January 14, 2025
9 mins read

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

fanoፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም የተለያዬ ጉዳይ የተነሣ ትግሉ አሁንም የዕንፉቅቂት እየሄደ ብዙዎቻችንንም ተስፋ እያስቆረጠ ይገኛል፤ በዋናነትም የብዙዎችን ታጋዮችና የአማራ ሕጻናትን፣ አረጋውያንን፣ ሰብልንና እንስሳትን ሳይቀር እያወደመ ለሚገኘው ጦርነት መሠረታዊ ምክንያት ከመሆን አልዘለለም፡፡ ይሄ አካሄድ ለዐይን ይበጃል ያሉት ኩል ዐይንን እያጠፋ ስለመሆኑ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ ከእንግዲህ ግን “ያበጠው ይፈንዳ የሚሰማንን ከመናገር ወደኋላ አንልም” የምንል ዜጎች ወደ መድረክ መዝለቅ ይገባናል፡፡ “እንትና እንዳይከፋ፣ እነእንትና እንዳይቀየሙ፣ እንቶኔ እንዳያኮርፍ ወዘተ.” የሚለው ሰበብ አስባብ ሀገርንና ሕዝብን እንጦርጦስ ከማውረድ አላደነም፡፡ አቢይንና የሚመራውን ዐረመኔ የዘረኞች መንጋ አንድም ሳናስቀር በስድብና በዘለፋ እየሞለጭን ሳለን ገና ለገና እገሌ የሚባለው የነጻነት ታጋይ አራት ኪሎ ሲገባ “እንዲህ ወይ እንዲያ ሊያደርገን ይችላል” በሚል ፍራቻ ይመስላል ብዙዎቻችን እየተሸፋፈንን ቆይተናል፡፡ ውጤቱ ግን ያው የምናየው ነው፡፡ “እየመጡ ነው” የሚለው መፈክርም የተነገረበት ቅላጼና የተጻፈበት ቀለም መደብዘዝ ከጀመሩ ቆዬ፡፡ “እየተፈራራን እንጂ…” – አለ ኃይሌ – “ፋኖን ብንተች ቀዳሚው ተጠቃሚ ራሱ ነው” ብዬ ጨመርኩ እኔ፡፡

ለገባንበት ፋኖኣዊ የአደረጃጀትና የአካሄድ ችግር አንድ ልጨኛ ሥነ ቃላዊ ብሂል ባስታውስ ደስ ይለኛል፡፡ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፡፡ ምናልባት ወጣቶችን ማስታወስ ካስፈለገ ነው የምደግመው፡፡

አንድ ሠነፍ እረኛ በአንድ መንደር ውስጥ በጎቹን አሰማርቶ እየጠበቀ ሣለ “በጎቼን ቀበሮ በላብኝ፤ ቶሎ ድረሱልኝ” ብሎ ወደ መንደሩ ሰዎች ጮኸ፡፡ ትንሹም ትልቁም ዝርግፍ ብሎ መጣ፡፡ ግን ውሸቱን ነበር፡፡ ከዚያም በሰዎቹ “ሞኝነት” ከትከት ብሎ ሣቀባቸው፡፡ በሁለተኛውም ቀን ልክ እንደቀደመው ቀን በጎቹን ቀበሮ በላብኝ ብሎ ጮኸ፡፡ ባለፈው ከመጡትም እንደአዲስ ከሰሙትም የተወሰኑት ደረሱለት፡፡ ግን ውሸቱን ነበርና አሁንም በሰዎቹ “ሞኝነት” መሬት ላይ ወድቆ እየተንፈራፈረ በሣቅ አላገጠባቸው፡፡ በሦስተኛውም ቀን ደገመው፡፡ አሁን ግን አንድም ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ግን እውነቱን ነበር፡፡ የቀበሮ መንጋ ድንገት መጥቶ በጎቹን ለቃቅሞ በላበትና ማታ ባዶውን ወደቤቱ ተመለሰ፡፡

አዎ፣ አንድ ነገር ወረቱ ሳያልቅ ሲሆን ያምራል፡፡ ፍቅርም በወረት ነው፤ ንግድም በወረት ነው፤ የሥራ ቅልጥፍናን ስኬትም በወረት ነው፡፡ ወረቱ ያለፈ ነገር ደስ አይልም፤ ስሜትን ያጎፈያል፡፡

የፋኖም ነገር ከፍ ሲል ከተጠቀሰው መራር እውነት የሚዘል አልሆነም፡፡ በጥቃቅን ሰበር ዜናዎች አእምሮን ቢያደነዝዙት ጎመን ተበልቶ ጉልበትን በዳገት እንደመፈተን ነው፡፡ አንድን የገጠር ከተማ ለተወሰኑ ሰዓታት ወርሮ የተወሰነ ጥቃት በጠላት ላይ ማድረስ በሰበር ዜናነት የሰውን ቀልብ መያዝ የሚችለው ለተወሰነ ጊዜ እንጂ ለሁለትና ሦስት ዓመታት ሊሆን አይችልም፤ ራሳችንን አናታልል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አስቡበት፡፡ በጣት በሚቆጠሩ ሰዎች አለመግባባትና የፍላጎቶች መለያየት የተነሣ ሀገርና ሕዝብ አይጥፋ፡፡ አቢይ አንድ ወር በሥልጣን በቆዬ መጠን ኢትዮጵያና ሕዝቧ የ50 እና 60 ዓመታት ጥፋት እያስተናገዱ ነው፡፡ በልማት ስም አዲስ አበባ ጠፋች፡፡ ሌሎችም እየተከተሉ ነው፡፡ የፋኖ ጥረት ደግሞ አቢይን በተሻለ አቢይ የመተካትና ሥቃይንና መከራን የማስቀጠል መሆን የለበትም፡፡ ጭንቅላት የተሠራው ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬንም ከነገ በማገናዘብ መልካም ውሳኔዎችን ለመወሰን እንጂ አንዱን የሲዖል በር ዘግቶ ሌላውን ለመክፈት አይደለምና ተሰሚነት ያላችሁ ወገኖች በበረሃ ያሉ ወንድሞቻችንን ምከሩ፡፡ አራት ኪሎ የሚይዘው የሰው ብዛት አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ያ አንድ ሰው ደግሞ ራሱን የመረጠና አቢይ አዘውትሮ እንደሚለው በእናቱ ትንቢት የሚነዳ ሳይሆን በሕዝብ ቀጥተኛ ምርጫ የሚሾም መሆን ይኖርበታል፡፡ በሕዝብ ምርጫ ሥልጣን የማይዝ ሰው የሚፈራው ነገር ስለሌለ ያሻውን እያደረገ ሥልጣን ላይ መቆየት ነው ቀዳሚ ምርጫው፡፡ አቢይ ከእርሱ የተሻሉና የበለጡ ናቸው የሚባሉትን የተማሩና የሠለጠኑ አንጋፋ ዜጎችን ሳይቀር ባልተወለደ አንጀት እየቀረጠፈ ወደመቃብርና ሻል ሲልም ወደስደት የነዳው ከርሱ በላይ ዐዋቂና ከርሱ በላይ መሪ የሌለ መሆኑን ለማረጋገጥ ሲል ነው፡፡ ለሥልጣኑ እንደሚያሰጉት የሚገምታቸውን አማራና ትግሬዎችን ከነጄኔራል አሳምነው፣ ጄኔራል ገዛኢ አበራና ዶክተር አምባቸው ጀምሮ በጥይት ሲጨፈጭፍ ኦሮሞዎች ከሆኑ ግን በአብዛኛው በድርድር ከሀገር እንዲወጡለትና በዚያው እንዲያርፉለት ሲያደርግ መቆየቱ የአደባባይ  ምሥጢር ነው፡፡

ለማንኛውም ፋኖ ለራስህ ስትል ጣፍጥ፤ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ተብሎ መጣልም አለ፡፡ ልድገመው – የሥልጣን አራራና የሀብት ጥማት ከሚያቃጥላቸው እፍኝ የማይሞሉ ባላባቶች ይልቅ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጣልና በተለይ የፋኖ አመራሮች ከዚህም በላይ ሳይረፍድባችሁ ተሰባስባችሁ አንድ ነገር ወስኑ፡፡ ጊዜው ካለፈ ትርፉ ጸጸት ነው፡፡ ሁሉም እናንተን አንጋጦ ሲጠብቅ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ያ ተስፋ እየተሸረሸረ ነውና በጥልቀት አስቡበት፡፡ የተበላሸ ዕድል “ና ተመለስ በሞቴ፣ በጊዮርጊስ ባውነተህሌ”  ቢሉት አይሆንም፡፡ ፈረንጆቹ እኮ Hit the iron when it is hot! የሚሉት ወደው አይደለም፡፡ አለቀ፡፡

 

2 Comments

  1. በእውነቱ ይህ ጽሁፍ ፋኖን የሚመክር አቅጥጫ የሚሰጥ ብሎም የሚኮንን መሰለኝ። ፋኖ ነገሮች አልጋ በአልጋ የሆኑለት አልመሰለኝም ከባህር ማዶ ከሁኔታው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ዋናው ፋኖ ነን ገንዝብ ወደኛ ላክ ይባላል እዚህ የተሰበሰበው ብር በአንድ በኩል እዚህ ተሽራርፎ እራሳቸውን ሚዲያ ብለው ለሚጠሩት መተዳደሪያ ይሆናል። እንግዲህ ሰው መተዳደሪያውን ከነኩበት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አስቸጋሪ አይሆንም ተው ሲባሉ እንደ እብድ ያደርጋቸዋል ስራ መስራት ካቆሙ ቆዩ አሁን ስሩ ሲባሉ ፍርሃት ፍርሃት ይላቸዋል።

    እነዚሁ ሰዎች የዩቲዩብ ገበያ ለመሳብ ከስር ስር እየተከታተሉ አንዴም በድሮን ሲያስፍጇቸው በሌላው በኩል ያለው ዩቱዩበኛ ደግሞ እኔን ችላ አሉ ብሎ ይወርድባቸዋል። የተዋጣውን ገንዘብም በዲያስፖራ የሚኖሩት ዘራፊዎች ለፋኖዎች ባለማድረሳቸው ፋኖዎች ችግር ላይ ናቸው ማዋከቡን መቼም የምናውቀው ነገር ነው። ስለዚህ ፋኖዎች አጥፍተው ሳይሆን ዲያስፖራ አንድም ለስልጣን አንድም ገንዘብ በነሱ ስም ለመሰብሰብ በሚያደርገው ግብ ግብ ነገሮች ተጎትተዋል። ጎበዝ እነዚህ በዲያስፖራ ገንዘብ እየሰበሰቡ መተዳደሪያቸው ያደረጉ የካበተ የሌብነት የመበጥበጥ የማምታታት ልምድ ያላቸው ናቸው ይህም ስሩ ሲፈለግ ወደ ግምቦት 7 ላይ ያደርሰናል እነዚህ ሞራል የሌላቸው ከኢትዮጵያ ጠላቶች (ግብጽ) ሳይቀር ገንዘብ ሲቀፍሉ የኖሩ ሞራል የሌላቸው ናቸው። በእርግጥ የነጻነት ቀን ሲቀርብ ብርሃኑ ነጋ፤ነአምን ዘለቀ፤ታማኝ በየነን የመሳሰሉ ዘራፊዎች በህግ ፊት እንደሚቀርቡ እምነታችን ነው።

    ባጠቃላይ ፋኖን ተውት ከሃገር ውስጥ ቱባ ቱባ የሚያህሉ አባላት አሉለት ከባህር ማዶ እነ ፕሮፌሰር ሓብታሙ፤አቻምየለህ ታምሩ፤አቶ ተክሌ የሻውን የመሳሰሉ በሳል አመራር ሊሰጡት የሚችሉ ዜጎች ስላሉለት አመራር እንስጥ ገንዘብ በስምህ ሰብስበን ቤትና መኪና እንግዛበት አትበሉት። አሁን ግምቦት 7 በተለይም ታማኝ በየነ በኢትዮጵያን ስም የሰበሰበውን ገንዘብ ኦዲተር ቢታዘዝበት ምን ከምን ያደርገዋል እንደው ዝም ነው እንጅ። ለነገሩ “የብዙ ሰው ገንዘብ ብላ የብዙ ሰው ዘመድ አትንካ” ይል የለ? ፋኖ በርቱ በራችሁን ጠርቅሙ ከኛ በላይ ላሳር ነው የምትሉ አመራሮችም ለቃችሁ ተራ አባል ሁኑ እያንዳንዳችሁን እናጠናለን እኛ ካልደገፍን የሚሆን ነገር የለም።ጌታ ከለላውን ይስጣችሁ ብርሃኑ ነጋ፤ ግርማ…ኢዜማን በለጠ ሞላን ሁናችሁ መኖር ትችሉ ነበር የሞራል ጉዳይ ሁኖባችሁ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

Go toTop