በቴዲ ላይ የዘመቱ – በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዳይመቱ | ይገረም አለሙ 

ይህ መዳቡ መልኩን ቀይሮ ብረቱ ተመሳስሎ ቆርቆሮው ቅርጹን ለውጦ ሁሉም ወርቅ ተመስሎ ሊቀርብ ይችላልና ሆኖም ታይቷልና ፊት ለፊት ከሚታየው ብልጭልጭ ቀለሙ  በስተጀርባ ምንነቱን ማስተዋል እንደሚገባ ነው የሚያስገነዝበው፡፡ይሁን አንጂ አባባሉ የሚነገረው ለዚህና ለዚህ ብቻ ሳሆን ይልቁንም ለሰው ልጆች ነው፡፡

አንዳንዱ በአነጋግሩ ተለሳልሶ በገጽታው ፈክቶ ውሳጣዊ ማንነቱንና ትክክለኛ እሱነቱን ደብቆ ፍጹም መልካም ሰው መስሎ በመታየት ወዳጅ ዘመዱን ሳይቀር ይጎዳል፣ለጥቅም አሳልፎ ይሰጣል፣አንደውም አንዳንዱ ሊጠቀምበት ወይንም ሊያጠፋው እያደባ ቀን የሚጠብቅለትንና ቦታ የሚፈልግለትን ሰው በአፉ ፍጹም ወዳጁ መስሎ ከመቅረብ አልፎ ገበታ እስከመጋራት ሻይ ቡና እስከማለት ይደርሳል፡፡የሆዱን ሰይጣንነት በአፉ ስብከት መልአክ አስመስሎ መስሎ ተመሳስሎ ራሱን ለመጥቀም ግለሰቦችን ሲበዛም ሀገርንና ህዝብን ይጎዳሉ፡፡

የእዚህ ሰዎች ትክክለኛ ማንነትና ምንነት የሚጋለጥና የሚታወቀው በጣም ዘግይቶ ብዙ ጥፋት ካደረሱ በኋላ በመሆኑ ብዙዎች የእነዚህ ሰዎች ተከታይ ካልሆነም ደጋፊ በመሆን ሳያውቁ የጥፋት ተባባሪ ይሆናሉ፡፡ ብዙዎቻችንም የትናቱን ዛሬ እየረሳን ዛሬ ለሚገጥመን መልካም ነገር የምናጨበጭብ ለሚያጋጥመን መጥፎ ነገር  የምንጮህ ለምን ብለን የማንጠይቅ እንዴት ብለን ነገሮችን ለመመርመር ሰንዝርም መንገድ የማንሄድ መሆናችን ወርቅ ያልሆኑ ብዙዎች  ራሳቸውን በአብለጭላጭ ወርቃማ ቀለም አመሳስለው እንዲያጭበረብሩ ስተው እንዲያስቱ  እንመቻችላቸዋለን እናመቻችላቸዋለን፡፡

ይህን ሁሉ በመንደርደሪያነት አንድል ያደረገኝ ሰሞኑን የተለቀቀውን የቲዎድሮስ ካሳሁን ኢትዮጵያ ነጠላ ዜማ አንተቻለን ብለው ወጥተው የቅናት የምቀኝነትና የጥላቻ ስሜት በጉልህ ከታየባቸው ሰዎች መካከል አንድ የማውቀው የሚያብለጨልጭ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለም የሚለው አባባል ሊነገርለት የሚችል ሰው ማግኘቴ ነው፡፡ ዳኝነት መኮንን፡፡

ይህን ሰው የማውቀው ከአዲስ ነገር ጋዜጣ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ስራ የጀመሩበት ቦሌ መድሀኒዓለም አካባቢ በነበረው  ቢሮአቸውን በተከፈተ ሰሞን  ተገኝቼ ነው ብዙዎቹን የጋዜጣውን ባልደረቦች የተዋወኩዋቸው፡፡ ከዛም ብዙም ሳይቆይ በዚህ አጭር ግዜ እንዴት ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ ሊያነሳ የሚችለውን አዛው አካባቢ የተከራዩትን የተሟላ ቢሮ ጎብኝቻለሁ፡፡ ከአንዳንዶቹ ጋር ደግሞ ዋናውን ባለቤት አብይ ተክለማሪያምን ጨምሮ ብዙም ባይሆን በአካል ተገናኝተናል፡፡  በዚህ ምክንያት ነበር ወ/ት ብርቱካን ከሁሉም ጋር ሊባል በሚችል መልኩ የቅርብ ጓደኛ እንደነበረች ለማወቅ የቻልኩት፣በተለይ ደግሞ ዋና ከሚባሉት ጋር አብራ ምሳ ትበላለች ቡና ትጠጣለች፡፡

ቅርርባቸው ይህን ያህል ሆኖ ሳለ ግን ወ/ት ብርቱካን ላይ ወያኔ ፈንጂ ባጠመደበት ሰአት እነዚህ ገበታ የተጋሯት ሰዎች ፈንጁን በሩቅ ርቀት ማፈንጃ መሳሪያ ለማፈንዳት ነው የሞከሩት፡፡ ነገሩ የሆነው ከብዙ በአጭሩ እንዲህ  ነው፡፡ ወቅቱ  ብርቱካን ይቅርታ አልጠየኩም ብለሻል አስተባብይ አለበለዚያ መልሰን ቃሊቲ እንስገባሻለን ተብላ አይደለችም እሷ ወዳጅ ዘመድና አድናቂዋቿ ይጨነቁ የነበረበት ታህሣሥ 2001ዓም ነው፡፡  በመጨረሻ ለተጠየቀችው መልስ ብላ ያዘጋጀችውንና ቃሌ የሚል ርዕስ የሰጠችውን  ጽሁፍ ቅዳሜ ታህሳስ 18/2001 ዓም ለንባብ ለሚበቁ ጋዜጦች ላከች፣ ከተላከላቸው ጋዜጦች አንዱ የሆነው የአዲስ ነገር ሰዎች ማለትም አነ ዳኝነት መኮንን ወ/ት ብርቱካን አላስተባበሉም  በማለት እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የፊት ገጽ ዜና አድርገው ወያኔ ብርቱካንን ማሰሩ አንዲመቸው መንገድ የመጥረግ ያህል ስራ ሰሩ፡፡ በዚህ አላበቁም ወያኔ እሷን ሲያስር የአድናቂዎቿና ደጋፊዎቹ ተቃውሞና ቁጣ እንዳይነሳ ብርቱካን ዩኒቨርስቲ በነበረች ግዜ እንዲህ ነበረች አንዲያ ታደርግ ነበር በማለት ብዙ አተቱ፡፡ ለምን ዓላማና ግብ አንደዛ ማለት እንዳስፈለጋቸው በአራት ነጥብ መናገር ቢቸግርም ተንኮል ለመሆኑ ግን ምንም አያጠራጥርም፡፡ ብርቱካንም በሁለተኛው ቀን ታህሣሥ 20/2001  እንደ ወንበዴ ከመንገድ ታፍና ቃሊቲ ተወሰደች፡፡

የእነ ዳኝነት ነገረ ሥራቸው በወያኔ ተባባሪነት የሚያስጠረጥር ቢሆነም ድርጅታቸውን ዘግተው ሀገራቸውን ጥለው ለስደት የበቁት በወያኔ  በመሆኑ ለህሊና ፍርድ ያስቸግራል፡፡ የመረጃ ቋት ላይ ተቀምጠው የሁለት ምርጫዎች ወግ የሚል የአሉባልታ መጽሀፍ የጻፉት አቶ በረከት ሰምኦን አዲስ ነገር የተቋቋመው በአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ነው በማለት ከሲአይ ኤ ጋር ለማገናኘት የሞከሩበት ማስረጃ ያልቀረበበት ከመሆኑ በሻገር አዲስ ነገሮች በብርቱካን ላይ የፈጸሙት አድራጎት ለሲአይኤ የሚያስገኘው ፋይዳ አይታይምና የአቶ በረከትን ፍረጃ ለመቀበል ቢቸግርም ማእድ በተቋረሱዋት ብርቱካን ላይ ያውም በዛ ሰው ሁሉ ስለ እሷ በተጨነቀበት ወቅት ያንን መጻፋቸው ለምንና ስለምን ማሰኘቱን ሊያስቀረው አይችልም፡፡ አንዳንድ ሰዎች በወቅቱ በአዲስ ነገር ሰዎች ማዘናቸውን ገልጠው ለምንስ አደረጋችሁት ብለው ጠይቀው ጽፈዋል፡፡

አዲስ ነገሮች ማለትም እነ አቶ ዳኝነት ብርቱካን ከታሰረች በኋላ በጓሮ በር ገብቶ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለመሆን ከበቃው አቶ ስዬ አብርሀ ጎን ተሰልፈው ፓርቲያችን መስመሩን እየሳተ ነው በማለት አመራሩን ለማስተካከል ትግል የጀመሩትን የፓርቲውን መስራቾች ማውገዙን ተያያዙት፡፡ የጋዜጣው ባልደረባ የነበረው  አቶ መስፍን ነጋሽ   የዚሁ ዘመቻ አካል የሆነ ያለዎት ቀሪ ሂሳብ በሚል ርዕስ ሐምሌ 11/2001 ዓም ጽሁፍ አወጣ፡፡ በሳምንቱ ሐምሌ 18/2001 ሀሳብ የሌለው ሂሳብ በሚል ርዕስ ምላሽ የሰጡት ፕ/ር መስፍን ርዕሱ ሂሳብ ስለሆነ መስመሮቹን ቆጠርኳቸው 183 ናቸው፣መጣያው “በነገራችን ላይ” የሚለው ከተጨመረ 195 ይሆናሉ ..በማለት ጽሁፉን በጽሞና ማንበባቸውን የሚያሳይ መንደርደሪያ ከሰጡ በኋላ ..አንደ ስድብም ቢሆን በጋዜጠና ነጻነት አምናለሁ ግን ይግ ጋሬ መጫጫር ማሰብ ተብሎ አንጀራ የሚያበላ ከሆነ የዕድል ጉዳይ ካልኾነ ስራ ፈት ለምን ይኖራል ? በማለት ራሱን ከሰቀለበት ከፍታ አውርደው ትክክለኛ ማንነቱን አሳዩት አሳዩበት፡፡ በዚህም ክፉኛ ቅስሙ ተሰብሮ ያለ ቁመቱ አድጋ የነበረች ልቡ ከቦታው ተመልሳ እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያነሳ ሆኖ ዛሬ መስፍን ነጋሽን በሌለበት ጉዳይ ማንሳቴ ዛሬ ዳኝነት ውስጥ የምናየው ነገር የዋለ ያደረ የሰነበተ መሆኑን ለማሳየት አብዩ ማስረጃ አዲስ ነገር በመሆኑ ሁለትም ከማን ጋር አንደምትውል ንገረኝና ማን እንደሆንክ ልንገርህ ስለሚባል ነው፡፡

ከዛ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አዲስ ነገር ለስደት በቃ፤ ከዛ በኋላ ዳኝነትን አልፎ አልፎ ስሙን ብሰማም ጽሁፎቹን ባነብም አንደዚህ ሰሞኑ ያለ ከመስመር የወጣና ወጥ የረገጠ የሚባል አይነት ድርጊት ሲፈጽም አልሰማሁም ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ግን  የቲዎድርስ ካሳሁን ነጠላ ዜማ ተለቆ ያውም ኢትዮጵያ የሚል ሙሉው አልበም የሚለቀቅበት ግዜ ተነግሮ ሳለ ሙሉውን አዳምጠው ለመተቸት ወይንም እንደታየባቸው ለመዘባረቅ ትእግስት አጥተው አንድ ቲዎድሮስ ከሚባል ቴዎድሮስ ካሳሁን ምን አይነት ግጥም መጻፍና እንዴት ብሎ መዝፈን እንዳለበት ምክር አይደለም ትዕዛዝ ለመስጠት ከሚቃጣው ቢከፍቱ ተልባ ከሆነ ሰው ጋር ሆነው  ራሳቸውን ያስገመቱበትንና ያጋላጡበትን ሲናገሩ ሰማን፡፡

ለመሆኑ ጸባቸው ከማ ነው? ከኢትዮጵያዊነት፣ ከሰንደቅ ዓላማው፣ ወይንስ ከቲዎድርስ መግነንና መታወቅ፡፡ ሰይጣ ለተንኮሉ ከመጽሀፍ ቅዱስ ይጠቅሳል እንደሚባለው  ኮሶአቸውን በማር ጠቅለው ሊግቱን አንደኛው እየደጋገመ ስለ ኢትዮጵያ በመዝፈኑ ደስተኛ ነኝ ሲል ሰማነው፡፡ አቶ ዳኝነት ግን ይህንንም ለማለት አልቻለም፡፡ ያኛውም ቢሆን ይህን ያለው ለማስመሰል እንጂ ከልቡ እንዳልሆነ በቃ የቲዎድሮስ ኢትዮጵይ ይህች ነች በማለት ተመጻድቆ ተጋለጠ፡፡ አረ ለመሆኑ ልጅ ቴዎድሮስ የአንተ ኢትዮጵያ የቷ ነች? ሰንት ኢትዮጵያስ ነው ያለችው? አፍ ሲያመልጥ.. ነው የሚባለው፡፡

የሁለቱም ሰዎች የቃላት አጠቃቀማቸው የምጸት አነጋገራቸው ቅናት ምቀኝነት የተጠናወታቸው መሆኑን እንጂ ለማሳደግ የሚተቹ ላለመሆናቸው በበቂ ያረጋግጣል፡፡ በግማሽ ቀን ይህን ያህል ሰው ያውም በአንድኛው ዩቲዩብ ብቻ ተመልከቶታል በማለት ሲናገሩ የድምጻቸው ቅላጼም ሆነ የቃላት አገላለጻቸው እርር ደብን ማለታቸውን ያሳያል፡፡  ይህ ንዴታቸውም ነው የቲዎድሮስ ተከታይ ያሉትን በሙሉ መንጋ በማለት በድፍረት ለመሳደብ የበቃቸው፡፡ ይሄ ነው ጋዜጠኝነት እንከፎች!

በቲዎድሮስም ላይ ዘመቱ አድናቂ ደጋፊውንም ተሳደቡ ዘለፉ  በአንድ ድንገይ ሁለት ወፍ እንዳይመቱ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ይሄውም  የጥላቻ ስሜታቸውን ለማስተንፈስም ይሁን  የበቀል ጥማቸውን ለማርካት ወይንም ስውር ተልእኮ ኖሮአቸው ባናውቅም ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየትና መከወን ይገባል፡፡ በቲዎድሮስ ላይ በሚወረውሩት ድንጋይ የቲዎድሮስ ደጋፊ በአብዛኛው የወያኔ ተቀዋሚ ነው ተብሎ ስለሚታመን የእነርሱ ብልግና አስቆጥቶት ለእነርሱ መልስ በመስጠት ሲጠመድ ስሜቱ በዚሁ ጉዳይ ሲታሰር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለው ትኩረት እንዲቀንስ ወይንም አቅጣጫ አንዲስት የማድረግ ነገርም ሊኖር ይችላል ብሎ ማሰብ ደግ ነው፡፡ ጠርጥር ከገንፎም ይኖራል ሰንጥር ይባል የለ፡፡

ስለሆነም ይህ እንዳይሆን ሁለቱንም በአግባቡና በወጉ እንደ እነርሱም ሳይባልጉ በማስተናገድ ፍላጎታቸውን ማምከን ዓላማቸውን  ማክሸፍ ያስፈልጋል፡፡ ብልግናቸውን ሀገር አውቆት ማንነታቸውን ህዝብ ተረድቶት ታርመው እንዲመለሱ ካልሆነም ቫይረሳቸውን እየረጩ ሰው እንዳይበክሉ ወይ መድሀኒት ልንፈልግላቸው ግድ ይላል፡፡

1 Comment

 1. Ato yegerem tebarek abo !!ANJET ARIS TSHUF NEW !

  be Teddy lay enan endetenehubet,, eneman esat endelekosu lib bilehal ?

  be tekawami party yeteselefut , birr yemezerfut nachew

  yaw endetelemedew kibretun yecharew demo Hager wedad tebiyew

  comediyan entone kene wendimu new !

  Teddy alitemed selachew ,, be sim matfat tenesubet

  Egzeyabher yeshomewin ,, manim leshrew aychlim

  Teddy ke Egzeyabher yetesetew chlota ena yesew mewded alew !

  ye Teddi telatoch yergefu !

  hmmmmmmmm 7 honew tenesubet eko jal !!

Comments are closed.

Previous Story

ፖለቲካም እንደ ሳይንስና እንደ ሂሳብ መታየት ያለበት ወይስ ሳይንሰ-አልባ ! – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

Next Story

ይህን ነበር የምፈራው – ነፃነት ዘለቀ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop