Browse Category

ነፃ አስተያየቶች - Page 86

የባለሙያ ቡድናችን ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የግልነፃ የመረጃ ስብሰባዎች

ኢትዮጵያዊነት  እና ፋኖን  ለያይቶ ማየት እንዴት..? –  ማላጂ

ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት እና ገናናነት አብዝተዉ የሚናገሩ ግን ደብቅ ፀረ ኅዝብ እና ዓማራ አስተሳሰብ ያላቸዉ ከራሳቸዉ የግል እና ቡድን ጥቅም ዉጭ ሌላ እንዲጣስቡ መጠበቅ ከንቱነት ነዉ ፡፡ ይህን አለማሰብም ሆነ አስቀድሞ ከታሪክ
January 13, 2022

ውድ ወንድሞችና እህቶች – ሙሉጌታ በትረ ገብረማሪያም

እንደገና አብዝቶ በአያሌው ጤና ይሥጥልኝ!! እንዲያውም ብዙም … ወደ የቅርብ ሩቅ የኋለ መለስ ብለን …፣ ልክ በ“ወንጀለኛው ዳኛ” መጽሐፍ በጉልህ እንደተመለከተው ሁሉ፣ምናልባትም ”ከወዳጅ ጠላት ያድን“፣ ”ልዩ ዋጋ ለማይከፍል ልዩ አስተያየት አያስፈልገውም“፣ “ከጠረጠሩት ክፉ ያልጠረጠሩትን መልካም
January 12, 2022

 ከነ “ጃሥ“ከእሥር መፈታት ጀርባ ታላቅ ሤራ አለ ። ሲና ዘ ሙሴ  

ከዚህ የእሥር መቋረጥ በሥተጀርባ የተጠነሰሰ ታልቅ ሤራ እንደነበረ  ወደፊት ገለፅ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ። ወደፊት እነ ጃሥ የራሳቸው ኃይለኛ ሤራ እንደሚኖራቸውም ይገመታል  ። ክሳቸው የተቋረጠላቸው እነ ጃሥ ( ጃዋርና ሥብሐት )
January 11, 2022

ፍትሕን እራሳቸዉ አልከሰከሷት!-መኮንን ብሩ(ዶ/ር)

ከክርስቶስ ዉልደት አንድ መቶ ሰባ ዓመታት በኋላ የተወለደዉ ሮማዊዉ ዳኛ ዮፒያን “ፍትህ ማለት ሁሉም የድርሻዉን ይቀበል ዘንድ የሚያደርግ ሚዛን ነዉ” ሲል ይገልፃል። አርስጣጣሊስ በበኩሉ “የሰዉ ልጅ ከሕግ እና ፍትህ ዉጪ ከሁሉም አዉሬዎች የከፋ አደገኛ ፍጡር ነዉ” ሲል የሕግና ፍትህን አስፈላጊነት ያሰምርበታል። ያለ ሕግ እና ያለ ፍትህ ሀገር ሊኖር ቢችልም ሰላምና ዲሞክራሲ ግን ፈፅሞ አይታሰብም። እንግሊዛዊዉ ፈላስፋ እና ፖለቲከኛ ፍራንሲስ ቢከን “ፍትሕን መጠበቅ ያልቻለ ሕብረተሰብ ወይም ሀገር እራሱን መጠበቅ አይችልም” ሲል ፅፏል። ፍትህ ለሰዉ ልጆች በመከባበር አብሮ ለመኖር ወሳኝ ነዉ። ያለ ፍትህ ጭቆና ወይንም አምባገነን የትዉልድ ነቀርሳ ሆኖ ይንሰራፋል። “ፍትህ ባለበት ማንኛዉም እዉነት አይጎዳም” ይሉ ነበር ጋንዲ፤ ያለ ፍትህ ግን ሁሉም ይጎረብጣል። ከአንድ ቀን በፊት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ የእራሳቸዉን መንግስት በተለያየ ፈርጁ አምርረዉ ሲወቅሱ ተደምጠዋል። በተለይም የፍትህ ስርሃቱን የዘቀጠና የተጨመላለቀ ሲሉ ገልፀዉት ነበር። ይሁን እንጂ እስከ ገና ባዕል ምሽት ድረስ ጠቅላዩ ሊሉ የፈለጉት በትክክል የተገለፀለት ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ለፍትህ የሚታገል ግን ፍትህን የተራበ ሕዝብ በመሆኑ የጠቅላዩን “የዘቀጠ የፍትህ ስርሃት” ንግግርን ያዳመጠዉ የነገን የፍትህ ዘመን ተስፋ በመናፈቅ እንጂ ሰዉዬዉ በኢፍታዊነት ቆስለዉ አመርቅዘዋል ብሎ አልነበረም።ይሁን እንጂ የሕመማቸዉ ዱብዳ በጌታ ልደት ምሽቱ ተገለጠ። በርካቶችን ለሞትና ለስቃይ የዳረጉትን ፋሺስቶች በቀጭን ትህዛዝ ከእስር እስኪለቁ ድረስ በእዉነትም አብዝተዉ የተጨማለቁ ብቻ ሳይሆን በኢፍታዊነት ነቀርሳ የቆሰሉና የሚያጣጥሩ በሽተኛ መሆናቸዉን ያልጠረጠሩ ሁሉ ዕጢ አስጣሉ። አዎን ጠቅላዩ በኢፍታዊነት በፀና ታመዋል። አመርቅዘዋልም። በአንድ ወቅት እራሳቸዉ ሲናገሩ “ከዉጪ ሀገራት ለምኜ ያመጣሁትን ፍራንክ ምንም ላደርገዉ እችላለሁ፤ …… ፓርላማዉም ሊጠይቀኝ አይገባም” ብለዉ ሲመፃደቁ ብዙዎቻችን ሰምተን እንዳልሰማ ያለፍነዉ ሰዉዬዉ በለመኑት ሳንቲም እየሰሩ ያሉት ለሀገር ሊጠቅሙ የሚችሉ ፓርኮችና መዝናኛ ቦታዎች በመሆናቸዉ እንጂ የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ፣ በሕዝብ ጊዜና ገንዘብ ከሀገር ሀገር እየበረሩ፤ በትረ ስልጣኑንም ሆነ ማዕረጉን ተላብሰዉ በየሄዱበት ዕቅፍ አበባ እየታቀፉበት ልትጠይቁኝ አትችሉም የሚለዉ አባባላቸዉ ዉሃ የማይቋጥር ተላላ አባባል መሆኑ ሊገባቸዉ እንዲት እንዳልቻለ ተገርመን ትተነዋል። ምናልባት ያኔ የሕመማቸዉ ሁኔታ ቀላል ቁስል ቢጤ በመሆኑ እያደር ይደርቃል ያሉ በርካቶች ሳይሆኑ አይቀሩም። አሁን አሁን ግን ቁስሉ ዉስጥ ዉስጡን ሳያመረቅዝ የቀረ አይመስለኝም። ይህ ደግሞ አደገኛ ነዉ። አሜሪካዊዉ ገጣሚ እና ፀሐፊ ተዉኔት ጀምስ ባልድዊን እንደሚለዉ “አለማወቅ ከስልጣን ጋር ከተጣመረ በጣም አደገኛ ነዉ”። ጠቅላዩ የኢፍትሃዊነታቸዉን ጥልቀትና ንቅዘት አለማወቃቸዉ ከድርጊታቸዉ በላይ አደገኝነቱ አስፈርቶኛል። ማርክስ ኤንግልስ እና ሌኒን የሶሻሊዝም መገለጫዎች የሆኑትን ያህል ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ እና ደብረፂሆን የሽብርተኛዉ ትህነግ ማዕተሞች ናቸዉ።እነዚህ ፋሺስቶች  የሃያ ሰባቱ ዓመታት የኢትዮጵያዊያን ስቃይ እና እንግልት፣ ለብዙ ሺዎች ከሀገር መሰደድ፣ ለበርካቶች አካለ ስንኩል መሆን፣ ለመቶ ሺዎች ያለ ወላጅ አልያም ያለ ልጅ ባዶ መቅረት ተጠያቂ ናቸዉ። በተጨማሪም ላለፉት አንድና ሁለት ዓመት በተኙበት ለተረሸኑ፣ ከወላጆቻቸዉ ተመንጭቀዉ ተወስደዉ ለተደፈሩ፣ ቅዬቸዉ በትግራይ ወራሪዎች ተወሮ በቁማቸዉ ለተቃጠሉ ወገኖቻችንም ኃላፊነቱ በእነሱ ጫንቃ ላይ ነዉ። ታዲያ አንድ ቀን ለፍርድ ሳይቆሙና ሳይጠየቁ መለቀቃቸዉ የማያበሳጨዉ ካለ እሱ ገዳዩና ደፋሪዉን መሆን አለበት። ለዚህም ወንጀል ፍትህን የማይሻ እርሱ በሽተኛ ነዉ። ጊዜ ይፈጃል እንጂ ፍትህ ደግሞ ሁሉም ላይ መፋረዷ አይቀርም። ፍትህ ያጎደለም፣ ፍትህ ያዛባም ሁሉም በጊዜ ዉስጥ ዋጋዉን ከፍትህ ያገኛል። ከሁለት ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ የቀድሞ ነገስታትንና መሪዎችን በመጠቃቀስ የሚመስለኝን ፁሑፍ ለአንባቢዎቼ አቅርቤ ነበር። መይሳዉ ካሳን በጀግንነቱ፣ እምዬ ሚኒሊክን በብልሃተኝነታቸዉ፣ ኮረኔል መንግስቱን በሀገር ፍቅር ስሜታቸዉ፣ እንዲሁም ዶክተር አብይን ከፕሬዘዳንት ሊንከን ጋር በማመሳሰል ኢትዮጵያን በዚህ ወቅትም ለማስቀጠል መቻላቸዉን በመተረክ የእኛዉ ሊንከን ብያቸዉ ነበር። በዚያ ፁሑፌ አልፀፀትም፤ እንደዉም አሁንም ቢሆን ያ ዕምነት እና አመለካከት በእሳቸዉ ላይ አለኝ። ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በሆነ መልኩ ብቅ ብለዉ የተዋጋሁት ለኢትዮጵያ አንድነት ስል አልነበረም እስኪሉ ድረስ (የሚሉ ከሆነ) እኔ ለኢትዮጵያ መዝመታቸዉን አደንቃለሁ። እቀበላለሁ። ይሁን እንጂ ይህን ያህል ጭፍን እና ኢፍትሃዊ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ መቼም ገምቼ አላዉቅም ነበር። ይህ ብቻ አይደለም፤ መዋሸትም እንደሚችሉ ታዝቢያለሁ፣ በመሆኑም ዳግም ላምናቸዉ እቸገራለሁ። “ሽማግሌ ከፍርድ በፊት አትላኩ እኔ ይህን ማድረግ አልችልም” ያሉትን ዘንግተዉ በቀጭን ትህዛዝ ፋሺስቶችን ከእስር ቤት በመፍታት ዋሽተዋል። የዋሸ ደግሞ ዉሸታም ነዉ። ስለሁሉም አዝናለሁ። ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! መኮንን ብሩ (ዶ/ር)

ሳይቃጠል በቅጠል! – አበበ ገላው

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የስልጣን መንበሩን ከተቆጣተሩ ጀምሮ ለበርካታ ጊዜያት የልባቸውን ስሜት በውብ ቃላት አጅበው ለህዝብ በንግግር አቅርበዋል። ለዚህም ህዝቡ ከመቀመጫው ተነስቶ በተደጋጋሚ አክብሮቱን ገልጿል። በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በተረከቡ ሰሞን ፓርላማ ቀርበው

አወዛጋቢው የመንግስት ውሳኔ – ፋሲል የኔዓለም

ፖለቲካ ትርፍና ኪሳራን አስልቶ የሚከወን ስራ ነው። ከንግድ የሚለየው ነጋዴዎቹ ፖለቲከኞች መሆናቸው ብቻ ነው። ጠ/ሚኒስትሩም ይህን ውሳኔ ሲወስኑ፣ እንደ ነጋዴ፣ ትርፍና ኪሳራውን አስልተው ነው። ቢያንስ አምስት ነገሮችን ግምት ውስጥ አስገብተው የወሰኑት እንደሆነ

ምሕረት ሲሉ : ፍትሕ ስንል ለየቅል!!! – ከቴዎድሮስ ሃይሌ

የታማሚው የበሽታ ውጤት መክፉት ያስጨነቀው ዶክተር በደንበኛው ላይ ሊያስከትል የሚችለውን የአካልስቃይና የሞራል ስብራት አለሳልሶ በዘዴ ለመንገር መላ ይዘይዳል:: ታማሚውም ዶክተሩን ሲመለክት እንዴት ነውጤናዬ ሲል ይጠይቃል ? ዶክተሩም ለታማሚው ጥሩም መጥፎም ዜና አለ

ኢትዮጵያ በታሪኳን እንደ ዐቢይ አሕመድ አይነት እቡይና ፍጹም አምባገነን አጋጥሟት አያውቅም! – አቻምየለህ ታምሩ

በኢትዮጵያውያን ሕይዎት እንደሚቀልደው እንደ ከሀዲው ዐቢይ አሕመድ አይነት ፍጹም ስልጣን የነበረው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፣ ፕሬዝደንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አልነበረም። በነገሥታቱ ዘመን እያንዳንዱ መንግሥታዊ ውሳኔ ሲወሰን ሥርዓት ነበረው።የኢትዮጵያ ሥነ መንግሥት ፈላጭ ቆራጭ ንጉሠ ነገሥት

የዐብይ አሕመድ ተውኔት፣ ገቢር አምስት – መስፍን አረጋ

ጥያቄ፡  የተጭበረበረው ምርጫ መጭበርበሩ ሙሉ በሙሉ ስለተረሳና ኦነጋውያን አዲሳባን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩ እስክንድር ነጋ ምንም አያመጣም ተብሎ ታሰበና ከእስር ተፈታ፡፡  ዐብይ አሕመድ ድምጹን አጥፍቶ አማራን እስኪያጠፋ ድረስ አፋቸውን ሳይከፍቱ በቅምጥል እየኖሩ ሊጠባበቁ

ለይቶና አቅዶ የገጨንን ዘር ጨፍጫፊ ሾፌር ለቀው ተሽከርካሪውን (የነጂውን) እንዴት እንክሰሰው? – ወንድእጥር መኮነን 

ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ማሳሰቢያ- ጽሁፍ ከምሰራው ስራም ከመስሪያቤቴ አቋም ጋርም አይያያዝም!! – ወንድእጥር መኮነን የሰሜን እዝ ጭዳነት ዝንጋኤ ይገባዋልን? ሞረሽ ለሃገሬ ብለው ለተሰዉት ጀግኖች አጽም ፍትሃት እንጂ ዳግማዊ ግፉዕነት ልኬታቸው ነውን? በአሸባሪዎች

ለቂም በቀል ያልታጨ ማንነት – በቀለ         

አዲሱ ትውልድ  አምቆ የያዘውን አልበገር ባይነት ወቅትን ጠብቆ ተነሳ !!! ኢትዮጵያን አዳነ እውነትም አኩሪ ተግባር ፈፀመ የማንነታችን ተምሳሌት  በዚህ ዘመን የተገኙ ከቀድሞዎቹ ጀግኞች ተርታ አሰለፈው እምቢ እነኔቴን አሳልፊ አልሰጥህም የሚለው ማንነት ለመስዋት የቀረበ

ለልብ ሰባሪው ሰበር (ከፈረሱ በፊት ለቀደመው ጋሪ)  የሚሰጡ ማብራሪያዎች ሁሉ የንፁሐንን እንባ አያብሱም። ሲና ዘ ሙሴ

ሰበር ዜና ፤ እነ  ጃዋርን እና እነ ሥብሐትን ፣ በነሱ ክስ የተመዘገቡትን ሁሉ ከሞራል አንፃር ፈታናቸው ። ከሞራል አንፃር እነ ጃዋርን እነ ሥብሐትን ፈታናቸው ። ተባለ ። ለነጃዋር ፣ ለነሥብሐት ደጋፊዎች ይህ ታላቅ ድል ነው

ፍትህ የሌለበት ይቅርታና ምህረት በምድር ላይ ቀርቶ በሰማይ ቤትስ ይኖር ይሆን??

እነ ስባሃት ነጋ ተፈቱ፣ እነ ጀዋር ተፈቱ፣ እነ እስክንድርም ምን ያህል ጦር እንደመሩና የተኛውን እዝ እንደ አጠቁ ባናውቅም በምህረት ተፈቱ። ´የለህም አይባል ይመሻል ይነጋል አለህ እንዳይባል ስንት ጉድ ይታያል።´ ያለችው መሪ እረምዴ
1 84 85 86 87 88 249
Go toTop