Hiber Radio: ግብጽ ኢትዮጵያ በአባይ ጉዳይ ጀርባዋን ሰጠችኝ ስትል ስጋቷን ገለጸች

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ፕሮግራም

<< ...ጆርጅ ዚመርማን ተኩሶ በገደለው የትራይቮን ማርቲን ጉዳይ በተሰጠው ጠቅላላ ውሳኔ ቅሬታ አለኝ …ይሄ ነገር የተገላቢጦሽ ቢሆንና ጥቁር ጎልማሳ መሳሪያ ያልያዘን ምንም ጥፋት ያላጠፋን የ17 ዓመት ነጭ ወጣት ገሎ አይ እኔ ፈርቼ ነው የገደልኩት ቢል ውጤቱ እንዲህ ይሆን ነበር የሚል ጥያቄ ያስነሳል? እኔ በበኩሌ አይመስለኝም። በሕግ አንጻር የተሰጠውን ፍርድ ስንመለከተው ግን ... >>

በአሜሪካን አገር ጠበቃ የሆኑት አቶ ሳህሉ ሚካኤል የ17 ዓመቱን ወጣት

ትራይቮን ማርቲን በጥይት የገደለው ራሱን ለመከላከል ተብሎ ነጻ መባሉን አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

<< ...እስርና ማስፈራራት የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ዘመቻ እንደማያስተጓጉለው ደሴና ጎንደር ላይ የሆነው ምስክር ነው።...ሰሞኑን ከሰልፎቹ በሁዋላ የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረትና የተለያዩ አገራት ዲፕሎማቶች በአንድነት ጽ/ቤት ከአመራሩ ጋር ተወያይተዋል። የሰሞኑን በህብረቱ በኩል የወጣውን ሪፖርት በአወንታ ነው የምናየው። በእኛ በኩል በዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ሁኔታ ትግሉን ወደፊት ለመቀጠል ወስነናል። የፋይናንስ አቅም ችግር ግን አለብን...>>

የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት አስተባባሪ ግብረ ሀይል ም/ል ቃል አቀባይ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሰጡን ወቅታዊ ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ)

ፕ/ት ኦባማ ያለ ወንጀሉ በጥይት የተገደለውን የ17 ዓመቱን ትራይቮን አስመልክቶ በይፋ ተናገሩ <<...ከ35 ዓመት በፊት ትራይቮን ማርቲን እንደኔ ይሆን ነበር ...>> (ከመቶ በላይ የአሜሪካ ከተሞች የተደረገውን የገዳይን ነጻ መባል የተቃውሞ ንቅናቄ በዘገባችን ቃኝተነዋል)

የአውሮፓ ሕብረት የፓርላማ አባላት እና የሰብዓዊ ጥበቃ ኮሚቴ አባላት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው በአገዛዙ ሰብዓዊ መብት ላይ ስለሚያደርሰው በደል ጠቅሰው የሰላ ሂስ ሰንዝረዋል ።ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሁሉም የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያና ግብጽ በተባበሩት መንግስታት የጸደቀውን የውሃ ኮንቬንሽን ሳይፈርሙ ቀሩ

(ሙሉ ዝርዝሩን ከወቅታዊው ዘገባ ያዳምጡ)

ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን

ዜናዎቻችን
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከእስር ቤት ለፕ/ት ኦባማ የሚደርስ ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ

አሜሪካ ሰብዓዊ ዕርዳታን የማይነካ የኢኮኖሚ ማዕቀብና በባለ ስልጣናቱ ላይ የበረራ ማዕቀብ እንድትጥል ጠይቋል

መድረክ በመቀሌ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ ማካሄዱ ተገለጸ

በአገር ውስጥ በበረራ ላይ የነበረ አውሮፕላን በድንገት አረፈ

ግብጽ ኢትዮጵያ በአባይ ጉዳይ ጀርባዋን ሰጠችኝ ስትል ስጋቷን ገለጸች

አሜሪካ በሟች ጥቁር ወጣት ትራይቮን ማርቲን ገዳይ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳቢያ ከመቶ በላይ ከተሞች ተቃውሞ ተደረገ

ቢዮንሴና ጄዚም ተሳትፈዋል

ፍሪያስ ኩባንያ ያባረራቸውን የስራ ማቆም አድማ ተሳታፊዎችን ወደ ስራ ለመመለስ በተመለከተ ከሽማግሌዎች ጋር ለመወያየት ጥሪ አቀረበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Share