June 24, 2022
13 mins read

ከአ.ህ.ኢ.ን በአማራ ወገኖቻችን ላይ ተጠናክሮ የቀጠለውን መንግስት መራሹን ሰቅጣጭ የዘር ፍጅት ወንጀል በተመለከተ የተሰጠ የአቁዋም መግለጫ

ethiopia hlwnaሰኔ 17ቀን 2014 (23/06/2022)                                                                             

የአዲስ አበባ ህልውና ለኢትዮጵያ ንቅናቄ መንግስት ነኝ ብሎ እራሱን በሚጠራው በኦነጉ አብይ አህመድ የኦዴፓ የደም በልፃጊ ቡድን በሚደገፈው በኦነግና በወያኔ የሽብር ቡድኖች ወደው ባልተወለዱበት ማንነታቸው እየተመረጡ በቃላትም ሊገለፅ በማይቻልበት እጅግ ሰቅጣጭ በሆነ ሁኔታ በወለጋ በግፍ የዘር ፍጅት ወንጀል በተፈፀመባቸው ከ3000በላይ በሚሆኑ የአማራና በጋምቤላ በ47የጋምቤላ ወገኖቻችን እልቂት የተሰማውን እጅግ መሪር ሀዘን እየገለፀ ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍና ለቤተሰቦቻቸው ፤ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንዲሰጥለት ይመኛል ።

በመቀጠል ለተከበረው  ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በፓርላማ ቆሞ እልቂትን ከሚቀሰቅስው ከወያኔ አሸባሪ ቡድን የበኩር ልጅና እልቂትን ከደገሰልህ ከኦነጉ አብይ አህመድ ምን ተስፋ ሰንቀህ ነው አሁንም እጅና እግርህን አጣጥፈህ የተቀመጥከው የሚል አንድ አንኩዋር ጥያቄ እያቀረበ ከዚህ ቀደምም አህ ኢን በተደጋጋሚ በፋሽስት ወያኔ የሽብር ቡድን እና በኦነጉ ዐብይ አህመድ የደም በልፃጊ ቡድን መካከል ያለው የስልጣን ሽኩቻ እንጅ ሁለቱም በዓላማ አንድ መሆናቸውንና እየተናበቡ ዘወትር የእልቂት ድግስ ደጋሾች መሆናቸውን እየገለፀ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስት በሌለበት ሐገር እራሱ መንግስት ሆኖ እጅ ለእጅ በመያያዝ ለማይቀረው የነፃነት ትግል እንዲነሳ ሲያሳስብ መቆየቱን ለማስታወስ ይወዳል።

የተከበርከው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በማንነትህ እየተመረጥክ በቁምህ የምትቃጠለው፤እንደከብት እየታረድክ ደምህ እንደጎርፍ የሚፈሰውና ከምድረ ገፅ እንድትጠፋ የተፈረደብህ የተከበርከው የአማራው ወገናችን

እነዚህየወያኔና በአብይ አህመድ የሚመራው የኦነግ አሸባሪ ቡድንም ሆነ ሌሎች በየጊዜው የሚነሱ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች “ኢትዮጵያን የማፍረስ እቅዳችን ሊሳካ የሚችለው በቅድሚያ አማራውን ከምድረ ገፅ ስናጠፋ ነው”! በሚል የዘመናት እቅዳቸው እየተሰራበት የመጣና በየጊዜው ከሰውነት ባህሪ በወረዱት በእነዚህ  የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ተልኮ ፈፃሚ ሐገር በቀል አውሬዎች በየጊዜው እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ የዘር ፍጅት ወንጀል በአማራ ወገኖቻችን ላይ ሲፈፀም የቆዬ ሲሆን አሁን ግን ከከፋውም ጊዜ በላይ እጅግ የከፋው ጊዜ ላይ ደርሰን በፓርላማ ቆሞ በይፋ እልቂትን በሚያውጅ አብይ አህመድ በሚባል መንግስት ተብዬ በይፋ የእልቂት ቅስቀሳ እየተደረገ ከምንጊዜውም በላይ እጅግ ዘግናኝ የሆነ እልቂት በወገኖቻችን ላይ መፈፀሙ ብቻ ሳይሆን ወገኖቻችን አልቀዋል የህሊና ፀሎት እናድርግ አዠንዳም ይያዝልን ያሉ ከ የአማራ ወገኖቻችን ተወካዮች በፓርላማ ያቀረቡትን ጥያቄ ባለመቀበል በይፋ ለህሊና ፀሎት እንኩዋን የማይበቁናቸው የሚል ንቀትን በማሳየት ክልከላ ድርገዋል።

*ታዲያ አንተ በማንነትህ እየተሳደድክ፤በገጀራ እንደከብት እየታረድክ፤ሆድህ እየተቀደደ ፅንስህ የሚወጣው፣ተቆራርጠህ ላውሬ የምትጣለውና ለይስሙላ እንኩዋን የህሊና ፀሎት አይገባህም ተብለህ የተከለከልክ የአማራ ወገናችን ሆይ በቃኝ ለማለት፤እንደ ሕዝብ ሆ ብለህ ለህልውናህ ለመነሳት ከእንግዲህ ምን ቀረህ?

**አንተስ አማራው ወገንህን አጥፍተው አንተንም ከነልጅ ልጆችህ በተራህ ጭዳ ሊያረጉህ ያዘጋጁህ የተቀረኸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ከሰውነት ተራ በወረዱ አረመኔ የሽብር ቡድኖች እጅግ ዘግናኝ በሆነ ጭካኔ በግፍ ስለሚጨፈጨፈውና ሆድ እየተቀደደ ፅንሱ ስለሚወጣው አማራው ወገንህ አረመኔዎችን በቃችሁ ለማለት ዛሬ ካልተነሳህ መቼ ልትነሳነው? ፤ የኖረው ኢትዮጵያዊ እሴትህስ ይሄ ነው?  ፤ ወንድምህ ሲጠቃ ዝም ማለት? ፤ የነጩን፣የቀዩንና የጥቁሩን በሬ ተረት አስታውስ፤ዛሬ የአማራ ወገንህ በግፍ ሲጨፈጨፍ ባሳየኸው ዝምታህ በተራህ የተሳለው ሰይፍ በርህን እያንኳኳ መሆኑን ተገንዘብ።

ስለዚህ አ.ህ. ኢ.ን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት፣ፍትህና እኩልነት እንደቆመ እንደ አንድ ንቅናቄ ሐገራችን ኢትዮጵያንም ሆነ የአማራ ወገኖቻችንን እየተፈፀመባቸው ካላው ከፍተኛ የዘር ፍጅት ወንጀል መታደግ የሚቻለው በውስጥም ሆነ በውጭ ያለው መላው ሐገር ወዳዱ ሕዝባችንም ሆነ ንቅናቄያችን የሚከተሉትን የትግል መርሆች ብቻ ከተከተሉ ብቻ በመሆኑ በውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ሕዝባችን በከፍተኛ መናበብ ተግባራዊ ያደርጋቸው ዘንድ በፈጣሪና በግፍ በተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ስም በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

ይኽውም:- 1መላው ሕዝባችን ሐገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑዋ ሰዓት መንግስት አልባ ሐገርና የሽብር ቡድኖች መናኸሪያ እንደሆነች ተገንዝቦ እያንዳንዱ ዜጋ ታጥቆና ተደራጅቶ በኦነጉ አብይ አህመድ ከሚመራው ከኦነጋዊው የኦዴፓና ከፋሽስት ወያኔ የደም በልፃጊ የሽብር ቡድኖች  ሊሰነዘር ከሚችል ከማንኛውም ጥቃት አካባቢውንና እራሱን እንዲከላከልና እንዲታገላቸው፤

2/ የተለያዩ ጠንካራ ሕዝባዊ አመፆችንና የስራ ማቆማ አድማዎችን በመላው ኢትዮጵያ በይፋም በህቡም ማደራጀትና መምራት፤መታገል፤

3/ ህዝባዊ አምጹም ሆነ ትግሉ ገዥው ኃይል ሥልጣኑን እስካላስረከበ ድረስ  በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ፤

4/  በትልልቅ ከተሞች በተለይም እንደ አዲስ አበባ ባሉ ህዝብ በሚበዛባቸው  ሁሉም  ዜጋ የትግሉ አጋርና ታጋይ እንዲሆን  በተደራጀ መንገድ መሥራት።

5/ በተቃዋሚ ስም ከገዥው ኃይል ጋር  ሥልጣን የተጋራችሁና የፓርላማ መቀመጫ ያላችሁ ለቃችሁ እንድትወጡና ህዝባዊ ትግሉን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን። ይህን ባታደርጉ ግን የዘር ማጽዳቱ ተካፋዮችና አጋሮች መሆናችሁን ተገንዝባችሁ ከኦነጋዊ ብልጽግና እና ከወያኔ  ጋር ተጠያቂ መሆናችሁን እንድታውቁት ከወዱሁ  እናስገነዝባለን።

6/ በውጭ  አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያዊኖች በዶላርም ሆነ በኢሮ የምትልኩትን ገንዘብ እንድታቆሙ፣ የገዥው ኃይል ጥቅም የሚያገኝባቸውን ማንኛቸንም ነገሮች ያለመጠቀምና ከገዥው ኃይል ጋር ያለን ግንኙነት ከስልጣን እስኪወገዱ ድረስ ማቋረጥ።

7/ በውጭ አገር የምትገኙ አገር ወዳዶች  በያላችሁበት በመደራጀት የውስጡን ትግል ማገዝና የሚዲያ ሽፋን በመስጠት ከፊስቡክ ባለፈ በተግባር የተደገፈ ትግል ማካሄድ።

8/ በተለይም ባለፋት አራት ዓመታት በአማራ ላይ የተፈጸመው የዘር ፍጅት የመጀመሪያ  ተጥያቂዎች በሥልጣን ላይ ያሉት መንግስት ነን ባዮች መሆናቸውን ተገንዝበን፤ ስልጣናቸውን እስካለቀቁና ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ ትግሉ በማንኘውም መንገድ መቀጠልና ህዝባዊ አመፁን በተለያየ አቅጣጫ ማፋፋም።

9/ ዐብይ መራሹ የኦነጋዊው የኦዴፓ የደም በልፃጊ ገዥ ቡድንም ሆነ የፈለፈለችው የፋሽስት ወያኔ የሽብር ቡድን የጋራ ዓላማ አማራውን አጥፍተን ኢትዮጵያን እናጥፋ በሚል እኩይ ዓላማ ሁላችንንም ሊያጠፉን በጋራ የተነሱ ጠላቶቻችን መሆናቸውን ተገንዝበንና ከሰራነው ከቀደመው ስ ህተት ተምረን በየትኛውም ጊዜና ቦታ በመደራጀትና በተባበረ ትግል ሐገርንና ሕዝብን መታደግ ፤እርስ በርስ መጠባበቅ።

10/  ሐገራችን ኢትዮጵያንም ሆነ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ የእልቂት አዋጅ የታወጀበትን የአማራው ወገናችንን መታደግ የምንችለው ሰውነትን አስቀድመን ከተራ የጎሳ ፓለቲካ ወተን ስንደራጅና ከራሳችን ውጭ ሌላ ነጻ አውጭ እንደሌለን ጠንቅቀን በማወቅና በፅናት በመታገል መሆኑን መገንዘብና ለዚህም ራስን ዝግጁ ማድረግ ናቸው።

******************

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ማሰሪ ውል ናት!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop