የጥፋት እሣትና ኢትዮጵያዊነት (በመኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ)
እሣት ፣ እሣት ፣ እሣት ነው ፤ ዘመኑ የሚጋረፍ ፣ የሚለበልብ ፤ ወላፈኑ የሚቀቅል ፣ የሚጠብሥ ፤ ሙቀቱ የሚያከሥል ፣ የሚያሣርር ፤ ቁጭቱ ፡፡ ……………………………………….. ጉልቻ እየተቀያየረ ከተረሳ ድስቱ አይቀርም በእሳት መጎርናቱ ፡፡ ገብስ እንኳ ፣ በወግ ካልሆነ አቆላሉ በእሳት ፣ አራሪው ይበዛል ከብሥሉ ፡፡ ………………………………… ለዚህ ነው እናቶች ገብሥ ሲቆሉ የአሻሮ እና የቆሎ ጉልቻን የሚያሥተካክሉ ፡፡ ለቆሎ ጥቂት አሸዋ ምጣዱ ላይ የሚበትኑ ገብሱን ከማረር ፣ ከአሻሮነት ሊያድኑ ፡፡ ……………………………………….. አገር ተገንዘብ ወግኛውን የእሣት ጫወታ በገዛ አገርህ ሳያደርግህ ከርታታ ና አውታታ ዛሬ እጅግ ረቋልና የእሣት ጫወታ