በደርግም ይሁን ላለፉት 23 ዓመታት፤ በኛ በኢትዮጵያውያን የኣዲስ ኣመት መለዋወጫ ግዜ የኣመለካከት እና የተግባር ስራ መሻሻል ስለማናደርግ እስቲ በኣውሮፓውያን ኣዲስ ዓመት መለዋወጫ እንመኩረው ብየ ኣሰብኩኝ። ምን ነው የሌሎች መዋስ መረጥክ የሚል ኣይጠፋም። የውጭ ስልጣኔ ያልተማጸነ ኣልነበረም መጥፎውን እየተውን። ኣሁንማ በውጭ ያለነው በሚልየን ስለሆን ኣንድ ሊያደርገንም ይችላልና ኣይጠላም።
ስለዚህ ላለፉት 23 ዓመታት ወያኔ/ኢህኣዴግ እና ተባባሪያቸው እንደደላቸው፤ ሌላው ወገን ደግሞ ሲሰቃይ እንዳለ ግልጽ ነው። የሃይማኖት፣ የስርዓት፣ የባህል፣ ኣትንኹኝ ባይነት የነበረች ሃገር፤ ለወያኔ/ኢህኣዴግ መስገድ ኣልያም ቤት ኣልባ እንደመሆን ተደርሶ መሬት ላራሹ እንዳልተባለ መሬት ለባእዳን እንዲሰጥ ህዝብ መሬት ኣልባ ሁነዋል። ፍጥጫው በወያኔ/ኢህኣዴግ እና በተቃዋሚ ደጋፊዎች ተፋጥቶ፣ የመለያየት እንጂ የመደማመጥ ባህል ጠፋ። ኣውሮፓውያን እየተደማመጡ ኣንድ ሁነው በሰላም ይኖራሉ። ኣክራሪነትና ጠባብነት መለያችን ኣድርገን ክርቢትና እሳት ሁኖ እየተቀጣጠለ የባሰ ኣስከፊ ክስተት የምናይበት ሁነታ እየገባን ነው። ቂም በቅል እንጂ ሰው መሆናችን ኣልታነጸም።
ኣሁን ችግሮቻችን ተገዝበን እንዴት ወደ ኣብሮ የመስራት ባህል እንሸጋገር ነው ጥያቄው???
ግልጽ እንሁንና የሚሰማንን ኣውጥተን፣ የሚያዳምጥ ልቦናም ሰጥቶ፣ ይቅር ይቅር ተባብለን ወደ ተሻለ ደረጃ መሸጋገር ኣለብን። ካልሆን እንዳለፉት 44 ኣመታት መጠላለፍ፣ መገዳደል፣ መበታተን እና ፍዳችን ማየት ነው። ሰለዚህ፤
፩ ኦሮሞዎች ኣጼ ሚነሊክ በድለውናል ይላሉ፣ ትክክል ነው እንቀበለው።
፪ ትግሬዎች ኣጼ ሚነሊክ ኣደሀዩን ይላሉ፤ ትክክል ነው እንቀበለው።
፫ ኤሬትርያኖች ኣጼ ሚነሊክ ለጣልያን ሸጡን ይላሉ፣ ትክክል ነው እንቀበለው።
፬ በኣጼ ሚነሊክ መሪነት ኢትዮጵያውያን ኣንድ ሁነው ወደ ዓድዋ ዘምተው፣ የሰለጠነውና ሃያሉን ጣልያን
ኣሸንፈዋል፤ ትክክል ነው እንቀበለው። እምየ ለሚሉዋቸውም መብታቸው ነው። የተበደለው ዓማራ ትተን።
፭ ዘውዳዊው መንግስት እና ባልደሮቦቻቸው (ከኣማራ፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከሃድያ፣ ወዘተ) ሲደላቸው ሌላው
ተበድለዋል፣ ትክክል ነው እንቀበለው።
፮ በደርግ የምንለያይ ኣይመስለኝም።
፯ መኢሶን እና ኢህኣፓ ከኣመራር ኣለመስማማት ተጨራረሱ ትክክል፣ ፍርዱ በምስክርነት በፍርድ ቤት ይፈጸማል።
፰ የርስ በርስ ኣለመስማማት ወደ ጦርነት ገብተው መጨረሻው ህወሓት ኣሸንፎ ኣዲስ ኣበባ ገባ። ወያኔ ስልጣን
ኣላካፈልም ብሎ ሌላውን እያባረረ፣ እያሰረ፣ እየገደለ፣ ንግድ እያካሄደ ሙሱና ነግሶ፣ የሌላውን መብት በኔ መስፈርት
ካልሆነ ወየላቹህ ብሎ፣ ሃገሪትዋ የሶማሌ እጣ ሊደርስባት ወደሚችል መንገድ እየመራት ነው።
የፈረንጆች 2015:
ብርቅየው ኒልሰን ማንዴላ ለበዳዮቹን ይቅር ብሎ በህግ እንዲጠየቁ እንዳደረገ ሁሉ፤ እኛም ሌላውን ኣልተበደልክም ከማለት፣ ሰምተን በጥናት ቀርቦ እንድንማርበት እንቀበለው። የብሄሮችና የብሄረሰቦች መብትና ኣደገጃጀት የደረሰበት ተገንዝበን፣ ባንዲት ኢትዮጵያ ስር እንዴት እንደሚተዳደር ረጋ ብለን ማገናዘብ ኣለብን። ለስልጣን የሚደረገው ሩጫ ተስፋ የለውም። ኣብረን ሁላችን ህገ መንግስት ማጽደቅ ነው ያለብን። ከዛ ነጻ ማህበራት ማደራጀትና ነጻ ምርጫ ማካሄድ። ውጤቱን ያለ ምንም መቀባጠር መቀበል፣ ለተግባራዊነቱ በትጋት መስራት። የዘርና የክልል የፖለቲካ መደራጀት የትም ኣያደርስም፣ የማይፈታ ህልም ነው። ስለዚህ ያመለካከት ለውጥ ከራሳችን ይጀምር። ሌላውን እናክብር። ኣብረን እንስራ። ሃገርና ህዝብ በህግ የመላይነት ይተዳደሩ። የፈረንጆች ዓዲስ ዓመት ለሁላችሁም መልካምን እመኝላቹሃለሁ። ወገኖቼ ያባረሩኝ ፈረኝጆች ተቀብለው በሰላም ኣኑረውኛልና እግዝኣብሔር ይባርካቸው። እነሱን የደረሰቡት ማልካሙን ያድለን።
ገብረየሱስ!