ጦርነቱ የአሜሪካንና የአውሮፓውያን ነው ! ጦርነቱ ራሺያን ለማውደም የታለመና ይህንን ዕቅድ ለማክሸፍ የሚካሄድ ጦርነት ነው!
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) መጋቢት 15፣ 2022 መግቢያ የቀዝቃዛው ጦርነት ካከተመ፣ እስከ 1989 ዓ.ም በሁለቱ ኃያላን መንግስታት መሀከል የነበረው ፉክክርና ፍጥጫ ካበቃና፣ የሶቪየት ህብረት ፈራርሳ ራሺያ ሌሎችን በሶቪየት ህብረት ስር የተጠቃለሉትን አገራት እንደ ፈለጋችሁ ሁኑ ብላ ካሰናበተቻቸው በኋላና፣