March 9, 2022
9 mins read

“ጊዜና ትውልድ ገና የሚያከብረው ኢትዮጵያዊ” ገዱ አንዳርጋቸው!!

ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ ( ለንደን)

የለውጥ ጉዟችንን ማዳን እንጅ ማዳከም አያስፈልግም !!

Geduየሰው ልጅ ቢኖርም ባይኖርም በምድር ላይ አድ ግዜም ቢሆን ታሪክ ሰርቶ የራሱን እውነት ቋጥሮ ነፃ ህሌና ይዞ ለዘላለም በታሪክ ፊት ሳይሸማቀቅ ይኖራል ::

ብቻ የትም ይሁን መቼ ታሪክ ከመቃብር በላይ ነውና አፈር ሳይለብስ እንደዚህ ፀሐይ በጥዋት እንደ ጨረቃ በለሊት ደምቆ ይታያል: :

ታሪክ ይዋል ይደር እንጅ ድፍርሱ ንጋት ሲጠራ ለዛሬው ህይዉታችን ለነገው ፈራሽ ስጋችን ምስክርኑቱን ሰጥቶ እውነት ቦታዋን ትይዛለች: :

ለዛሬው ብዕሬን ያስጨበጠኝ የእንደመሩ አብዮት ማሀንዲስ የለውጡ የጀርባ አጥንት ሆነው በሁለት ጎራ የተከፈለውን የወያኔ ኢሀድግ የፓለቲካ ድርጅት አንገዳግደው ከጣሉት የመጀመሪያው ደፋር የእንደመር አብዮተኞች አንዱ” የአማራው ጄኔራ” በመባል በቅፅል ስም የሚጠሩት ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው: :

አሁንም አቋማቸውን ግልፅ አድርገው እንዲህ አሉ: :

*** ” “በቀረችኝ የህይወት ዘመኔ ህዝቤን ለዳግም ባርነት አልዳርግም! ፋኖ ትጥቅ ይፍታ የሚለውን የብልፅግናን አካሄድ አጥብቄ እቃወማለሁ ” *** ::

ወደድንም ጠላንም ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በዲሞክራሲው ግንባታም የራሳቸው አሻራ ያስቀመጡ ጠንካራ ፓለቲከኛም ቢሆኑም የለውጡን የጠ/ሚኒስትር አብይን ቡድን ደምና ስጋ ለብሶ ቆሞ እንዲሔድ ካደረጉት የለውጡ አውራዎችም ትልቁን ድርሻ በባለቤትነት ይዘዋል : :

ከአርባ አመት በላይ ከአገር ውጭ የነበሩት ጨምሮ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች. ወደ ሐገራቸው ተመልሰው ለሰላምና ለኢትዮጵያ አንድነት ለዲሞክራሲና ለልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ ሆደ ሰፊው ገዱ አንዳርጋቸው የዶክተር አብይን የእንደመር አብዮት ተቀብለው

” የኦሮሞ ደም የአማራ ደም ነው ” በማለት ለ27 አመት በተጠናከረ የአፈናና የግድያ ጥፍር ነቃይ ስርአት የወደቀች ሐገራቸውን በህይወት ተወራርደው ጣና ኬኛ ብሎ የመጣውን የቲም ለማን ትውልድ በሰከነ አመራር ተቀብሎ. የወያኔን ስነ ልቦናዊ ጦርነትና የነበረከት ስምኦንን አሻጥር ተቋቁመው ቲም ለማን ፓርማ ውስጥ ያነገሱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው : :

275489515 4967692483338491 3633769968169063573 n

ከዚህ ባለፈም ገዱ ጠንካራ አቋምና የኢትዮጵያን አንድነት የሚመርጡ የገዘፈ ሰብእና ያላቸው ፓለቲከኛ እንደመሆናቸው ሁሉ በአያት በቅድመ አያትቶቻችን ደምና አጥንት የተገነባችውን ሐገር በጥቂት የጎሳ መንደርተኛ ፖለቲከኞች፣ ተሸራርፋ የተገጣጠመች አድርገው የሚቃርቡትን የዘመናችን ጅላጅል ቂሎ ሞሮዎችን አጥብቀው የሚተቹ የአማራን ሕዝብ አለኝታ “ፋኖን ” ትጥቅ ለማስፈታትና አማራን. በማሸማቀቅ አንገቱን ሊያስደፉት የሚያሴሩት ዘረኞች ጋር. ትንቅንቅ በመግጠማቸው ቅልብተኞቹ የዩቲፕ አመንዝራዎች በተለመደው የሶሻል ሚዲያ ጫጫታ ከፍተውባቸዋል : :

በእርግጥም ገዱ አንዳርጋቸው እንደሚሉት . ኢትዮጵያ፣እንደ ሐገር ለመፍጠር በሽሕ የሚቆጠሩ ዘመናት ጠይቀዋል: :

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦችም ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰውባታል: :

ኢትዮጵያዊያኖች ፣ የቋንቋን ድንበር ግድብ ዘልቀው የትውልድን ዋስትና አሻግረው አይተው አባቶቻችችን የመሰረቱልንን የጋራ ሀገር ለማቆየት አሁንም የገዱን መርህ ተከትሎ የአማራ ሕዝብ ከጎናቸው መቆምና ለገዱ አንዳርጋቸው መመከት ይገባዋል ::

ገዱ በተለያዬ ጊዜ ባቀረቧቸው ጠንካራ ሀሳቦች ውስጥ የአንድ ሐገር ልጆች እኩል እንክብካቤ እኩል ጥበቃ እኩል የጥቅም ተካፋይ.መሆን እንደሚኖርባቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ በመደመጤቸው በዘረኞች ጩልሌዎች እንዳይጠለፉ የአማራ አይኑን መግለጥ አለበት : : ኢትዮጵያውያኖች የዜግነታቸው መብት እኩል ሳይጠበቅና ፍትህና ርዕት ሳያገኙ. ሐገር የጋራ መሆኑ ቀርቶ የጥቂት ተረኞችና አምባ፣ ገነኖች፣ መሆኑ ማብቃት አለበት በለው. በፅኑ የሚያምኑ. ብርቱ ፓለቲከኛ በመሆናቸው ሰሞኑን. ቅጥረኛ ሸኔዎች በእሰጥ አገባ ተጠምደዋል ::

በእርግጥ ዜጎች እንደዜግነታቸው ተከብረው እንደሰው ኑረው እንደሰው በክብር ለማለፍ የሚችሉበት ሐገር ሳንዘናጋ ጠንክረን መስረቱን መጣል ያስፈልገናል. የሚሉት በሳሉ ትእግስተኛው ፣አርቆ አሳቢና፣ አስተዋዩ ፣ፓለቲከኛ ፣ገዱ አንዳርጋቸው :: የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሉአላዊነት አላስነካም በሚል ፅኑ አቋማቸው በተለያዩ የኢትዮጵያ

ጠላቶች ስውር ሴራ እየተቀነባበረባቸው መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአየነ ቁራኛ እየተከታተለው ይገኛል ::

ሆኖም ግን እውነት አትሞትም የሚሉት ገዱ አንዳርጋቸው ለመሰሉ፣ኩሩ ኢትዮጵያዊን ይህ ጌዜ ከባድ ቢሆንም

በህዝብ መከበርና መወደድ መታቀፍና የህዝቡን ስነ ልቦና መግዛት መቻልን ይጠይቃል: : የዘረኛ ስርአት የእድገቱ ምልክቶች አንዱ ቢሆንም በደመቀ መኮነንና በገዱ አንዳርጋቸው ላይ. አማራን የማግለል ጥላቻ. ተጀምሯል :: በዚህ ምክኒያት በሐገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ከአውሮፓ እስከ ሰሜን አሜሪካ. በድጅታል ወያኔዎች አማካኝነት የስም ማጥፋት ዘመቻ ቢከፍቱባቸውም ብርቱው ፖለቲከኛ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ንቅንቅ አላሉላቸውም : :

በዚህ የሀገር ሉአላዊነት አደጋ ላይ በወደቀበት አስቸጋሪ ወቅት

ሴራው ተቀነባብሮ እውነት ከሆነ ግን የአማራን ልጅ ቀኝ እጁን ቆርጦ እንደመጣል ይቆጠራል ::

ስለሆነም ገዱ አንዳርጋቸውን በተለያዩ ፌስ ቡኮችና በዩቲዩብ ጡረተኞች አማካኝነት የአማራ ተቆርቋሪ በመምሰል የተከበረ ስማቸውን ለማጠልሸት ” ታላቁ ሴራ በድጅታል ወያኔዎችና በኦነግ ሸኔ ቅጥረኞች ዘመቻው ተጀምሯል ::

ኢትዮጵያ ከገዱ አንዳርጋቸው ገና ብዙ አገራዊ ለውጥን መጠበቋ አይቀሬ ቢሆንም የተቀነባበረባቸው ሴራ በቆራጥ ኢትዮጵያዊያኖች ተጋድሎ እንደሚከሽፍም ፍፁም ጥርጥር የለኝም ::

ሁላችንም ገዱ አንዳርጋቸው ነን ::

አበቃሁ በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን: :

አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop