ሴት የሁላችንም እናት በመሆኗ ሠላምን እና ዳቦን አጥብቃ ትሻለች – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ 

በመጀመሪያ  ፈጣሪ አዳምን ፈጠረ ። ቀጠለና ሔዋንን ፈጠረ ። አዳምም ሔዋንን ሴት አላት ። ከእርሱ ቅንጣት አጥንት ተወስዳ ተፈጥራለችና !ሴት የቀጣዩ ትውልድ እናት መሆኗንን ልብ በል ። አዳም ግን ሌላ ሥም አልነበረውም ። ሌላ ቅፅል ሥም የለውም ።

አዳምና ሄዋን ከገነት በጥፋታቸው ምክንያት ፣ ተባረው በምድር ላይ ጥረውና ግረው   እንዲኖሩ ፈጣሪ ብይን ሢሰጥ ፣ በሴት አማካኝነት ምድርን እንደሚሟሏት አሥቀድሞ ሥለሚያውቅ ነው   ። ይኽ ማለትም ፈጣሪ ሰውን የሚፈጥርበትን ኢንዱስትሪ በሴት አካል ውሥጥ በመፍጠር አዳምና ሔዋን እንዲበዙ ጥርጊያ መንገዱን አመቻምቾ ነበር ማለት ነው ።

እናም በአዳምና ሄዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ አቤልና ቃዬን ተወለዱ ። ከአቤልና ቃዬን በኋላ የተፈጠሩ ብዙ ልጆች ናቸው ።ዛሬ እነሱ አድገው ነው ፣ እርስ በእርስ ተጋብተው ና ተዋልደው ምድርን የሞሏት ። ሴትና ወንድ የምትወልደው ሴት ናት ። …

ሴት የዚች ዓለም ሰው ሁሉ ፈጣሪ ናት ።  ሴትን ፈጣሪያችን ባይፈጥር ኖሮ ፣ ማንኛችንም ወደዚች ምድር ለመምጣት አንችልም ነበር ።

ሴት ይኽንን ያህል ከፍታ ካላት ፣ በዓለም ላይ ለምን ተገቢውን ክብር አልተሰጣትም ። ለምን እሥከ  1977 ዓ/ም  ድረስ የተባበሩት መንግሥታት የሴትን እኩልነት ና መብት ለማክበር ጊዜ ወሰደበት  ? የማርች 8 የሴቶችን ትግል ማሰቢያ ቀን እንዲሆን የወሰነው በዚህ ዓመት ነው  ።

ሴቶች እኮ በአሜሪካ በ1909 እኤአ ከፍተኛ የእኩልነት ትግል አድርገዋል ።ከአሜሪካ ሴቶች ተሞክሮ ተነስተው በጀርመን ሶሻሊሥት እንቅሥቃሴ ውሥጥም 1910 ዓ/ም እኤአ  ሴቶች ጉልህ የትግል ተሳትፎ አድርገዋል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የብልጽግና  ወንጌል  አና  የሉትራን  አብዮት  በኢትዮጵያ

አብዛኛው የሴቶች ትግል ፣ እኩል የሥራና የትምህርት ምህዳሩ ለሴቶች የጠበበ መሆንን ና  የጉልበት ሥራ በረከሰ ዋጋ መሥራታቸውን ፤  የቤት ውሥጥ ጭቆናን ፣ ባርነትን ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ ውሥንነትን  ፤ የመሪነት ተሳትፎ መጥበብን አሥመልክቶ የተደረገ ና ዛሬም እየተደረገ ያለ ነው ።

በሩሲያ በማርች 8 /2017 ዓ/ም በፔትሮግራድ ታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር ። ይኽ ሠላማዊ ሰልፍ የአንደኛው የዓለም ጦርነትን ተከትሎ በተከሰተው ርሃብ የተነሳ የተከናወነ ነው ። በሰልፉ ላይ የያዙት መፈክርም ” ሠላምና ዳቦ  ! ” የሚል ነበር ።

ሴቶች በጦርነት ሰበብ በሚከሰተው ምሥቅልቅል  ግንባር ቀደም ተጎጂ እንደሆኑ ይታወቃል ። ቤተሰቦቻቸውን ፣__ ልጆች ና አዛውንት አባትና እናቶቻቸውን ፤ ወዘተ ። ለመመገብ እንዴት እንደሚቸገሩ  በሚገባ ያውቁታልና ሰላማዊ ሠልፍ መውጣታቸው አያሥገርምም ።

ተመልከቱ ፈጣሪ ያሳያችሁ ፣ የጦርነት ጥንቡሳስ ፣ ዛሬም  ዓለምን እየለበለባት ነው ። በእኛ አገር ጦርነቱ ያሥከተለውን የሰው እልቂት ፣ በአማራና በአፋር ያፈናቀለውን እና ያወደመውን ሀብት ና ንብረት መለሥ ብሎ መቃኘትም ፣ ከቀጣይ የሞኝ ጦርነት ና ከእናት ጭንቀት እንደሚታደግ እወቁ ።…

በአንክሮ ከመመልከት ተሻግራችሁም ፣ በዩክሬን ኮመዲያኑ ዘሌኒስኪ ያለአዋቂነቱ ያሥከተለውን ጥፋት ብተገነዘቡም  መልካም ነው ። ዜሌኒሥኪ   ሩሲያን ለማጥፋት ከአሜሪካ ጋር መሻረክ አልነበረበትም ። ሩሲያ ጎረቤቷ ከአሜሪካ ጋር ተሻርኮ ሊያጠፋት በማቀዱ የተነሳ ፣ ደጋግማ ይቅርብህ እረፍ ብላለች ። ኮመዲያኑ ና የፊልም አክተሩ ዜሌንስኪ  ግን የገሃዱ ዓለም እውነት ፊልም መሥሎት ከኃያላኗ ሩሲያ ጋር ተጋጭቷል ። በዚህም ጥፋቱ ዩክሬንን አፈራርሷል ። ከ3 ሚ በላይ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል ። ሩሲያ ግን የዩክሬንን ከፍተኛ ኃይል ማመንጫ የኒኩለር ጣቢያዎችን በመያዝ   ድሏን አረጋግጣለች ። እናም ” እረፉ ! ከእኔ ጋር መጋጨት ፣ በእሳት መጫወት ነው ። ” በማለት ደጋግማ እያሥጠነቀቀች ነው ። ይኽንን መሥጠንቀቂያዋንም ሲአይ ኤ በቅጡ በመገንዘብ ” በይደን ሆይ ይቅርብህ ! ” በማለት ምክሩን ለግሷል ።  ማንም ኃያል መንግሥት ከዜሌንሥኪ ጋር እንደማይቆም ቀድሞም  የታወቀ ነበር ። ምክንያቱም ባለፈው ፅሑፌ እንደጠቆምኩት ሦሥተኛ የዓለም ጦርነት ብሎ ነገር እንደማይኖር ኒኩለር የታጠቁ ሁሉ  የተገነዘቡ ይመሥለኛል ። የፈረንሣይን ከሩሲያ ጋር መቆም ተመልከት ። በእሳት ላለመጫወት የሩሲያን የአደጋ ሥጋት ተገንዝበው ሌሎችም የእሷን ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነው ። ደግሞም አሜሪካ ሥንትና ሥንት ኪሎሜትር አቋርጣ በየሰው አገር ጣልቃ የምትገባው ፣ ለዜጎቼ ህልውና ያሰጋኛል ። አሸባሪነትን ከጥንስሱ ቦታ ሄጄ በመዋጋት ማጥፋት አለብኝ በማለት እንደሆን አንዘንጋ ። የሩሲያ ሥጋትም ከአሜሪካ ያላነሰ እንደውም የላቀ መሆኑ መታወቅ አለበት ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊያን ቅድሚያ ለሀገር ሉአላዊነት መስጠት ግዴታቸው ነው -  ሲና ዘ ሙሴ

የእኛ አገር በሥጋ ና በውሥኪ የሚቃዡት 1%  ፖለቲከኞቻችንም ከዚህ እውነት አንፃር ፣ ቅጥረኝነታቸውን ለማቆም የሚያሥችላቸውን እውነተኛ  ልብ ቢገዙ መልካም ነው ። በፍቅር የተሞላ ልብ የኢትዮጵያ እናቶች ዘንድ አለ ። ከእነሱ ሃዘን እና ዋይታ በፀፀት የሚሸምቱትን ነፁህ ልብ ያገኛሉ ። ይኽንን ንፁህ ልብ አልሸምትም ካሉ ግን ” እነዚህ ለማይጠረቃ ሆዳቸው  ብለው ጎሣን እና ቋንቋን የሙጥኝ ያሉ  ፖለቲከኞች ሥለፖለቲካ ጥልቅ እውቀት የላቸውም  ። ልክ እንደ ፊልም አክተሩ ዘለንስኪ የገሃዱ ዓለም የህዝብ ሰቆቃ ። የሴት አህቶቻችን ፣ ልጆቻችን እና እናቶቻችን ለቅሶ ተከታታይ ፊልም እንጂ እውነት አይመሥላቸውም ። ” ብለን ለመደምደም እንገደዳለን ። የሴቶችን ቀን ያከበሩትም ትርጉሙ ሳይገባቸው ፣ እልም ባለ ድንቁርና ነውና  ሊያፍሩ ይገባቸዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share