ከቶ ዬት ይሆን ዬፍላጎታችን ሴሉ ያለው (ከሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 23.03.2014 ( ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

በእኔ ውስጥ እኔ ነኝ ያለሁት። እማስበውም አምጽፈወም በነፃ ዕይታ መንፈሴን ቃልቲ ወይንም ቂልንጦ ሳልክ ውስጤ የሚለኝን በድፍረትና በልቡ ሙሉነት ነው። ስለዚህ እኔ „እኔን“ ስገልጽ ተሸማቅቄ ወይንም ምን ይሉኝ ብዬ ወይንም አዩኝ አላዩኝ ብዬ ተሸፋፍኜ አይደለም። በዬትኛውም ዘመንና ጊዜ እኔ „እኔን“ ተውሶት ወይንም ተበድሮት አያውቅም። በጣም ብዙ ሰዎች በተለያዬ አጋጣሚ ከልጅነት እስከ እውቀት ሥርጉተን ያውቋታል። ጊዜና ሁኔታ ሲፈቅድም ቆመው ይመሰክራሉ። ባነብም ባዳምጥም እምኖረው ግን እራሴን ሆኜ ነው – በጣም በእርግጠኝነት። ተዳብሎ የሚኖር ፍላጎት ሆነ ጭሰኛ ወይንም ሞፈር ዘመት ስሜቴ ያዘለ ወይንም የሙጥኝ ብሎ ጥገኝነት የጠዬቀ ፍላጎት ኖሮኝ አያውቅም። ለዚህም በሙሉ መንፈስ እራሴን ሆኜ እንድኖር መንፈሴን በማያቋርጥ የራስ መተማማን መስኖ አልምተው ያሳደጉኝን ወላጆቼንና እጅግ የሚናፍቀኝን ማህበረሰቤን አመሰግናለሁ።

 

ስለዚህም እኔ ለምሰጠው አስተያዬት እኔን የወከለ ስለሆነ ጊዜ ወስዳደችሁ ለምታነቡት ወገኖቼ እንዲሁም፤ አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ አስተያዬት ለምትሰነዝሩት ወገኖቼ እኩል አክብሮት አለኝ። እማርበታለሁም። አመሰግናችኋላሁ። አለፍ ብላችሁ መሄድ ካሰኛችሁም ሥርጉተ ጠጥታው ያደገችው ፈተና ሆነ ተመክሮ ሁሉንም ለማስተናገድ ስለመቻሏ መለኪያዋ ስለሚሆን አዝናንታ እንደምታስተናግደው ተሰፋ አላት – እራሷ።

 

ትናንት ነበር ያነበብኩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፓርቲያቸውን ወክለው ወደ አሜሪካ የተዘጋጁበት ጉዞ እንደ ታገዱ ከዘሃበሻ። ከዚህ የባሰ ፈተና ብጠብቅም አዘንኩኝ። https://zehabesha.info/archives/13729

እጅግ ያሳዘነኝ ደግሞ ከአንባብያን የተጻፉት አስተያዬቶች ናቸው። ለመጻፍም ያነሳሳኝ ይሄው ነው። አንዱ ወያኔ ያዘጋጀው ነው አትመኑት የሰማያዊ ሊቀመንበር እንደ ልደቱ ነው ይላል። ሁለተኛው ደግሞ ወርዶ ታች ሰፈር ይቆጥራል። ወያኔ ከወሰደው የእገዳ እርምጃ ሁለቱም አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ አስተያዬቶች አሳዘኑኝ። ሰው እንዴት እራሱን ማሸነፍ ይሳነዋል። እኛ እንዲህ መንደር ካሰኘን፤ ስለምን ወያኔን እንነቅሳለን። ለሁላችንም መዳኛችን ኢትዮጵያዊነታችን ነው። ማናቸውም ሰው ሲያጠፋም ሆነ በጉ ሲሰራ መመዘን ያለበትም በዜግነቱ መሆን አለበት እንጂ ጎጡ?!  ክብርና ግርማ፤ ፍቅርና ትህትና፤ ናፍቆትና መሆን ያሉት ከሚስጥሩ እንብርት ከኢትዮጵያዊነት ላይ ነው። የትናንት ጀግኖቻችን ናሙናነት ወተታቸው የታለበው፤ የሞቱት የተሰዉት ለሚስጥርነታቸው ነው …. ጠበል ቢጤ በዬጓዳው ሳያስፈልግ አይቀርም …. እኔ እማውቀው የሰማያዊ ሊቀመንበር ኢ/ ይልቃል ጌትነት ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ነው። ከዚህ ባለፈ መንፈሳችን ተቋማቱ ላይ እናሳርፍ፤ ፍቅራችንም እምነታችንም ከጋራው አመራር ላይ …. ከፓርቲው ንጥር መርህ፤ ይህ ከሆነ በስበብ አስባቡ በሚፈጠሩ ስንጥሮች አንታወክም ….

ተጨማሪ ያንብቡ:  የምንፈልጋቸው ነገሮች ነገር ግን ደግሞ ሂደታቸው የጨለሙብን !!  ግልጽ መሆን ያለባቸው መሰረተ-ሃሳቦች!! -   ፈቃዱ በቀለ

 

ሌላው ያነበብኩት አስተያዬት ብቃትን ማዬት የሚናፍቀን እንዳለን ሁሉ፤ ዓይንህ ላፈር የምንል መኖራችን ፍላጎታችን ጋር ምን ያህል እዬተላለፍን እንደመንባዝን ሰፊ ስዕል ነበር። ሰማያዊ ሲመሰረት ጀምሮ እኔ ከልብ ሆኜ እከታተለዋለሁ። አሁን ባላቤት ያላቸው ይመስለኛል ውጪ ሀገር። የሎቢ ተግባር የሚሰራላቸው። ቀደም ባለው ጊዜ ባልነበራቸው ሰዓት የሚያቅዷቸው፤ ሃላፊነት ወስደው የሚወስዷቸው ፈጣንና ደፋር እርምጃዎችና ውጤቶቻቸው፤ ፈተናዎቻቸውና ፈተናውን ተከትለው የሚያሰዮዋቸው ጥንካሬ ሁሉ ይደንቁኝ ስለነበረ ከረንት ላይ አንብቤ አስተያዬት ከሥር በጣም በትጋት እጽፍበትም ነበር።

 

ጉልህ ድፍረታቸውን ያዬሁበት የመጀመሪያው እርምጃቸው የሙሶሎኒን ግፍ ሊዘከር አይገባውም በሚል መንግሥት ነኝ የሚለው አካል ተቀምጦ እነሱ ነበሩ ቀዳሚውን የመከራውን ገፈት ፉት ያሏት፤ ከዛም በኋላ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ግልጽ ያለ አቋም መወሰዳቸው ብቻ ሳይሆን ተግባር ላይ መገኘታቸው አበረታች ነው – ለእኔ። በዛ ላዩ ታች እሳት በሚጋረፍ ቃጠሏማ ወጀብ ሆነው ዕለታዊ ቋያውን ተቀብለው በቅንነትና በሃቀኝነት እዬተንገረገቡ መገኘታቸው ወያኔ ሊያሰኛቸው ከቻለ እውርነት ነው። ሰማያዊ እንደ ተቋም ጠንካራ ራዕይና ጠንካራ ፍላጎት ይዞ በድፍረት እዬተንቀሳቀሳ ያለ ቀንበጥ ፓርቲ ነው – ለእኔ። ነገ ምን ይሆናል? ሥርጉተ ጠንቋይ አትቀልብም።

 

አሁን ባለው ሁኔታ ግን መሰረት የያዘ የተግባር ትልማና ክንውን እያዬሁ ነው። አንጋፋ የሚባሉት አብሶ ለህሊና መሰናዶ ቁብ ሲሰጡት አይታዩም። እነሱ ግን ህሊናን ከማሰናዳት ጀምሮ ያለው መንፈስ ጠንካራ ነው። አጋዥ ተቋማትን ወይንም ክንፎችን አጠናክሮ ማውጣት ብቻ ሳይሆን እንደዬባህሪያቸው „የእንቢታን“ተግባር መሸለማቸው በራሱ የብርታት መለኪያ ነው። አጋጣሚዎች ሳይበክኑ አቅምን ከሥር በመገንባት እረገድ ጅምሩም ፍሬ አዘል ነው። በአጭር ጊዜ ዘለግ ያለ ተግባርና ተመክሮውም ጠቋሚ ተስፋ አለው። ይህ ውጤታማ የግልና የቲም ተግባር ተናጠላዊ ፍርጃ የሚያሰጥም አይደለም። አመራሩ መደማመጥ፤ መከባበር መተማመን አስከቻለ ድረስ አውዱ ሰላም ነው፤ በሰላም መስመር ደግሞ ትርፍ አለ ….

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለሻለቃ ዳዊት - ሰለሞን ሥዩም ሲያትል፣ ዋሽንግተን

 

ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አንድ ሥንኝ ልዋስና „የድርሻ ልውውጡ“ ሰርቷል የሚያሰኘው ቁምነገር ያለውም ከዚህ ላይ ነው። ወጣት ለመኖር የሚጓጓ ቢሆንም ከፍላጎቱ በታች ባለው እንጂ በላይ ባላው ነገር አይደለም። እውነት ለመናገር ወጣቶች ለግል ኑሯቸው ስስታሞች አይደሉም። እንዲያውም የወያኔ መሰሪነት ዶክተሪን ለግል መኖር ነበር። ግን ተፈጥሯቸው አልፈቀደላቸወውምና በዬአጋጣሚውም የምናዬው የወያኔ ፍላጎት አብሶ ኢትዮጵያን በሚመለከት ተዘቅዝቆ ሲንጠለጠል ነው። ስለሆነም በዚህ ጠቀራማ ዘመን ብሄርና ብሄረሰብ እዬተባሉ ያደጉ የትናንት ለጋዎች በንጹህ መንፈስ ስለ አንድ ህዝብና አንድ ሀገር ፊት ለፊት ወጥተው፤ በባንዳነት ሀገርን በመበተን ላይ ያለውን ወያኔ እዬተፋለሙ መገኘታቸው ሊያስመሰግናቸውና እግዚአብሄር ይስጣችሁ ሊያሰኛቸው ይገባል። ይህንን በማደረጋቸውም  በዚህ ዙሪያ ቅሬታ ያላችሁ ወገኖች ድምጻችሁን አትስጡን ሲሉም አዳምጫቸዋለሁ። በጣም ደፋር እርምጃ ነው። ስለምን ትግላቸው ትውልድና ታሪክን፤ ሀገርን ከማዳን ላይ በጽኑ የተገነባ ስለሆነ ነው እንጂ በነፍስ ወከፍ የነበራቸው ቦታ ሆነ ኑሮ በቂ ነበር …. ማለት ይቻላል።

 

ግን አኛ አልታደለንም፤ የሚሻል፣ የሚበልጥ፣ የተወጣላት ነገር የማዬት። እንዲያውም የነጻነት ትግሉ ቤተሰቦች ሆነን አሁን በተገኘው እውቅናና ወያኔ በወሰደው የጉዞ እገዳ እርምጃ መስጥረን ደስ ሚለን የምንኖርም እንኖራለን። የእኛ ጀግናችን አደባባይ ወጥቶ እልፎችን አሰልፎ ወደ ፊት ሲገሰግስና ትርፍን ሲዝቅ ሳይሆን፤ ይልቁንም  በጠላት እጅ ገብቶ ሲታሰር፤ ሲታፍን በጠራራ ጸሃይ በባሩድ ሲነድ፤ ወይ እንደ የኔሰው ገብሬ በቤንዚን እራሱን አርከፍክፎ አቃጥሎ አምድ ሲሆን፤ ወይን ሀገር ጥሎ ተሰዶ ፊት ለፊት መጋፈጡን ሸሽቶ ለዕለት ኑሮው ሲያድር ብቻ ነው። በቃ ያልተሰረ ታታሪ፣ ያልተፈነ ባተሌ ስለነገ የሚፈለገውን ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት እወስዳለሁ ብሎ ለሚገፋጥ  ከወያኔ በበለጠ እኛው ስናሸው ሲሰኘንም ወያኔ በማለት ወስደን ከጠላት ጋር ስንለጥፈው  – አለመታዳል።

 

ከዚህ በተጨማሪ እኔ በግሌ „ሰማያዊ ጊዜ ገና ነው ተገጥሜ ለመሰፋት እኔ ለጋ ነኝ። መሬት ረግጬ እራሴን ችዬ ለመንቀሳቀስ ጊዜ እሻለሁ፤ ወይንም እራሴን ችዬ እድሌን እሞክራለሁ“ ማለቱን እራሱ ልናከብርለት ይገባል። ከእንጨትም፣ ከተራራም፣ ከቀንም፣ ከቤትም፣ ከሰውም፣ ከመሬም ዕድል አለ። እንታገልለታለን የምንለው ነፃነት እኮ ይህው ነው። ልንጫነው በፍጹም አይገባም። በተገኘው አጋጣሚም ካላፍላጎቱ በተጽዕኖ አቅጣጫውን ልናስተው አይገባም።  በመንገዱ ላይ ጋሬጣ ልንሆንበት አይገባም፤ እንደ ገራራ የማይገራ ኢጎም አድረገን ልናዬው አይገባም፤ ጉዙውን ሆነ ፍላጎቱን በፖዘቲብ ልናይለት ይገባል። ካለፉት ስህተቶች ተምሮ፣ በአገኘው ተመክሮ ተነስቶ ለትውልዱ አዲስ መንፈስ ምቹ የሚሆን ሽግሽግ ማደረጉ ራሱ ለእኔ በግሌ በጣም በጎ ነው። በራስ መንገድ፤ በራስ መርህ፤ በራስ ቴስት መንፈስን ለመምራት መወስንና መቁረጥ አንድ ጥበብ ነው። ወቅትንና ጊዜን፤ ፍላጎትንና ተስፋን ማድመጥ መቻል የአቅም ሥነ – ሥርዓት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ሆይ! ይልቁናስ ለማይቀረው ፍልሚያ ተዘጋጅ!! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

 

በአንፃሩ ተናጠላዊ ትግሉ ጎድቶናል፤ ፍላጎታችን አጓቷል፤ ራዕያችን አርቋዋል፤ ተስፋችን አጫጭቷል፤ ለጠላት ኢላማ የቅርብ ተጠቂ አድርጎናል፤ ጉልበታችን – ተመክሯችን – መክሊታችን ብናስተጋብረው የበለጠ ህዝብ በማሰለፍ አቅምና ችሎታ ይኖረናል፤ በአንድ ላይ ሆነን አብረን እንሰራለን፤ ተዋህደን ወይ ተቀናጅተን የሚሉም ከተገኙ ወሸኔ ነው።  የእነሱንም ነፃነት  ልናከብርላቸው ልናዳምጣች ይገባል። የሚመቻቸውን የሚያውቁት እነሱ መሬት ላይ ያሉት እንጂ እኛ አይደለንም።

 

በተረፈ ዬፓርቲዎች ፉክክር ለእኔ በጎ ነው። ለሚደግፉት ፓርቲ የበለጠውን ጊዜ መስጠት ወይንም ፕሮሞት የሚያደርጓቸውም ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ በጎ ነው። ችግሩ ያለው ነፃነት ለራሳችን የምንፈልገውን ያህል ከሌላው ላይ ሲደርስ ወይንም ለሌላው ለመስጠት ንፉጎች መሆናችን ነው። እንደ እኔ አንዱ በአቅደው ላይ ነፃነቱን ጠብቆለት ሌላው በመሳተፍ በማገዝ፤ ሌላው በአቀደው ላይ ሌለኛው ኃላፊነቱን ወስዶ በመጋራት ፍላጎታችን ዕውን ማደረግ ይገባል እንጂ አንዱ በሌላው ላይ በመንፈስ በማማጽ፤ ወይንም ልብን በማሸፈት በጠላት ላይ የሚገኝ ድል ምንም የለም። አብሶ ይህን ቆርጠን ከምንቀጥለው የወያኔ ተለጣፊ የምንለውን ስያሜ ነገር በእጅጉ ልንቆጠብበት ይገባል። የተያዘ የተረዘዘውን ሁሉ እንዲህ እያደረግን ለምለምን ማደረቅ ምን ሊባል እንደሚችል ሂዱበት ….

 

ይከወን። ግን እኛ የእውነት ወያኔ እንዲወድቅ እንፈልጋለን? የትም ሳንሄድ ወደ ጎረቤትም እስኪ እራሳችን እንፈትሸው? ምኑ ይሆን የሚያስደስተን? ምኑ ይሆን የሚያስከፋን? ከቶ የት ላይ ይሆን የፍላጎታችን ሴል ያለው? ለነበረን ጊዜ ከልብ አመሰግናለሁ – የኔዎቹ – ክብረቶቼ ቸር ሰንብቱልኝ።

 

ፍላጎቴን ሳውቅ ቀን እኔ በእኔ ውሰጥ አለመሽሎኩን አረጋግጣለሁ።

ፈተናን ከመፈጠሩ በፊት አሸንፎ የተፈጠረ ኢትዮጵያዊነት።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

3 Comments

  1. ልጅት ደህና ብለሻል።. እባክሽን ጽሁፍሽ ያለልክ እየደቀቀ ላረጀ ሰው አይነበብም።PDF የሚባል ፊደል ያወፍራል ይባላል።ሞክሪው፡፡በራስሽ ፣በማንነትሽ፣ለመቆምና እውነትን ለመመስከር በመታጠቅሽ ማለፊያ ነው።አልፎ አልፎ አማሪኛው መሐል ውር ውር የሚሉ የፈረጅ ቃላትን ጨከን ብለሽ አሶግጂ። ጽሁፍሽ ጠቅለል ባሉ ጉዳዮች ላይ ያትኩር።የዳያስፕራው ኩታር ሁሌም ያስካካል።እንቁላል አይጥልም እንጂ።የዛሬው መሰረታዊ ችግር ፣መፍትሄም የምንሻለት፣ወያኔን ለመፈንገል ምን መደረግ አለበት?የሚለው ጥያቄ መልስ እስኪያገኝ(የኢትዮጵያ ነጻነት እስኪመለስ) ለውይይት መቅረብ አለበት።ትግሉ ሁሉ አገር ቤት ነው።በውጪ ያለው በገንዘብ በሞራል በሌላም ደጋቢ ብቻ ነው። “ተዳብሎ የሚኖር ፍላጎትም ሆነ ጭሰኛ ……………” አባባልሽ በተግባር ከተፈተነ ወርቅ ነው።የብዙው በተለይ በውጪ አገር የሰፈረው ወገን ችግር ደግሞ ተቃራኒው ነው።ዛፍ ያጣ ጉሬዛ፣ፈንጋይ ያጣ ባሪያ ሆኗል።ማንነቱን ተሰልቧል።አንዱ ያነሳውን ሆያ ሆዬ ሌላው ሳያጣጥም፣በሕሊናው ሳያባዝተው ይደግመዋል።የመንጋ ፖለቲካ እርስ በርስ መካለብ ነው።እራስን ፈልጎ ማግኘት አልቻለም። በዚሁ ላብቃ በርቺ።በሌላ ጽሁፍሽ ቸር ይግጠመን።

  2. ስርጉተ ማንም ተደብቆ በሚተኩስ የሳይበር* ጀግና ጀግና የሚለውን በቅንፍ ያዥልኝ ጥይት ማባከን ካልሆነ በቀር ብዙ የሚያተክነን አይመስለኝም የወያኔ ካድሬዎችና ደጋፊዎች እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጡ እንዴ ጀግና እንዳንቺ ወጣ ብሎ ያለውን ይወረውራል ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም ተደብቆ ለሚወረውር ቡኬ ዘረጥራጣ ሁሉ መልስ ከሰጠን መሸ በከንቱ ሆነን ቀረን በተረፈ በሩስያ ልብ ወለድ የትርጉም መጽሃፍት ድባብ ከሽነሽ ለምታቀርቢው ጽሁፎች አድናቆቴን ልገልጽልሽ እወዳለሁ።

  3. Because of inundated attacking on my Face Book some one and half years ago I asked my compatriot, who are residing in Kenya, the same question that you asked ” Do you like the fall of EPRDF or not’?” All most all of my compatriots answer to the question is No. Their reason for it is their process of resettlement in a third country. For their illicit interest they put us in inferno by working hand-in-glove with the Gov’t of Kenya which is a staunch supporter of EPRDF/TPLF and Ethiopia Embassy in Kenya.
    Sirgut, Don’t forget that EPRDF/TPLF has produced millions of Zombies, who are working for EPRDF/TPLF regime, that has put our people in inferno, for the past two decades. They live to eat!

Comments are closed.

Share