ለእኛ የሚበጀዉ “ኢትዮጵያን ለቀቅ ጠላቶቿን ጠበቅ” ነዉ፡፡

የኢትዮጵያን ህዝብ እጂ ከወርች አስሮ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሀ..ሁ..  የጥላቻ እና ኢትዮጵያዉያንን የማግለል እርምጃ እና ዘመቻ የተጀመረዉ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማዳከም ዋዜማ ጊዜ አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት መሆኑን ከማንም በፊት ኢትዮጵያዉያን አብክረዉ ያዉቃሉ፡፡

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያዊነት ላይ የተጀመረዉ አፍራሽ ተልዕኮ በተለይም ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የዓማራ ህዝብ በሁለንተናዊ ነገሩ ማዳከም ከዚያ አስካሁን የሚታየዉ ሴራ ዋነኛ ማሳያ ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ ቢደራጂ እና ቢታጠቅ ኖሮ ዛሬ ኢትዮጵያ ከየትኛዉም ጊዜ በላይ ለደረሰባት ሁለንተናዊ ቀዉስ ባልበቃች ነበር ፡፡

ሆኖም ሁሉም በሚባል ሁኔታ የዓማራ ህዝብ እንዳይደራጂ እና ራሱን እና አገሩን እንዳይከላከል በተፈጥሮ ያገኘዉን ህልዉናዉን እና ነፃነቱን እንዳያስጠብቅ  በሁሉም ነገር እንዲራቆት እና እጂ አግሩን አጣምሮ ሙት ሲባል እንዲሞት አሜን ብሎ እንዲቀበል እንዲሁም በአገሩ ስደት እና ዉርደት እንዲያስተናግድ የ፴(ሠላሳ) ዓመቱን  ግፍ እና መከራ ዛሬም እንዲያስተናግድ ይፈለጋል፡፡

የሚያሳዝነዉ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያስፈልጋቸዉን ሁለንተናዊ ቁስ ( ትጥቅ እና ስንቅ) ከኢትዮጵያ ህዝብ እያገኙ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ለህዝቦች ህልዉና እና ደህንነት በባዶ እጁ ከአፍራሽ ኃይሎች ጋር ተናንቆ የህይወት ቤዛ ከፍሎ ያገኘዉን የነፍስ ወከፍ ሆነ የቡድን መሳሪያ ይገባኛል የሚል መኖሩ ለምንሰማ ኢትዮጵያ ከጠላተቿ ጋር የምትኖር “በሬ ካራጁ ”መሆኗ ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ ሆነ የዓማራ ዝዝባዊ ኃይል ባለመደራጀቱ እና ባለመታጠቁ የደረሰበትን የዘመናት አቻ የለሽ ሰቆቃ በቃ ለማለት ድምፁን ያሰማዉ ዛሬ ሳይሆን ገና በአስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ መጀመሪያወች መሆኑ እየታወቀ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን በደም እና አጥንት  ዋጋ የህይወት መስዋዕትነት መክፈሉ አመድ አፋሽ ማድረጉ ሳያንስ ዛሬም  እጂ እና ዕግሩን አጣምሮ ለሞት እና ባርነት እንዲኖር  መደራጀት እና መታጠቅ የለበትም የሚል ቢኖር እርሱ ኢትዮጵያዊነት ቀርቶ ሰባዊነት ያልፈጠረበት መናኛ ፍጡር ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዐቢይ አሕመድ አሊ ለሥልጣን የበቃው በምርጫ ነው ወይ በቅርጫ (ኘሮፌሰር ኀይሌ ላሬ)

የዓማራን ህዝብ መደራጀት እና መታጠቅ የሚቃወቀም ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚለይበት ንግግር ካልሆነ በተግባር የሚለየዉ ምንም የለም ፡፡

የዓማራ ህዝብ በመደራጀት ራሱን እና አገሩን ከማንኛዉም ጥቃት የመጠበቅ ተፈጥሯዊ እና ሉዓላዊ መብት ከማንም የሚሰጥ ሳይሆን በተፈጥሮ ሠዉ  እና ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ያገኘዉ አንጡራ መብት እና ግዴታ ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ መደራጀት እና ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት እና ዕድገት መሰረት እና አብነት እንደመሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚረዳዉ እና የሚቀበለዉ ዕዉነታ ነዉ ፡፡

የየትኛዉም አገር ህዝብ ከራሱ በላይ ማንም በችግር ጊዜ ሊደርስለት እንደማይችል ዓለም የሚመስክረዉ ቢሆንም በእኛም አገር ትናንት በኢጣሊያ ፤ዛሬ በቅጥረኛ የዉስጥ እና የዉጭ ጠላቶች የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ ወረራ እና ክህደት ሲደርስበት  ራሱን ከጥቃት የታደገዉ ራሱ ህዝቡ እናየህዝብ ልጆች መሆናቸዉን ከማየት በላይ አስረጂ ፤ነጋሪ አይሻም፡፡

ኢትዮጵያዉያንን የርኩስ መዉጊያ ማድረግ በቃ ሊባል ይገባል ፡፡ ህዝብ የህይወት እና የደም ዋጋ የከፈለዉ ህልዉናዉን ለማስከበር እና ዳግም ለጠላት ለመገበር እና የየትኛዉንም አካል ስልጣን ዘመን ለማራዘም እና ለማስቀጠል አልነበረም ፡፡

ለሁላችንም “በክፉ ቀን የደረሰ ክፉ ቀን ይምስላል እንዲሉ  ” ኢትዮጵያዉያንን እና የኢትዮጵያ ወዳጆቿን ማቀፍ እና መደገፍ እንጂ  ጊዜ እያዩ መደነቃቀፍ በቃ ሊባል ይገባል፡፡

እንደ አገር የምናስብ ከሆነ  የኢትዮጵያዉያንን ህይወት እና ንብረት የነጠቁትን እና እየነጠቁ ያሉትን ጠላቶች የህዝብ እና አገር ሀብት እንዲመልሱ መስራት እና ጠበቅ ማድረግ እንጂ የምቀኝነት እና የበታችነት ንትርክ ለማንም አይበጂም እና ኢትዮጵያዉያንን ለቀቅ ፤ጠላተቿን ጠበቅ  ማድረግ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወልቃይት ፣ ጠለምት እና ራያ ህወሃት በከለለው ግዛት ስር ይሁን ፣ (Status- Quo -Ante) ይከበር የሚለው ቅዥት እና ተረት ተረት።

መዘናጋትም ሆነ ማዛጋት ዋጋ  እንደ ሚያስከፍል አንድ የድሮ እና የዘንድሮ  አበባል ልጥቀስ ፡፡ የድሮዉ  ድሮ የወሎ ግዛት ሰፊ እንደነበር እና የተወሰነዉን እንዳጣ በአፈ ታሪክ እንሰማለን ፡፡ ይኸዉም“  ቡና ሲል ወሎ ርስቱን ተቀማ”  ሲሆን ዘንድሮ “ ብልፅግናን ሲል በመዘናጋት“ የደረሰበትን ዓለም የሚያዉቀዉ ፤ፀሃይ የሞቀዉ  ሀቅ ነዉ ፡፡ እናም አገር እና ህዝብ የሚጠበቀዉ በህዝብ አንድነት እና መደራጀት እንጂ በሌላ በማንም በምን አይደለም እና መዘናጋት እና እያዩ ሞት በቃ ፡፡

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ” ፤

“ኢትዮጵያዊነት ንግግር ሳይሆን መኖር ነዉ  ፡፡ ”

————————-

ንጉሥ ሆይ ፋኖን ማሣደድ ያቁሙ ዕዳው ለርሥዎ ነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share