March 13, 2014
8 mins read

በለው! ቄንጠኛ ዳንስ በዕንባ ሲደንስ

ሥርጉተ ሥላሴ 13.03.201 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ምን አለባቸው አልሞተባቸው፤ ጥቁር አለበሱ፤ የተራበ ወግን የላቸው፤ የታሰረ ሥጋ የላቸው፤ ባለጊዜ እንዲህ በቄንጥ ዳንሱን ያስነኩት፤ ይጨፍሩ! በጣም አምሮባቸዋል! ተዋጥቶላቸዋልም። ሂዶላቸዋልም። ሚሊዮኖች ጉርሻ ፍላጋ ለትራፊ በረድፍ ተሰልፈው ከጠኔ ጋር ተፋጠዋል። ሚሊዮኖች ከቦታ ቦታ ተራ ዜጋ ናችሁ ተብለው ይፈናቀላሉ። ሺዎች „ኢትዮጵያዊ“ እተባሉ በዬአረብ ሀገሩ እዬተነጠሉ ይታረዳሉ፤ ይደፈራሉ፤ ወንዶችም ይሰለባሉ – ይደፈራሉም፤ በፍል ይቀቀላሉ፤ በፎቅ ይፈጠፈጣሉ። በገጀሞ ይከተከታሉ —- ይታረሳሉ፤ ቄንጠኛው ደግሞ ዳንሱን እንዲህ ያስነኩታል ….

አዎን! በሺህ የሚቀጠሩ ዜጎቻችን ዜግነታቸው የትኛው ሊሆን እንደሚችልም መላ አጥተው ዛሬ ይታመሳሉ። የሱዳን ወይንስ የኢትዮጵያ? የሱዳን መንግሥትና የወያኔ የሽፍታ አስተዳደር የሚስጢሩ ድርድር „ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሆኗል።“ ቀንደኛው ሄሮድስ መለስ አፈር ሊያጫውቱ ቢሄዱሙም ጨፋሪው አቶ ሃይለማርያም ደግሞ በሙት መንፈስ ፈረስ እየጋለቡ ታሪክ ይቅር የማይለው አርበኝነትን፤ ታሪክን ማንነትን የዳጠ፤ የጠቀጠቀ ተግባር ፈጸሙ፤ ይንንም ሐሤት አድርገው የፍንጥሩን የልባቸውን ሞልተው የለ ምን ሲገዳቸው፤ እንዲህ ፍለቅልቅ ብለው ይደልቃሉ። በችርስ ይዘንጣሉ። ሳቅ በእናት ኢትዮጵያ ምድር ከገጠር እስከ ከተማ በፈለሰበት ዘመን ከሳቸው ቤት የበቀል ፈገግታ በገፍ እንዲህ ይመረታል – ወይ ነዶ! አሁን ዳንስስስስስ! ህም!

ሚሊዮኖች አስፓልትን ተጠልለው ነገን በሞት ይጠባበቃሉ። የኑሮ ዋስትና፤ የጤና ዋስትን፤ የመማር ዋስትና የላቸውም። የዕምነት አዛውንቶች ካለ ባህላቸውና ትውፊታቸው ስደትን የሙጡኝ ብለው እንደከሰሉ ያልፋሉ። ሀገርም ያሉት የጸሎት ቤታቸው በስጋት ተወጥሮ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆነው ተሳቀው ይኖራሉ። ዳንሰኛውም ደግሞ ዳንኪራቸውን እንዲህ መሬት አይበቃኝ ብለው መድረኩን ቀውጢ አድርገው ያስነኩታል …. ፍርሰት —

ለእለት ጥም ጠብታ ማርኪያ የሚማስኑ ዕልፎች ናቸው። እንደተቆለፈባቸው ጧሪና ጠያቂ አጥተው ትውልዱን ረግመው የሚሰናበቱንም እጅግ በርካታ ናቸው። ቄንጠኛው ዳንሰኛ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ ሞቅ ብሏቸው፤ ጥጋቡም አላስችል ብሏቸው እንዲህ ይሉታል …. ማላጋጥ … ምልገትም —-

ጠቀራ የለበሱ ቀናት ረሃብን እያወጁ፤ ስጋትን ነጋሪት እዬጎሰሙ፤ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጎጆ እንደ ጉድ ይተማሉ። ቅብጠት ያመራቸውና ያልወጣላቸውም ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ ደግሞ ክርስትናውን ባፍ ጢሙ ብለው ይደልቁታል። ሁሉም አይቅርብኝ በማለት ከተቃራኒ ፆታ ጋርም የዐይን ፍሰቱንም ሆነ የእግር ዳንኪራውም እንዲሁም የመንፈስ ኮማውም …. በአንድነት በመደዴ ያስኬዱታል —- እርግማን!

አሁን ያን የሳውዲ ሰቆቃ ያዬ ፍጡር ዳንስ? ፈንጠዝያ?! ውቂ ደብልቂ?! እፍረት ነው። እውነት ለከፈን፤ ለመጠለያ፤ ለጉሮሮ ያልበቃች በብድር የተነከረች ሀገር እዬመሩ እንዲህ ሃላፊነት የጎደለው የአደባባይ ጥቁር ትዕይንት ማሳዬት እጅግ አንገት ያስደፋል ህሊና ላለው ሰው። „ባልወለድ“ ማለት የነበረበችው እርሳቸው ነበሩ ግን … በዬትኛው ህሊና?

ለነገሩ ምን አለባቸው እሳቸው አልጎደለባቸው። ፈሰስ ብለው ይኖራሉ። እልፎች ድምጻቸው ታፍኖ መተንፈስ ሲጀምሩ እዬተለቀሙ ለእግር ብረት ይዳረጋሉ። ልጆች ካለወላጅ፤ ጎጆም ካለ ጉልቻ፤ ትውልድም በነጠፈ ተስፋ 23ዓመት እንደዋዛ … ወገን ደም እንባ እያለቀሰ ታፍኖ፤ ተከዝኖ የሞት ቀናትን ይጠብቃል። ናፍቆት እስክንድርና መሰሎቹ ህጻናት ደግሞ ወላጆቻቸውን ተነጥቀው በሰው ሀገር ናፍቆታቸውን ሰንቀው ባልበሉት እዳ ይታሻሉ። ክልትምትም ይላሉ። አቶ ሃይለማርያም ደግሞ ከመላ ቤተሰባቸው ጋር የልጆቻቸውን ፍቅር ጠዋት ማታ እዬኮመኮሙ ጥጋቡ አላስችል ብሏቸው እንዲህ በመከራ ላይ፤ በግፍ ላይ ይጨፍራሉ ትዝብት ነው ….

ክውና — እረኛ ያጣ ህዝብ፤ ሙሴ የሌለው ትውልድ፤ ባላቤት የሌላት ኢትዮጵያ በፈላ እንባ እስከ መቼ ይሆን መቀቀሉን የሚቀጥሉት? ፈጠሪ አምላክስ መቼ ነው ፍርዱን አደላድሎ በቃችሁን የሚያውጅው!?! ….. ለግፍኞች፤ በእንባ ጨፋሪዎችስ ላይ ቅጣቱን አከታትሎ መቼ ነው የዶግ አመድ አድርጎ ብን የሚያደርጋቸው …. ? መቼስ „ተስፋ“ አያልቅ ደግሞ እንደ አመላችን „ተስፋ“ የሚባለውን እንጠብቅ ወይንስ ከእሱ ከራሱ „ተስፋ“ ከሚባለው ልብ አንጠልጣይ ጉድ ጋር ጦርነት እንግጠም ይሆን?

በሉ የኔዎቹ በዚህች ቆራጣ መጣጥፍ ትንፋሽ — የውስጤን ቁስለት በማሳዬት ተብተከትኩ። ለነበርን መልካም ጊዜ አመሰገንኩ – በፍቅር። ደህና ሰንብቱ።

እልፍ ነን። እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop