ማይክሮሶፍት በኢትዮጵያ ያለውን የትምህርት ስርዓት ለማዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10 ፣ 2014 – ማይክሮሶፍት ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የትምህርት ሴክተሩን ስኬታማ ዲጂታል ሽግግር የሚደግፍ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር የመረጃ ስርዓትን ተግባራዊ አደረገ። የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ዘርፉ ያለውን ደረጃ አቅም በማሳደግ ውጤታማ፣ጥራት ያለው እና እኩል የትምህርትና ስልጠና ስርዓቶችን ተግባራዊነት የማረጋገጥ ተልዕኮ እንዳለው ይታወቃል። በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ስኬታማነት ለማረጋገጥ በዋናነት ግብአት የሆነውን