መስከረም፥፪፡ሺህ፡፲፬ ሎንዶን ከሰምና ወርቅ ክፍል ፩ `ኣዲስ~አበባ`፡ከተማን፡ለቅቄ፡የወጣሁት፥የ፡`ቀይ~ሽብሩ`፡እሳት፡እየተንቦገቦገ፤ ንፁሃን፡ እና፡ፍትሕ፡ ፈላጊዎች፤ በእየ፡ ስፍራው፥ ከአለ፡ ፍርድ፡ በሚፈጁበት፣ አስከፊ፥የምድር፡ ሲዖል፡ወቅት፡ ነበር። ወደ፡ ኋላዬ፡ ዘወር፡ ብዬ፡ የአለፈውን፣ ጥዬው፡ የወጣሁትን፡ ገሃነም፤ ለመገላመጥ፡ እንኳን፡ የሚያስችል፥የሰከነ፡ልቡና፡ አልነበረኝም። የዘመናት፡ሥቃይዋን፡ ምድር፥