ውድ ወንድሞችና እህቶች – ሙሉጌታ በትረ ገብረማሪያም

እንደገና አብዝቶ በአያሌው ጤና ይሥጥልኝ!!

እንዲያውም ብዙም … ወደ የቅርብ ሩቅ የኋለ መለስ ብለን …፣ ልክ በ“ወንጀለኛው ዳኛ” መጽሐፍ በጉልህ እንደተመለከተው ሁሉ፣ምናልባትም ”ከወዳጅ ጠላት ያድን“፣ ”ልዩ ዋጋ ለማይከፍል ልዩ አስተያየት አያስፈልገውም“፣ “ከጠረጠሩት ክፉ ያልጠረጠሩትን መልካም መስማት ያስደነግጣል”፣ “የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይለማመጡ”፣ “ሞቴ ያሞማዋቴን ያህል አያሳዝነኝም”፣ “ድል ነስቶ መሸሽ”፣ “የህዝብ ድምጽ የግዜር ድምፅ …“ ዓይነት፣ በተለይም እንደ የተባበሩት አሜሪካ ስቴትስ አስተዳደርና ጋሻጃግሬዎቻቸው መልካም ነገር ያመጣሉ ብሎ ማሰብ … እጅግ በጣም አሳሳቢ እጅግ በጣም አስጊ እጅግ በጣም አደገኛ … የተሳሳተ የስሌት መላ ምት!!

እንደ አጠቃላይ፣ ብርቅ ዕፁብ ድንቅ ውድ ኢትዮጵያችን ዓውድ፣ በተለይም ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ጊዜ ያህል፣ ዓይነተኛ ሁነኛ የመፍትሔ መላ ባልተገኘለት፣ ከውስጥም ይሁን ከውጭ ኃይላት በሚወነጫጨፉብን፣ በፅንፍ ሰበዞች የተመረዘ፣ በተረኝነት አባዜ የተጠላላፈ እጅግ በጣም አደገኛ፣ የሴራ ፖለቲካ አዙሪት ማዕቀፍ ወስጥ ተተብትበን በመደነቃቀፍ ስንዳክር ስንደነጋገር ስንደፋደፍ ስንገፈታተር ስንታመስ ስንተረማመስ፣ ወዘተ፣ ይህ ነው ሊባል የሚችል ትርጉም ሠጪ የሆነ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ያለመቻላችን ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ፣ ያፈጠጠ ያገጠጠ ጥሬ ሐቅ፤ እንዲያውም አያሌ መሥፈርቶች (በአስተዋይነት በትኩረት በጥንቃቄ በሉዓላዊነት በነፃነት ምድረ-ባህረ ነጋሽን (በአሁኑ የ“ኤርትራዊያን” ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን) ጨምሮ በአንድነት እና በመሣሠሉት ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስከበር በጥብቅ በቁርጠኝነት በጽናት በመከራከር በመሞገት) በኩል፣ ምናልባትም የኋልዮሽ ሊባል በሚችል ካልሆነ በስተቀር፣ …፤

በብዙሐኖቻችን ረገድ፣ በመሠረታዊ ማህበራዊ መሥተጋብሮቻችን (ግንኙነቶቻችን) በኩል፣ በሰላም በአስተዳደራዊ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በውኃ፣ በመብራት፣ በፀጥታ በደህንነት፣ ወዘተ አገልግሎት ጥራት ረገድ፣ በተለይም ከህዝብ መጠን፣ ከዘመኑ የረቀቀ የሥልጣኔ (ዘመናዊ ዕውቀትና ተግባረዕደ) ደረጃ፣ ወዘተ ጋር በንጽጽር …፤ እጅግ በጣም ኋላ ቀር …፤ በአመዛኙ የካድሬዎች የጋሻጃግሬዎች የይስሙላ የድለላ የሽንገላ ትዕይንቶች መድረክ ካልሆነ በስተቀር፣ ትክክለኛ ነፃ ህዝባዊ ምክክሮችና ውሳኔዎችንም በተመለከተ፣ ገና በብርቅ በሩቅ … እንደተመኘናቸው ባጀን፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለኦሮሞ አባቶችና ልሂቃን - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

እሺ እስኪ ሌላውን ሁሉ ትተን፣ ዓመታዊ የሰብል ግብርና ምርትን ብቻ፣ እንደ ዓይነተኛ ሁነኛ ማሣያ ብንወስድ እንኳን፣ ለአያሌ አሥርተ ዓመታት፣ ከዓመት ወደ ዓመት በነፍስ ወከፍ ተመን ከሁለትና ሦስት ኩንታል በላይ ዕመብዛም ያልተሻገረ … በነበረበት የመዳከር የዜሮ ድምር አዙሪት፤ የእንስሳትና የዓሣ ምርትም …፤ በየሣምነቱ በየቀኑ ማለት በሚቻል መልኩ፣ የዋጋ ንረት …፤

በውጭ ንግድ ረገድም እንዲሁ፣ ከዓመት ወደ ዓመት በዛ ቢባል ሦስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ብቻ የተወሰነ፤ ለንጽጽር ያህል፣ ብዙም ሩቅ መጓዝ ሳያስፈልገን፣ እንደ ታነዛኒያ፣ ኬንያና ዩጋንዳ የመሣሠሉት ሀገራት፣ በህዝብ ብዛት ወደ አንድ ሦስተኛ በዛ ቢባል ደግሞ አንድ ሁለተኛ ሲሆን፣ በገቢ ረገድ ግን፣ በየዓመቱ ከኢትዮጵያችን ከሦስት ዕጥፍ በላይ … ሩዋንዳም በአጭር ጊዜ …፤

የኢትዮጵያችንን ወቅታዊ የዲጂታል (በምጣኔ ሀብት ዙሪያ ልዩ ትኩረት) ስትራቴጂን በመቅረጽ ረገድ፣ ጉልህ የጥቅም ግጭት ያለባቸው እንደ እነ የቶኒ ብሌር ፈውንዴሽንና የመሣሠሉት ተቋማት በሁነኝነት በቅርብ ሩቅ ‘የሚቆጣጠሩት’ …፤

ብቻ ከወቅታዊ የተረኛ የአንዳፍታ መናኛ ቡድነኛ ወገንተኛ የታይታ የዝና ቱማታ ባለፈ፣ በመሠረታዊነት ይህ ነው የሚባል ዓይነተኛ ሁነኛ …፤

ከዚህ በላይ በተመላከቱት እጅግ በጣም ጥቂት ዋነኛ ጥቆማዎችን እና አያሌ ሌሎች ምክኒያቶችን ምርኩዝ በማድረግ፣ አጣዳፊዉንም የረዥም ጊዜዉንም በጣምራ፣ በሁሉም ግንባር ከመቼውም ጊዜ በላይ፣ እጅግ ልዩ በሆነ፣ በላቀ የአርበኝነት የቅንጅት ቁጭት ባለማሰለስ በብርቱ ለመረባረብ የውዴታ ግዴታ’ አለብን ቢባል …!!

ሙሉጌታ በትረ ገብረማሪያም

ጥር ፬ ቀን ፪ ሺህ ፲፬ ዓ. ም.

 

 

1 Comment

  1. ይገርማል ፓለቲካው ተማቶብናል የምለው ያለ ውል አይደለም። አሁን ማን ይሙት ከአውራ ጣት አመልካች እጣት ይሻላል? ዘመን መቁጠርስ የነጻነትና የእምነት ጥንካሬ መሰረት ነው? የመጀመሪያው ቪዲዮ ባይለጠፍ ይሻል ነበር። ፍሬፈርስኪ ይሉሃል ይሄ ነው። እኔ ቀድሜ ተወልጄአለሁና አንተ ቆመህ እኔ ልብላ አይነት ነው። ግን እውነቱ ይህ ነው። ልክ የአሜሪካ ፕሮቴስታንቶች ሁሉም ባይሆኑ ይበልጡ የሰው ልጆች መብት አደፍራሹንና በራሱ ጉራ የታሰረውን ዶላንድ ትራንፕን በጭፍን እንደ ደገፉት ሁሉ የሃገራችን ፕሮቴስታንቶችም ዶ/ር አብይን የሙጥኝ ያሉ ይመስላል። ይህ ታላቅ ስህተት ነው። የጠ/ሚሩ ተግባር አሁን አሁን ሲታይ ወያኔ ቀመስ ነው። የወደመውን ሃብት፤ የሞተውን ሰው ቁጥር፤ የተፈናቀለውን ሰው እንባ ደምሮ ላሰላ የአብይ መንግስት ብልጽግና አምጭ ሳይሆን ድህነትና መከራ እንደሆነ ያሳያል። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል የሚሉት አበው እንዲህ ባለው ተግባር ነው። እናስብ። ዶ/ር አብይ ከወያኔ ጆኒያ ያፈተለከ ሰው ነው። እነርሱን ባይመስል ያን ሁሉ ዘመን አብሮ መስራት ባልቻለም ነበር። የሚያስብና የሚጠይቅ ጭንቅላት ያላቸው ሃገር ለቀው ተሰደዋል፤ ታስረዋል፤ በግፍ ተረሽነዋል። በካፒቴን ተንኮሉ ላይ ወያኔ የፈጸመ የሁለት ዓመት የጨለማ ቤት ሰቆቃና በህዋላ ከሻቢያ ጋር ወያኔ ሲፋለም ጨንቆት ከእስር መፍታቱ ለክፋታቸው ጥልቀት በህይወት ቆመው ከሚናገሩት ሰዎች አንድ ነው። የእናቱ ሞት በጄ/አበበ ተ/ሃይማኖት እየተሰደበችና እየተገፋች ልጄን እንዳለች ማረፏ እውነተኛ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ የሚያስለቅስ ነው። እነዚህን ግፈኞች ነው አሁን አብይ በአሜሪካ ትዕዛዝ የፈታው። እንኳን በእግርህ በእጅና በጉልበትህ ተጎብሰህ ብትሄድ አሜሪካን ደስ ማሰኘት አትችልም።
    ጸሃፊውና ቪዲዮ ለጣፊው አቶ ሙሉጌታ የጠቀሱት መጽሃፍ ” ወንጀለኛው ዳኛ” የሃዲስ ዓለማየሁን ይመስለኛል። አሁን ወንጀለኛ ዳኛ የለም። ለወንጀል የሚፈርድ እንጂ። እንዲያውም ይባስ ተብሎ አሁን አንድ ኦሮሞ ወይም አማራ ሲታሰር ማጣጫ ታሳሪ ከአንድ ወገን አብሮ ዘብጥያ መውረድ አለበት። ምሳሌ፡ ታምራት ነገራ ሲታሰር፤ መዓዛ መሃመድ፤ ጀዋርና በዙሪያው ያሉ ሲታሰሩ፤ እስክንድር ነጋና በዙሪያው ያሉ ነው ተጋፈው የተዶሉት እስር ቤት። ፍትህ በምድሪቱ መንገዳገድ የጀመረው በወያኔ ጊዜ አይደለም። ከዚያም በፊት እንጂ። አሁን ግን ለይቶለት በወያኔና በአብይ ዘመን የእንፉቅቅ መሄድ ጀምሯል።
    በጥቅሉ ያለፈን ጠቅሶ፤ የአሁኑን መርምሮ ዘርና ቋንቋ ወደ ኋላ በመተው በሰውኛ መንገድ መሰለፍ ቀርቷል። ይህ እንዳይሆንም የሃገርና የውጭ ሃይሎች ሌት ተቀን ይሰራሉ። ለዚያ ነው ሽዋ ድረስ ወያኔ አልፎ ሃገር እስኪያወድም ድረስ ተጠብቆ ዘመቻ ተብሎ ነጻ አወጣን እያሉ ከበሮ የሚመቱት። እብደቱ የጋራ ነው። ወያኔ ካበደና ጨርቁን ካወለቀ ቆይቷል። እብደቱ ግን መላ ያለው ነው። ስልት አላቸው። ይተባበራሉ፡ ያስተባብራሉ። አንድ በቅርብ የሆነ ነገር ላስረዳችሁ።
    ልጂቱ 100 ዶላር ይዛ ለእናቷ ለመላክ እንደ አሸን ከፈሉት የወያኔና የሻቢያ የመላኪያ ሱቆች በአንድ ቆማለች። ምን ፈልገሽ ነው ይላታል ባለ ሱቁ። ገንዘብ ደብረሲና ለእናቴ ለመላክ ትለዋለች። የሆነ መዝገብ ያወጣና ሲመለክት እዚያ ከተማም ተወካይ እንዳላቸው ያይና እሺ ስንት ነው መላክ የምትፈልጊው ይላታል። 100 ዶላር ትለዋለች። አይ አሁን ወደ ሃገር ግቡ መባሉንና በዓሉን አስመልክተን የለውጥ ጭማሪም፤ የመላኪያ ቅናሽም አድርገናል። ያንቺ ትንሽ ስለሆነች 95 ስጭኝና እዚያ መቶ እንዲደርሳቸው አረጋለሁ ይላታል። እሷም ገልጃጃ ነገር በመሆኗ ምርቃቱን ታንጎደጉደዋለች። ከጎኑ አብሮ ከቆመው ሌላ ትግሬ ጋር ከት ብለው ይስቃሉ። ገንዘቡ እንደተባለው በማግስቱ ለእናት ይደርሳል። ሴራቸው ግን ማንም ሰው ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት እንዳይልክና መንግስት የውጭ ምንዛሬ ሪዘርቭ እንዳይኖረው ለማድረግ የዘረጉት ሴራ አንድ ቅርንጫፍ ነው። እዚያ የሚሰጠው ብር የተሰረቀና ከኢትዮጵያ ህዝብ ለ 27 ዓመት የተዘረፈ፤ አሁን ደግሞ በወሎ፤ በአፋር፤ በጎንደርና በሽዋ ባንኮችን እየሰበሩ የዘረፉት ገንዘብ በስልት ለሰዎች ተሰራጭቷል። ሥራቸው የጠለቀ ነው። ያዘኑ መስለው ይገድሉሃል። ገድለው አብረው ከሚያዝን ጋር ሃዘን ይቀመጣሉ። ኸረ ስንቱ! ከእነዚህ ጉዶች ጋር ነው ዶ/ር አብይ ሰላም የሚፈጥረው። በነጻ የወያኔን የሞት ሳጥናኤሎች የፈታውና ሌሎች ንጽሃን ወገኖቻችን በየስፍራው ታጉረው የሚገኙት። ባጭሩ ኦርቶዶክስ/ፕሮቴስታን/ወዘተ እየተባባሉ መነታረኩ ፍሬ የለሽ ነው። መስቀል አደባባይ ወራሽ የለውም። የሰማይ ቤትም የለም። ከፈለክ እዚያው ሂድና ሥራ። የመስቀል አደባባይ የአንድ ሃይማኖት መሰብሰቢያ ብቻ ሊሆንም አይችልም። ይህ አክራሪነት ነው። ጠብ የለሽ በዳቦ ይሉሃል ይሄ ነው። ግን የፕሮቴስታንት አማኞች ለጠ/ሚሩ ያላቸውን ድጋፍ ቆም ብለው ቢፈትሹት ሰልፍ ከመውጣት ያድናቸዋል። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share