የኢትዮጵያ ሰማይ! –ፊልጶስ

February 21, 2022
5 mins read

ትላንት ያለንበርኩኝ፣ ነገም የማልኖር
ከቃንቄ ብርሃን፣ ከነቁጥ ያነስኩ ፍጡር
የማለዳ ጤዜ፣ ለዚች ዓለም-ምድር፤

መነሻ-መድረሻው፣ ሚስጢር ቢሆንብኝ
ልጥይቅህ ደፈርኩ ግራው ቢገባኝ።

በአርባ አራቱ ታቦት
በቅዱስ ሰማዕታት፤
በምስኪኗ እናት- በቆዘመው አባት
በወላጅ አልባዎቹ- በእነዚያ ህጻናት
በተደፈሩት፣ በተዋረዱት
በፈሰሰው ደም፣ መሰዋት በሆኑት ፤

በአንጋጠጡ ዓይኖች
በተዘረጉ እጆች፣
በአዘኑ ልቦች፤

በስደተኞቹ
በባይታወረሮቹ፤

በረሃ-ውቅያኖስ፣ በልቶ ባስቀራቸው
በምንዱባኖቹ፣ ድምጽ በሌላቸው
በሚቅበዘበዙ ቀን ጨልሞባቸው፤—

ልማጸንህና!
ልለምንህና!

የኢትዮጵያ ሰማይ!
“እህ” ብለህ ስማኝ
ልጠይቅህና፣ እስቲ መልስ ስጠኝ
እናታለም ምድሬን!—-
አገሪን! ወገኔን! ከቶ ምን ነካብኝ???–

አንተ ክላይ ያለህ፣ የኢትዮጵያ ሰማይ
ምን ትታዘባለህ አቆልቁለህ ስታይ?

አሃዱ ዓለም ተብሎ፣ ቀደምተ-ፍጥረት
ኢትዮጵያ ስትባል የገነት “አፍላጋት”
ዛሬ እንዴት ሰው ያምናል፣ ጥንት ለሚያውቃት?—–

ከላይ ሆነህ አንተ፣ ከታች ሆነን እኛ
ምን ብለህ ታዘብክ ፣ ስንሆን መናኛ፣ ስንሆን ምፃ’ተኛ።

ተርፎ ከሚደፋው፣ የዕለት ጉርስ አ’ተን
እንላብሰው ልብሳችን፣ አልቆ ከላያችን፣
ተጋልጦ ገላችን፤

እምቦቀቅላ ልጅ፣ የሙት እናት ጡት
ሩሄ ሆኖበት ሊጠባ ሲጎትት፤

ነፍሰ ጡሯ “አምሳለ ፍቁር”፤ ሆዷ ሲተለተል፤ ጽንሷ ሲገደል
በልጇ ሬሳ ላይ ስታለቅስ ሃርሞ ፣ ”ዋቆ የት ነህ?”ስትል፤

የመከራው ቋቱ ፣ የሰቆቃው ጽዋ ፣ የታሪክ ማኅደሩ
ትውልድ አልፎ- ትውልድ፣ ላይማር- መማሩ፤

ወገን- በወገኑ፣ ሰይጣን የማያውቀው፣ ይኽ ሁሉ ስቃይ
ከቶ ምን ይመስላል ከላይ ሆኖ ሲታይ?

ነገራችን ሁሉ እንዳይሆን !
እንዳይሆን! እንዳይሆን!………
“—-ከፈርሱ ጋሪን እንስቀድማለን፤

አሳን ለገደል – ዝንጀሮን ለባህር
እናሰማራለን፤
አንበሳን ለሸክም – በቅሎን ለቀንበር
እርሻ እንልካለን፤
ብረት ምጣድ ጥደን፣ ቅቤ እንጋግራለን።—-”
ይኽ ሁሉ ድንብርብር፣ ከቶ በአንተ ሰማይ እንደምን ይታያል?
ይኽን ያህል ዘመን ምንስ ታዝበሃል?–
ለስልጣኔ አቻ፣ ድንቁርናን ወርሰን
ከነበረን ዕምነት እርሾውን አድርቀን፤
የእፍኝት ልጆች፣ ከብረው ሲነግሱብን
እውነት አንገት ደፈታ፣ ሃሰት ሲገንብን፤
‘ርስ – በእርስ ተባልተን ስንተላለቅ
ሰማይ ያንተ ዝናብ፣ ምንጩ ለእኛ ሲደርቅ
አገር አልባ ስንሆን፣ ዓለም ሲመጻደቅ፤
አንተ የሁላችን፣ የጋራ የሆንከው
አንጋጠን ስናይህ፣ በእውነት አለወይ ለ’ኛ የደበከው?—–
——ግን እኔ የምልህ የኢትዮጵያ ሰማይ……፡
ቢጨንቀኝ እኮ ነው!
ቢጠባኝ እኮ ነው!
መላው ቢጠፋብኝ
እድሜዩን በሙሉ ሚስጥሩ ቢሆንብኝ
የልቤ-ደም እምባ፣ ዓይኔን ቢያስጓጥጥኝ፤
በድቅድቅ ጨለማ፣ በጋግርታም ለሊት ዓለም “በተኛበት ”
እኔና ወገኔ እንቅልፍ ባጣንበት
የመከራው ዝናብ፣ ዶፍ በሚወርድበት፤
አንተን ማናገሩ፣ ይቅርብኝ ልተወው
ሰማይን ለሚያክል ጥያቄ አቅርቦ መልስ ያገኘ ማነው::
ግን እኔ የምልህ !– የ’ኔን ዘንጋውና
አንተ የሚሳንህ ምንም የለምና
አዎ—–የኛ ነገር …….
ብንለው! ብንለው !ብንለው! ብንለው!
አንስተን -ብንጥለው፣ ጥለን – ብናነሳው፤
ውሃ መውቀጥ ሆኖ፣ ውሉ ጠፍቶብናል
ከሰው ተራ ወርደን፣ ስብዕናችን ጠፍቷል።
ስለዚህም ሰማይ—–
ፍቃድህ ከሆነ፣ ከፈቀድክልን
በቃችሁ ብለህ ኢትዮጵያን አጽናልን
ወይም ምድሯን ውረስ፣ አንተ ተተካለን።

——//——ፊልጶስ
e-mail: philiposmw@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በእብደት ላይ እብደት እየጨመሩ ያሉት የአድዋ ልሂቆች – ነጋሪት

Next Story

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት አጽድቋል

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop