December 3, 2022
12 mins read

አማራ ሆይ! በአውሬ የተጎረሰ ልጅ ራሱን ሳያተርፍ እናቱን ሲያድን የት አገር አይተሃል? – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ ([email protected])

 

በልጅነቴ አንድ ቆፍጣና ጎበዝ ሊበላው በቃጣ የቀን ጅብ የፈጠመውን ጀግንነት አይቻለሁ፡፡ ይህ የቀን ጅብ የሰነፍ አህያ ፍለጋ ሰፈሩን ሲያዳርስ አድሮ ነጋበትና ሲረፋፍድ ጎረምሶችና ውሾች ሲከተሉት እያነከሰ መሮጥ ጀመረ፡፡ አንድ ኪሎ ሜትር ያህል እንደተጓዘም በተቃራኒ አቅጣጫ ለጉዳዩ ከሚጓዝ ጎበዝ ፊት ለፊት ተፋጠጠ፡፡ ይህ ጅብ በፍርሃት ርዶ ማምለጫ እንደሌለው ሲረዳ በዚህ ጎበዝ እመር ብሎ ተኮፈሰ፡፡ ጅቡ የተኮፈሰበት ቆፍጣና ጎበዝ ፎከረና ጋቢውን በፍጥነት አውልቆ ለጅቡ አጎረሰው፡፡ ጅቡ ሰውየውን አገኘሁ ብሎ ከጋቢው ሲታገል ያ ጎበዝ በጅንፋም ሽመል አናቱን ፈጥፍጦ ከምድር አነጠፈው፡፡

Amhara cryይህን ጎበዝ ያፈራ አማራ ዛሬ እንደ ጅብ የእንሰሳ መልክ ሳይሆን የሰው መልክ ካላቸው አውሬዎች ተፋጦ ይገኛል፡፡ “ሰውን በአምሳላችን እንስራ” እሚለው የኦሪት ቃል የሃይማኖቱና የባህሉ አስኳል በመሆኑ አማራ ሰው መሳይ አውሬዎችን ከሰው ለመለየት የተቸገረ ይመስላል፡፡ አማራ ሰውን እግዚአብሔር በአምሳሉ ፈጠረው ብሎ ስለሚያምን በቅየው የመጣውን ሰው ሁሉ በየእግዚአብሔር እንግዳነት ያይና ቤት-ለእምቦሳ ብሎ ተቀብሎ እርሱ መሬት እየተኛ አልጋውን ወይም መደቡን ለእንግዳው ይለቃል፡፡ አቶ ደበላ ዲንሳ “ጎጃም ስትነግድ ለስንቅ መጨነቅ የለብህም” እንዳሉትም እንኳን በችግር የተሰደደውን ለትርፍ የመጣውንም እየደገሰ ምርጥ ምርጡን ለእንግዳ ይመግባል፡፡

ይህ መለኮታዊ ባህል ግን አማራን ለአደጋ አጋልጦታል፡፡ በእንግድነት እንጀራውን እየበላ ለሚሰልለው የልዋጭ ነጋዴ አጋልጦ ዛሬ እርሱ አምራች ሰላዩ የልዋጭ ነጋዴ በይ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይባስ ብሎም ዛሬ በገጠር በከተማው እንደነ ቅዱስ ጴጥሮስንና ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን እንዲቀነጠስ፤ እንደ ሰንጋ እንዲሰለብ፣ እንደ መሲና እንዲመክንና እንደ ፍሪዳም እንዲታረድ አድርጎታል፡፡

አማራ ሆይ! ይህቺ ከንቱ ምድር ለበጎዎች ተመችታ አታውቅም፡፡ ይህቺ ምድር እንደ ፈሪሳውያን ላሉ ቀጣፊዎች፣ እንደ ይሁዳ ላሉ ከሃዲዎች፣ እንደ በርባን ላሉ ቀማኛዎችና እንደ ጲላጦስ ላሉ አፈ ጮሌዎች ናት፡፡ በእነዚህ ዓይነት ከሀዲዎች፣ ቀማኛዎችና አፈ ጮሌዎች ቅዱስ እስጢፋኖስ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ እንደሞተ፣ ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስም አንገቶቻቸውን እንደ አገዳ እንደተቀሉ ላንተ አልነግርህም፡፡ ይህቺ ዓለም እንኳን ለሌላው የሰው ሥጋ ለብሶ ለመጣው መለኮት ለክርስቶስም አልሆነችም፡፡ ክርስቶስና ሐዋርያቱን የሰዋቸውን የከሀዲዎች፣ የቀማኛዎችና የጮሌዎች ትንኮና ጭካኔ በወፍ አሞራው በጠላትነት የተፈረጅከው አንተ አማራው በምን የትዕግስት ጫንቃ እንደቻልከው አላውቅም፡፡

አማራ ሆይ! በጠላትነት ፈርጀው የሚያሳድዱህ ወፍ አሞራዎች ከአውሬዎችም እጅግ የከፉ ጭራቆች ናቸው፡፡ ከአውሬዎች እጅግ የከፉ ጭራቆች ስለሆኑም ጅብ በጅብ ፣ አሳማ በአሳማ፣ ከርከሮ በከርከሮ ወይም እባብ በእባብ የማይፈጥመውን ግፍ በአንተ ፈጥመዋል፡፡ በአንተ የደረሰው ግፍ ከአርባ ሁለት አመታት በፊት ከወልቃይትና ባዶ ስድስት ይጀምራል፡፡ ከባዶ ስድስት የተረፉት እንደ ተናገሩት በዚያ ሲኦል ምድር የስንቱ አማራ ገላ እንደ ቋንጣ ተተልትሏል?

አማራ ሆይ! የተረሳ ይደገማልና ባለቤታቸው በደኖ ገደል ተወርውሮና አስራ ሶስት ልጆቻቸው ተበትነው ከአምሳ በላይ ታጣቂዎች ደፈረዋቸው ከማህፀናቸው መግል እንደ ጅረት ሲፈሳቸው ያየኋቸውን የአምሳ ዓመት እናት አትርሳ፡፡ በአርባ ጉጉ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በጋንቤላ፣ በአሶሳ፣ በመተከል፣ በራያና እንደዚሁም እንደ ከበት በክልል ታጉረህ እንድትኖር ተጨልፎ በተሰጥህ ጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ወልድያ፣ ማጄቴና ሌሎችም ሥፍራዎች የረገፉትን ወገኖችንህም አትዘንጋ፡፡

አማራ ሆይ! ግፉ በአደባባይ የዋለውን የአበጥርን ሰቆቃና ምስላቸው ሳይቀረፅ ያለፉ ብዙ የባዶ ስድስት፣ የማዕከላዊ፣ የቃሊት፣ የሸዋ ሮቢት፣ የዝዋይ፣ የብር ሸለቆ፣ የዴዴሳና የሌሎችም ያልታወቁ ወህኒቤት አበጥሮችን አትዘንጋ፡፡ በአማራነታቸው ግድግዳ እየገፉ ራቁታቸውን በሴት ታጣቂ የተገረፉትን መነኩሴ አባ ጡመልሳን የነገሩንንም አዳምጥና ያለህበትና ሁኔታ ተረዳው፡፡ (https://ethsat.com/2018/05/esat-menalesh-meti-with-qomos-aba-tumelessan-zemichael-and-artist-senaiet-berhanu/). ዛሬም በመላ አገሪቱ በተለይም በወለጋ የሚደርስብን አላባራ ያለ የዘር ፍጅትና የሕዝብን ሰቆቃ ልብ በለው፡፡  ወደፊት ልትሰማ የምትችለውን አደባባይ ያልወጣ ሰቆቃም ግምት ውስጥ አስገባው፡፡

የገዥዎችህ ራዲዮና ቴሌቪዥን ለፍትህ እታገላለሁ የሚለው የውጩ ድህረ-ገጥ ሳይቀር የተጨናነቀው አውሬ በበላቸው ልጆችህ ሳይሆን በማይፀድቅ ችግኝ ተከላ፣ በማይጠና የነፍሰ ገዳይ ሌቦች እርቅ፣ የደላው በሚጫወተው የእግር ጓዝ ወሬ ነው፡፡ በአንተ ደም ስልጣናቸውን የሚያስጠብቁት ወሮበላ ገዥዎችህም የፈሰሰውን ደምህን ከመጤፍ ሳይቆጥሩ ደምህ የፈሰሰበትን እርስትህን ሊያስነጥቁ እያቆበቆቡ ነው፡፡

አማራ ሆይ! አንተ በሰላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ወታደር እየሆንክ አገር ለመንገባት ስትባትል አውሬዎች አንተን ለመብላት ለክፍለ-ዘመናት ሲያደቡህና ሲደራጁ ኖረዋል፡፡ ይኸንን የአውሬዎች ደባ የተረዱ ታሪካዊ የውጪ ጠላቶችህ እነዚህን አውሬዎች እየረዱ ዛሬም ቻዝ ብለው ለቀውብሃል፡፡  ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ ባህሪህ ካዘልካት ኢትዮጵያ ፈልቅቆ ለአውሬዎች አስረክቦሃል፡፡ አውሬ ጎርሶህ እናትህን ኢትዮጵያን እንዴት ማዳን ይቻልኻል? በአውሬ የተጎረሰ ልጅ ራሱን ሳያተርፍ እናቱን ሲያድን የት አገር አይተሃል?

አማራ ሆይ! ብዙ አውሬዎች ተከፋፍለው ስለዋጡህ ወደ አምስት ሚሊዮን ጎለሃል፡፡ ተራ በተራ ሊውጡህ የተሰልፉትን አውሬዎች ካልተከላከልክ የመጥፋት እድልም ይገጥምሃል፡፡ እንደምታውቀው የደን ጭፍጨፋ ከአንድ ዛፍ ይጀምራል፡፡ የአንተ ጭፍጨፋ ግን በፍጥነት አምስት ሚሊዮን ደርሷል፡፡ ዛሬም እንደበፊቱ አውሬዎችን በትምህትና በፍቅር ወደ ሰውነት እቀይራለሁ በሚለው ቀጥለህ ከሆነ የመጥፊያህን ጊዜ አሳጥረሃል፡፡ ግዜ እየጠበቀና እያደባ የሚበላህ አውሬ የትምህርት ሐተታና የፍቅር ስብከት እንደማይገባው ተሞክሮህ ሊያስገነዝብህ ይገባል፡፡ ትምህርትና ፍቅር ለአውሬ እንደማይገባው ስለ አንድነትና ፍቅር ያስተማርከው ከአለት የተዘራ ስንዴ ሆኖ መቅረቱ በመረጃነት ሊያሳምንህ ይገባል፡፡

አማራ ሆይ! ማንኛውም ፍጥረት ዘሩ እንዳይጠፋ የተቻለውን ያደርጋል፡፡ አጋም ፍሬውን ላለማስነካት በእሾሁ ይዋጋል፡፡ ንብ ማሩን ላለመስጠት በሰንኮፉ ይናደፋል፡፡ አነር ከጠላት ለመከላከል በጥፍሩ ይፏጭራል፡፡ ጎሽ ልጁን ለማዳን በቀንዱ ይዋጋል፡፡ አንተም ዘርህን ለማትረፍ የተቻለህን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብሃል፡፡ ሰውነትህን እየዘነቸረና አጥንትህን እየጎረደመ የሚበላ አውሬ ሲመጣብህ ያን የቀን ጅብ ፎክሮ እንደገጠመው ልጅህ ራስህን ማዳን ይኖርብሃል፡፡ ራስህን አድነህ ዘርህን ከመጥፋት ስታድንና ክንድህን ስታፈረጥም ጉልበተኛን ብቻ የሚያከብረው ይህ ምድር ክብር ይሰጥሃል፡፡ የፈጠረውን ዘር ከመጥፋት ያዳንክለት መለኮትም በተመቻቸ የሰማይ ቤት ያኖርሃል፡፡

 

መጀመርያ ግንቦት ሁለት ሺ አስር ዓ.ም. እንደገና ህዳር ሁለት ሺህ አስራ አምስት ዓ.ም.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop