በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ዘመቻ በአስቸኳይ ይቁም!!!

ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ በነጻነት እንዳበራች ዛሬ ላይ እንድትደርስ የአማራው ሕዝብ መስፈሪያ የለሽ ዋጋ መክፈሉ ታሪክ ምስክር ነው:: ሃገራችን ተስፋፊና ወራሪ ሃይሎችን መክታ ሉዐላዊነቷ አስጠብቃ እንድትኖር የመላው ዜጎቿ ተጋድሎ ውጤት ቢሆንም አማራው ግንባር ቀደም በመሆኑ ለውጪና ለውስጥ ጠላቶች ኢላማ እንዲሆን አድርጎታል:: በዚህም ባለፉት 50 አመታት ግልጽ ጥቃት ተከፍቶበት ብዙ መከራን ሊያስተናግድ ተገዶ ቆይቷል::

በተለይ ባለፉት 28 አመታት አማራው በግልጽ ማንነቱን መሰረት  ያደረገ የጥቃት ዘመቻ ተከፍቶበት ዋጋ ሲከፍል ቢቆይም ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ወርዶ በብሄር ላለመደራጀት በትግዕስት ለመቆየት ሞክሯል:: የመከራው መርግ መክበድ የግፍ መበራከትና የስቃዩ ብዛት ሳይወድ በግድ በብሄር ማንነቱ ተሰባስቦ እንዲመክት ተገዷል::

ሕወሃት ኦነግና ግብረአበሮቻቸው አማራውን ገለን ቀብረነዋል :: አከርካሪው ተሰብሮ እንዳይነሳ አርገን ጥለንዋል:: ቢሉም በማንነቱ መሰባሰብ በጀመረ ማግስት ያሳየው መነሳሳት ጠላቶቹን ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ጥሏቸዋል:: የአማራው መነቃቃትና መደራጀት ለአማራው ብቻ ሳይሆን ጥላቻና የግንጠላ አጀንዳ ያላቸውን የጽንፈኛ ሃይሎችን ሕልም አምክኖ ለመላው ኢትዮጵያዉያን ብሄሮች ሕልውና ጭምር ተስፉ በመሆኑ አደረጃጀቱ እንዲመክን አንድነቱ እንዲበተን በግልጽና በስውር ሰፊ ዘመቻ ተከፍቶበት ቆይቷል::

ይህንንም ተቋቁሞ እራሱን ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል የሚያደርገውን ዝግጅት ለመቀልበስ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በተቀናበረ ሴራና የፖለቲካ አሻጥር መፈንቅለ መንግስት በሚል ሰበብ በአንድ ቡድን የበላይነት በሚመራ የፌዴራል ጣልቃ ገብ ወታደራዊ ወረራ ስር እንዲውል ተደርጏል:: ይህንን በዓለም ታሪክ ተሠምቶ የማያውቅና ፍጹም ግልጽነት የጎደለው ድርጊት በጽኑ እናወግዛለን:: ለሃገር የማይበጅና ሁሉንም ወገን ዋጋ የሚያስከፍልና መሪውን የሚያስጠይቅ እርምጃ ባስቸኳይ እንዲቆም የሕዝቡን መብትና ነጻነት እንዲያከብሩ በጥብቅ እናሳስባለን::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የደብረጺዮን ፖለቲካ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ድርጅታቸውና የፌዴራል ካቢኔያቸው ሃገር ሊያፈርስ ሕዝብን ለአመጽ ከሚጋብዝ ድርጊት ተቆጥበው ዘለቄታዊ አብሮነታችን እንዲቀጥልና ሰላማችን እንዲከበር ግልጽና አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እንጠይቃለን:: የአማራው ሕዝብ የጀመረውን መብቱን የማስጠበቅና ሕልውናውን የመከላከል
ትግል ሳይከፋፈል አንድነቱን አጥብቆና አጠንክሮ እንዲቀጥል ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን::

እንዲሁም :-
1, መፈንቅለ መንግስት በሚል ተራ የቅጥፈት ፖለቲካ ሃገሪቷ ብሄራዊ አደጋ ላይ የወደቀች አስመስሎ በዶር አብይና በመንግስታቸው የቀረበው ዘገባና ፍረጃ  አስቸኳይ የሆነ ማብራሪይ እንዲሰጥበት::

2, ከአማራ ክልል ፍቃድና እውቅና ውጪ በጠቅላይ ሚንስትሩ አዝማችንት በፌዴራል ወታደሮች  የተደረገው ጣልቃ ገብነት ሕጋዊ አግባብነት የሌለው በመሆኑ ውሳኔውን የሰጠው አካል እንዲጠየቅ የፈጸሙትም ድርጊት በነጻና ገለልተኛ አካል እንዲጣራ

3, በአንድ ቡድንና ብሄር የበላይነት የሚመራው ወታደራዊ ካውንስል የሚወስዳቸው እርምጃዎች ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ባስቸኳይ ከአማራ ክልል ለቆ እንዲወጣ ጸጥታ የማስከበሩን ሃላፊነት ለክልሉ ፀጥታ ሃይል እንዲያስረክብ

4, ከሕግ አግባብና ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የታሰሩ የክልሉ አመራሮችና የአማራ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥፉት አደረሱ የተባሉም ካሉ በግልጽ እንዲዳኙ እንዲደረግ

5, ምንም ባልተጣራ ምክንያት በፌዴራል መንግስት በአማራ ሕዝብና መሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ : በሃገሪቱ የኢታማጆር ሹምና በጡረተኛው ጀነራል ላይ ምንነቱ ያልታወቀው  ግድያ ገለልተኛና እለም ዓቀፍ አጣሪ ኮሚሽን ተቋቁሞ ሂደቱ እንዲጣራ

6,  ከሕግ አግባብ ውጪ የአማራውን ሕዝብ ትጥቅ የማስፈታት እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲቆም: ሰላም ለማስፈን በሚል ሰበብ በሕዝቡ ላይ የሚደረገው ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን::

7, ኢሳት የተባለው ሚድያ ሕዝባዊ ወገንተኛነቱን ትቶ ለገዥዎች ልሳን በመሆን ያልተጣራ ዘገባና ውንጀላን በስፋት በማናፈስ እውነትን ለማድበስበስ ከሚያደርገው እርካሽ ተግባር እንዲቆጠብ ሕዝባችንም የሚዲያ ተቋሙን ቅጥረኛ ተግባር ተረድቶ እንዳይታለል በጥብቅ እናሳስባለን!

ተጨማሪ ያንብቡ:  " ኦሮማይ ! "  በቋንቋ ና በዘር መቧደን አከተመ፡፡… - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ድል ለሕዝባችን!

አቶ ሐይለገብርኤል አያሌው
ሻለቃ ዳዊት ወልደጎርጊስ
ዶር ዳንኤል ክንዴ
ዶር ሰማህኝ ጋሹ
አቶ ቴዋድሮስ ፀጋዬ
ወ/ሮ ፀሃይ መዝገቡ
አቶ ዳንዔል ሐይሌ
ወ/ሮ ሜሮን አጎናፍር
አቶ ንጉሴ አዳሙ
አቶ ሚካኤል ሳህሌ
አቶ ይፍሩ ረታ
አቶ ይፍሩ ሀይሉ
ዶር ግርማ ብሩ
አቶ በላይ ሀይሉ

3 Comments

  1. ከፕሮፌሰር መኮንን ብሩ ፌስ ቡክ ያነበብኩት መልስ ይሁናችሁ። ትህግስት ጥበብ ነዉ። መማር ከቻላችሁ ተማሩ።

    “ሙሑር ማለት ያለ በቂ መረጃ ዉሳኔ ላይ የማይደርስ ነው:: ስለዚህም በመሑር ስም ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን ወደሚፈልጉት አቅጣጫ መጎተት ያስተዛዝባል:: የሚቻል ከሆነ ሀገር እናረጋጋ ካልተቻለ እዉነቱን በእርጋታ እንጠብቅ::በዚህ አስፈሪ ወቅት ነገሮችን ዝም ብሎ 360 ድግሪ መዘወር ኢትዮጵያችንን አይጠቅምም:: እያደርም ተጠያቂ ሊያደርግ ይችላል:: ዶ/ር ደዊት ወ/ጊዮርጊስ እና ሌሎች ያለ በቂ መረጃ ያወጣችሁትን መግለጫ እቃወማለሁ:: ሁሉም ነገር በነፃ አካል ይጣራ ዘንድም ጥሪ አቀርባለሁ:: መንግስት እጁ ካለበት እመኑኝ ሀገር ምድሩን አስተባብረን እንደ ወያኔ እናስወግደዋለን:: ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር::(መኮንን ብሩ)”

  2. Dear old gays!!

    I advise you all to stop instigating unnecessary conflict between the people of Ethiopia in general and Amhara and Oromo in particular whose collaboration brought about a successful change in ousting the previous minority dictators. False allegations being promoted by you people living abroad on the current PM may not help these two big people of Ethiopia to sustain the changes we started to feel nowadays. If it is not for personal goals, don’t involve in such dirty political objectives to put yourself on the shoulders of oppressed people of Ethiopia who has been subjugated and oppressed by your forefathers and the TPLF regime for the last 150 years. Now it the time the people of Ethiopia to stand together against any possible tyrannical aspirations like yours. The model of government rule in Ethiopia that your are proposing, “Minlik’s model” that worked for his groups dominance will no more work in the 21st century. Think twice, or trice before you star posting such divisive propaganda.

  3. እናንተ ትክክል ለሀገራችሁ የምታስቡ ከሆነ አሁን እንኳን ለምን ሀገራችሁ ገብታችሁ አትታገሉም እዛ የተንቀባረረ ህይወት እየኖራችሁ የሚሰራን ሰው እቃቂር እያወጣችሁ እጅግ የተጋነነ እና ጥላቻ የተሞላበት ንግግር በማድረግ ብህዝቦች መካከል ጥላቻ እና መቃቃር እንዲኖር እያረጋችሁ ነው በአጠቃላይ እነ ዶ/ር አብይን እጎዳለሁ ብላችሂ ሀገሪቱን እየጎዳችሁ መሆናችሁን ማወቅ አለባችሁ ስማችሁ ከስር የፃፈው በሙሉ እዚህ ሀገራችሁ መጥታችሁ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁማችሁ ታግላችሁ ህዝቡን አታግሉ በተረፈ በአለም በኢኮኖሚ አንደኛ በሆነች ሀገር ተቀምጣችሁ የተቀማጠለ ኑሮ እየኖራችሁ የማቀሳሰር እና የሆያሆዬ ፖለቲካ ከዛው ከአሜሪካ ከንጉሱ ስርዓት ጀምሮ የተለመደ ነገር ነው ግን ምንም ለውጥ አምጥቶ አያውቅም ወደፊትም አያመጣም እና እባካችሁ እንደው ለሀገራችሁ ስትሉ እውነታንን እና ሀቅን መሰረት አድርጋችሁ ተቹ ለምሳሌ አሁን ያለው የኢትዪጵያ መከላከያ ሰራዊት የአንድ ብሄር የበላይነት ይታይበታል የሚባለው እጅግ ስህተት ነው እንደው የህዝብን ቅቡልነት ለማግኘት ሲባል ብቻ ነጭ ውሸት መዋሸት እና ህዝብን ግራ ማጋባት ሀገሪቱን ዋጋ ያስፈልጋል በተለይ ሻለቃ ዳዊት ሁሉ ነገራቸው የስሜት እና የጎረምሳ አካሄድ ነው እየሄዱ ያሉት እና እባካችሁ የጥላቻውን ፖለቲካ ትታችሁ ጽንፍ ባረገጠ መልኩ ትግላችሁን ቀጥሉ።

Comments are closed.

Share