪ እናደርጋለን።
አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት፣ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ አገራችንና ሀዝባችንን ከዚህ አስከፊ የጥፋት መንገድ ለማዳን፣ የኦነግ/ሸኔ አላማ አስፍፈጻሚ የሆነውን አብይ አህመድን ከስልጣን አስወገዶ ኢትዮጵያዊና ህዝባዊ የሆነ የሽግግር መንግስት መመሰርት ወሳኝና አስፈላጊ አገር ወደድ ኢትዮጵያውያን በመላ ሊወስዱት የሚገባ ዘላቂ መፍትሄ ነው እንላለን። ይህ ተግባራዊ እንዲሆን በአብይ መንግስትና በተባብሪዎቹ ላይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሳዊ ማእቀብና ልዩ ልዩ የስራ አድማዎችን በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በማደርግ፣ የሚያደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ማንኛውንም የሰላማዊ ትግል ዘዴውችን በመጠቀም ለህዝባዊ አመጽ ተነሳሽነትን ማጠናክር ወቅቱ የሚጠይቀው አስቸኮይ ተግባር ስለሆነ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ቆራጥ ተሳትፎ እናደረግ ዘንድ የአንድነትና የትብብር ጥሪ እናቀርባለን። በተለይም በተቀነባበረ ሃይል ለብዙ አመታት የጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች የጥቃት ኢላማ የሆነው የአማራ ህዝብ ህልውናውና ደህንነቱን ማስጥበቅና አደጋን መከላክል ተፈጥሮዊ ህግና ግዲታው ስለሆነ ራሱን ክጥፋት ለመታደግ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ነቅቶና ዝግጁ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል።
ስለዚህም የአለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ህዝብን ከጥፋት፣ ከእልቂትና ከእርስ በርስ ጦርነት ለማዳን በወቅቱ አሰፈላጊውን ሁሉ እንዳረግ ዘንድ ወገናዊ ጥሪ ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በተለይም ለመከራው ገፈት ቀማሽ ለኢትዮጵያውያን ሴቶች ይህን ልዩ የትብብር ጥሪ እናቀርባለን።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ጀግንነት ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች!!
አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት
ታህሳስ፣ 2014።