ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<…ፖሊሶቹ ፍላጎታቸው ሰላማዊ ሰልፈኛውን ተንኩሶ ሰብስቦ ማሰር በነር በትግስት ተቃውሞውን አድርገናል ። በሰልፉ ላይ ሕዝቡ ምሬቱን ገልጿል…>>
ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ የም/ቤት አባል የዛሬውን የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ለህብር ከሰጠችው ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<<…የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ወደ ኢትዮጵያ ከመሄዳቸው በፊት በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ሰሞኑን የታሰሩትን ጋዜጠኞች፣ ጸሐፍትና የተቃዋሚ አመራሮችና አባላት በተመለከተ ትኩረት እንዲሰጡ ለማድረግ ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ድምጻችንን እናሰማለን…>>
አቶ ጌታነህ ካሳሁን የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ በዋሽንግተን ስለጠሩት ሰልፍ ከሰጡን ማብራሪያ
<<…በአዲስ አበባ ብዙሃን በጉስቁልና ጥቂቶች በመንደላቀቅ ይኖራሉ…>>
የህዝቡ ሕይወት በውጭ ጸሐፍት አይን(ልዩ ዘገባ)
<<…በአሜሪካ መንግስት ፊት ድምጻችን በአግባቡ መሰማት አለበት በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ስቃይ ትኩረት እንዲያገኝ ሰላማዊ ሰልፍ ብቻ ሳይሆን አብረው መታሰብ ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንስጥ!…>>
አክቲቪስት አቶ ዱላ አብዱ ከቴክሳስ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከጆን ኬሪ ጉዞ በፊት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)
የጋምቤላ የግዳጅ ሰፈራ ያስከተለው ማህበራዊ ጉስቁልና(ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
የታሰሩ ጋዜጠኞችና ጸሐፍት ቤተሰቦች ዛሬም ታሳሪዎቹን ሊያዩ አልተፈቀደላቸውም
ኢሰብዓዊ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው የሚል ስጋት አለ
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ታሳሪዎቹ ሀሳባቸውን በመግለጻቸው መታሰራቸውን ገለጸ
አንዷለም አራጌ በእስር ቤት የሚፈጸምበትን ግፍ በመቃወም የረሃብ አድማ ሊያደርግ ይችላል ተባለ
ኤርትራ ለእስራኤል ወታደራዊ ቤዝ ፈቀደች
የጦር ጄትን ጨምሮ በምትኩ መሳሪያ አገኘች
የመብት ጥያቄ ያነሱ የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ተጋጩ
ፖሊስ በሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ የተሳተፉትን ለማሰር ትንኮሳ ሲያካሂድ ነበር
ሁለት የኢትዮጵያ አገዛዝ ዲፕሎማቶች ሱማሊያ ውስጥ ታሰሩ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ