ሳይቃጠል በቅጠል! – አበበ ገላው

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የስልጣን መንበሩን ከተቆጣተሩ ጀምሮ ለበርካታ ጊዜያት የልባቸውን ስሜት በውብ ቃላት አጅበው ለህዝብ በንግግር አቅርበዋል። ለዚህም ህዝቡ ከመቀመጫው ተነስቶ በተደጋጋሚ አክብሮቱን ገልጿል።

በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በተረከቡ ሰሞን ፓርላማ ቀርበው አሸባሪ የነበርነው እኛ ነን በማለት የህወሃት እንደራሴዎች በታደሙበት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ሲጠይቁ ከመቀመጫዬ ተነስቼ ማጨብጨብ ብቻ ሳይሆን በደስታ አንብቻለሁ። “ስንጠብቀው የነበርውን መሪ አሁን ገና አገኘን፤” በማለት ለብቻዬ በሲቃ ጮህኩ። ያቺ ንግግር ነበረች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመደገፍና የተጀመረው ለውጥ ከዳር እንዲደርስ መልካም ከሚመኙ መሃል ያደረገችኝ።

ያ ሁሉ ቀረና ዛሬ ግን ጠቅላዩ የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ምረቃ ስነስርአት ላይ ያደረጉትን ንግግር ስስማ በአድናቆት ከመቀመጫዬ ተነስቼ ከማጨብጨብ ይልቅ ዝምታቸውን ተመኘሁ። ለእነ ስብሃት ነጋ መፈታት የደረደሩት ምክያትት እንኳንስ ሌላ ሰው እርሳቸውንም ማሳመኑን እጠራጠራለሁ። ፈጽሞ ያልተዋጣለት ንግግር!

ምህረት ያደረግነው ስላሸነፍን ነው ይላሉ፤ የእነ ስብሃትን እድሜና ጤንነትን ያነሳሉ፤ እነ ስብሃት በህወሃት ውስጥ ወሳኝ አለመሆናቸውን ይጠቅሳሉ፤ የእነ ሚኒሊክ ዘመንን ታሪክ ያትታሉ፣ ጉዳዩን ስንሰማ እኛም ደንግጠን ነበር ይላሉ። ይህን ሁሉ እርስ በርሱ የሚጣረስ ዝርዝር እየደራረቡ ጠቅላዩ መክሊታቸውንና በቀላሉ የማይገኝ ጸጋና ህዝባዊ አመኔታ እንደ ተራ ሸቀጥ አደባባይ ላይ ቆመው ሲያባክኑት በማየቴ ሃዘን ሰውነቴን ወረረው።

እርሳቸው የሚወክሉትን የኢትዮጵያ ህዝብ እና እስከ እዚች ደቂቃ ህዝብን በሚያሸብሩ፣ በሚገድሉ፣ በሚያፈናቅሉ፣ በሚዘርፉና በሚያተራምሱት ህወሃቶች መካከል ያለውን ስሜት በህሊናዬ ቃኘሁት። የህወሃቱ ጎራ የታባታቸው እያለ በህዝብ ሲዘባበት የወንጀሉ ሰለባ የሆነው ፍትህ ናፋቂው ህዝብ በዜሮ ውሳኔውን እንደ ኮሶ ቢመርህም ጭልጠው ሲባል መስማት ግፍ ሆኖ ነው ተሰማኝ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ልደቱ አያሌው፤ ፖለቲከኛ ወይስ ፖለቲካ ተንታኝ?

ጠቅላዩ ኢትዮጵያን የጸና መሰራት ላይ ለመገንባት ተወሰደ ያሉት እርምጃን አሉታዊ ግዝፈትን ጠንቅቀው የተረዱት አይመስልም። ከተረዱትም ምንም አያመጡም የሚል ስሜት ውስጥ የገቡ ይመስለኛል።

ባለፈው ጥቅምት የሁለተኛው ያለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ከ76 አመታት በሁዋላ በጀርመን ለፍርድ የቀረበው የመቶ አመት እድሜ ባለጸጋ የሆነው ጆሴፍ ኤስ የተባለው የናዚ ፓርቲ አባል ከእነ ስብሃት አንጻር ሲታይ ወንጀሉ በጣም ቀላል ነው። ግለሰቡ የእስር ቤት ጠባቂ በነበረ ጊዜ እስረኞችን በመግደል ተባባሪ ነበር የሚል ክስ ነው የቀረበበት። ጠበቆቹ ደግሞ ትእዛዝ ፈጸመ እንጂ ወንጀሉ የአዛዞቹ ሃላፊነት ነው ባይ ናቸው። ጀርመንን የመሰለ የሰለጠነ አገር ሊሞት አንድ ሃሙስ የቀረውን የመቶ አመት አዛንውንት ፍርድ ቤት ማቅረቧ ሰብአዊ ርህራሄ ስለጎደላት ወይንም የግለሰቡ ጤንነት ሳያሳስባት ቀርቶ ነው ብሎ ማለት አይቻልም። የናዚም ፓርቲ ከተሸነፈና በህግ ከታገደ ዘመናት ተቆጥረዋል። ለድርድር የማይቀርብ የፍትህ ጉዳይ ስለሆነ ህግ መከበር ስላለበት እንጂ ይህ ግለሰብ በአስራ አንደኛው ሰአት ቅጣት መቀበሉ ትርጉም ስላለው አይደለም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህወሃት ትጥቅ ባልፈታበት ጦርነት እያኬሄደና ለበለጠ ጥፋትና እልቂት እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ጊዜ ስላሸነፍን ምህረት አወረድን ማለታቸው በራሱ አግባብነት የጎደለው ክርክር ነው። ከሰርን እንጂ አላተረፍንም። እንደ እገር ተሸንፍን እንጂ አላሸነፍንም። አምስት ሺ የሚያህሉ ትምህርት ቤቶች፣ በርካታ ሆስፒታሎች፣ አስር ሺ በላይ የጤና ጣቢያዎች፣ መጠነ ሰፊ ዝርፊያና ውድመት በህወሃቶች ደርሶብን ስላሸናፊነት ማውራት ከንቱ ጨዋታ ነው። ያለቀውን ሰራዊትና ታጋይ ቤት ይቁጠረው።

እኔና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ የሚያሳስበው በጥጋባቸው ጦርነት አውጀው በረሃ ወርደው ምሽግ ውስጥ በብዙ መስዋትነት የተማረኩ ፋሺስቶች ጤንነትና እድሜ ሳይሆን የተደፈሩት አዛውንቶችና መነኩሴዎች ጤንነት ነው። እኛን የሚያሳስበን እነ ስብሃት አደራጅተው ለጥፋት ባሰማሯቸው የህወሃት ታጣቂዎች በአባቷ ፊት ለአራት የተደፈረችው የ12 አመት እንቦቀቅላ ጤንነት ነው። እኛን የሚያሳስበን በህወሃት የእብሪት ሰራዊት ቤት ንብረቱ ወድሞበት በየጢሻው የተበተነውና የሚበላውና የሚቀምሰው የሌለው በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብና ህጻናት ጤንነት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ያማራ ሕዝባዊ ትግል የመጨረሻ ግብ - መስፍን አረጋ

እኔ በበኩሌ እነ ስብሃት ከህዝብ የዘረፉትን እየበሉ በአሽከርና ደንገጡር እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሸራተን እንደ ለመዱት እያጨሱና እየጠጡ አስረሽ ምቺው ሲሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምስኪኖች ከቀዬቸውና ከቤታቸው ተፈናቅለው ልጆቻቸውን የሚያበሉት አጥተው የሚያነቡባትን ኢትዮጵያ ፈጽሞ ማየት አልፈልግም። ኢትዮጵያም ትርጉሟ ይሄው ከሆነ ለዘላለሙ ትቅርብኝ። እንዲህ አይነት አገር ኢንዲኖነኝ ፈጽሞ አልፈልግም።

ጠቅላዩ በረዱትም ባይረዱትም ስብሃት ነጋ የህወሃት ክፋት ቁንጮ፣ አርማና ምልክት ነው። ስብሃትን ይቅር ብለህ ህወሃትን መወንጀል በህግም በሞራልም ፈጽሞ አይቻልም። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የከፈለው መስዋትነትና ያደረገው ትግል መደምደሚያው የስብሃትን ንጽህና ለማረጋገጥና ለመመስከር የሚመስለው ካለ የዋህ ነው። ትግላችን መሰረቱ ፍትህ ፍለጋ ነው። ፍትህ ዋስትና ሳያገኝ አገርም ይሁን ሰላም ትርጉም አልባ ነው።

ይሄ ስህተት በምላስ ታሽቶ የሚስተካከል ተራ ስህተት አይደለም። ማንም ለድርድር ሊያቀርበው የማይገባውን የፍትህ ጥያቄን ከመሰረቱ የሚንድና ጥልቅ ትርጉም ያለው ብዙ ጣጣ የሚስከትል ጉዳይ ነው። ውሳኔው ህዝብና መንግስትን ፊትና ጀርባ ከማድረጉም በላይ በዱር ሸንተረሩ መስዋእትነት የከፈለውንና እየከፈለ ያለውን ታጋይና ወታደር ደም ደመ ከልብ የሚያደርግ ነው ታሪካዊ ስህተት ነው።

እነ ስብሃትን ነጻ ብሎ ሸኝቶ ከህወሃት ጋር መፋለም የሞራልም የስነልቦናም የበላይነትን የሚያሳጣ ግዙፍ ስህተት ስለሆነ እነ ፌልትማን ለዘላለሙ ቢያኮርፉ ይመረጣል። ለመንግስት የሚያዋጣው ህዝብ እንጂ የውጭ ሃይሎች አይደሉም። አሁንም በድጋሚ በጊዜ ይሄንን ታሪካዊ ስህተት ማረሙና ማስተካከሉ የተሻለ ነው። ሳይቃጠል በቅጠል!

8 Comments

  1. በበኩሌ እነ ስብሃት ከህዝብ የዘረፉትን እየበሉ በአሽከርና ደንገጡር እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሸራተን እንደ ለመዱት እያጨሱና እየጠጡ አስረሽ ምቺው ሲሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምስኪኖች ከቀዬቸውና ከቤታቸው ተፈናቅለው ልጆቻቸውን የሚያበሉት አጥተው የሚያነቡባትን ኢትዮጵያ ፈጽሞ ማየት አልፈልግም። ኢትዮጵያም ትርጉሟ ይሄው ከሆነ ለዘላለሙ ትቅርብኝ። እንዲህ አይነት አገር ኢንዲኖነኝ ፈጽሞ አልፈልግም።
    አቤ! እኔም ይህን ከሚሉት ወገን ነኝ! እጅግ ስው በደረስበት የዘመን ልልጣኔ ህሳቤ በይትኛውም ዓለም የጭካኔ ጥግ በወያኔ በእነ ስብሃት አመራር ስጪንት አአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደርስው ግፍና መከራም በዚህም አንድ ዓመት ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ የምንወራርደው ሂሳብ አለን ብለው ዕቅድ ይዘው ያንን ሁሉ ግፍ ስቅያ ዝርፍያ ውድመት እልቂት ምንም ሳይመስላችው እንደ ተራ ወንጀለኛ ስለህገር አንድነት ስንል ጠቅላይ ሚንስትሩ እየዋሹን እይተምታታባቸው ሲዘላብዱ ስስማቸው እጅግ በጣም እዝንኩ እፈርኩባቸውም!ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ሳይሆን የክህደት ወንጀል ጠቅላይ ሚንስትሩ ፈፅመዋል::ይህምድርጊታቸው ስልጣን መልቀቅና ለፈፀሙት በደል በህግም መጠየቅ አለባቸው::
    በተለይም የድያስፖራው ወገኔ በጠቅላይ ሚንስትሩ ተክደናል ::ሁላችንም ከህዝብ ወገን የህዝብ አለኝታነታችንን ወድቀደምው ተቃውሞ ትግላችን መመለስ ይኖርብናል::ወደ መንግስት ካዝና የሚገቡ ማናችውንም ዳርዳታና ድጋፍ ማቆምና በተለያዩ መንገዶች እንደ ቀድሞው ለወገናችን ድጋፉን ብቻ እናድርግ!!

  2. በበኩሌ እነ ስብሃት ከህዝብ የዘረፉትን እየበሉ በአሽከርና ደንገጡር እንክብካቤ እየተደረገላቸው ሸራተን እንደ ለመዱት እያጨሱና እየጠጡ አስረሽ ምቺው ሲሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምስኪኖች ከቀዬቸውና ከቤታቸው ተፈናቅለው ልጆቻቸውን የሚያበሉት አጥተው የሚያነቡባትን ኢትዮጵያ ፈጽሞ ማየት አልፈልግም። ኢትዮጵያም ትርጉሟ ይሄው ከሆነ ለዘላለሙ ትቅርብኝ። እንዲህ አይነት አገር ኢንዲኖነኝ ፈጽሞ አልፈልግም።
    አቤ! እኔም ይህን ከሚሉት ወገን ነኝ! እጅግ ስው በደረስበት የዘመን ልልጣኔ ህሳቤ በይትኛውም ዓለም የጭካኔ ጥግ በወያኔ በእነ ስብሃት አመራር ስጪንት አአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የደርስው ግፍና መከራም በዚህም አንድ ዓመት ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ የምንወራርደው ሂሳብ አለን ብለው ዕቅድ ይዘው ያንን ሁሉ ግፍ ስቅያ ዝርፍያ ውድመት እልቂት ምንም ሳይመስላችው እንደ ተራ ወንጀለኛ ስለህገር አንድነት ስንል ጠቅላይ ሚንስትሩ እየዋሹን እይተምታታባቸው ሲዘላብዱ ስስማቸው እጅግ በጣም እዝንኩ እፈርኩባቸውም!ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ሳይሆን የክህደት ወንጀል ጠቅላይ ሚንስትሩ ፈፅመዋል::ይህምድርጊታቸው ስልጣን መልቀቅና ለፈፀሙት በደል በህግም መጠየቅ አለባቸው::
    በተለይም የድያስፖራው ወገኔ በጠቅላይ ሚንስትሩ ተክደናል ::ሁላችንም ከህዝብ ወገን የህዝብ አለኝታነታችንን ወድቀደምው ተቃውሞ ትግላችን መመለስ ይኖርብናል::ወደ መንግስት ካዝና የሚገቡ ማናችውንም ዳርዳታና ድጋፍ ማቆምና በተለያዩ መንገዶች እንደ ቀድሞው ለወገናችን ድጋፉን ብቻ እናድርግ!!
    እግዚአብሔር በግፍ በወያኔ ስለባ ሆነው ደማችው የፈስስው ወገኖቻች እንድሁም ለወገናቸው ለመታደግ መስዋእት የሆኑትን ሁሉ ነብስ ይጠብቅልን!
    ኢትዮጵያን ይባርክ!

  3. Ato Gelaw,

    As much as Abiy is a traitor and a liar, you are an opportunist and knee kisser too. This what you said just a week ago on your face book because you saw one building that contains his Medemer book.

    “ከዛሬ ባሻገር መጪውን ትውልድ በመልካም መንገድ የመቅረጽ ራዕይ ሲኖርህ እንደ አብይ አህመድ ታላቅና ዘመናዊ ቤተ መጻህፍት አስገንብተህ ታስመርቃለህ።
    እንደ ህወሃት መሪዎች ስትዝግና ስትቀነጭር በህዝብ ትግል ተንኮታኩቶ የወደቀን አንባገነናዊ የበላይነትህን ለማስመለስ ጦርነት ጭረህ ህዝብና አገርን በጥፋትና እልቂት ወደ ድንጋይ ዘመን ልትመልስ ትሟሟታለህ።
    ኢትዮጵያ ወደ ፊት እንድትራመድ የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ ያላቸው ግሳንግሶች መንገድ መልቀቅ አለባቸው።
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጄክት የመቅረጽና የማስፈጸም አቅማቸው በጣም የሚደነቅ ነው።”

  4. አቤ ምንም እንኳን አሁንም moderate ቢሆን እስከ ዛሬ ከጻፍከው በጣም ይሻላል እኛ ከጅምሩ ስላወቅነው ተሰብስበን ነበር። አጣዬና ሻሸመኔ በቁማቸው ሲነዱ በየቀኑ በአማካይ 50 አማራ ሲገደል ኢትዮጵያ ማለት ኦሮሚያ ሲሆን ሳይጮህ ዛሬ ስብሀት ተፈታ ብሎ ማላዘን ብዙም
    አይፈይድም።ወጣት ህወአቶች (አርከበ እቁባይ አብረሀምን መከላከያ ሚኒስቴር ሲያደርገው……ከኦሮሙማም እንዲሁ አዳንች አቤቤ ታየ ደንዳ ሽመልስ አብዲሳ አባ ዱላ ሁለቱ ሌንጮዎችና ስፍር ቁጥር የሌላቹው አላዋቂዎች እንኳንስ ለኢትዮጵያ ኦሮሙማ ለሚባለውም ክልል አይበጁም ብሎ መጮህ በተገባ ነበር። ለማንኛውም ያንተ ከፍለን የማንጨርሰው ውለታ አለብን ያንን አጋንንት በሀያል ብርቱ ድምጽህ ገላገልኸን የተሻለ ባይሆንም ስርአቱን የለወጥከው አንተ ነህ ብሎ ማለት ያስችላል።

  5. አበበ አበበ አበበ ??????
    1- ለመሆኑ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም በቋንቋ እና በማንነት አጥር ውስጥ የተመሠረተ እና ማንም ሊለውጠው ሊሠርዘው በማይችል ፋሺሽታዊ ህገ መንግሥት ላይ የመሠረተ መሆኑን እና በመሆኑም የሰው ዘር ( አማራ ጠል ተደርጎ) የተፃፈ መሆኑን በዚህም አማራን እንደ ቱትሲ እንደ የመን አረብ እንደ ዮጎዝላዢያ እንደ አልቤኒያ በሚሊየኖች ለመጠፍጨፍ እና ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተረኛነት የሚመራ ቡድን የሃገር መሪ መሆኑን ሳትረዳው ቀርተህ አይመስለኝም እኔ ሆዴን ከሞላሁ ምን አገባኝ በሚል የድርጊቱ ተባባሪ ለመሆን መርጠህ ለመሆኑ ብዙ ማሳያ አለን ህዝብ ያውቃል።
    2- ህግን ጠቅሶ ሌቦችን ዘራፊዎችን ጨፍጫፊዎችን ተገንጣዮችን የሃገር እና የህዝብ ደህንነትን እና መንግሥትን በሃይል ለመደምሰስ አቅደው ተደራጅተው ስልጠና ሠጥተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን በቁጥጥር ሥር አድርገን ወንጀላቸው በህግ ተይዟል ያለን እና የዘላበደ አብይ ነው። ከሥልጣን ሲባረሩም የዘረፋትን እንዲበሉ በምህረት ወደ ተነሱበት የሸኛቸው አብይ ነው።እንደገና በሺ የሚቆጠሩ የሠሠራዊት አባላትን ባስጨፈጨፈው ጦርነት ተካፋይ ሆነው አገኘኋቸው ያለው አብይ ነው።
    3- አብይ ደንበኛው የዘመናችን ዲክታተር ተምሳሌ ለመሆኑ ዲክታተር ለህዝብ ክብር ስለሌለው በውሸት አዎቂ በመምሰል ከህግ በላይ ሆኖ ህግን ጥሶ ጨፍጫፊዎችን በምህረት ለቅቆ እኔ በመፈታቸው አላውቅም ነበር ደንግጬአለሁ ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ያዎረደ የውሸት ምንጭ ነው።አብይን ህዝቡ ታግሎ በመንቀል ምንጩን ካላስቆመ ህዝብ ለመዎረድ ፈቅዷል ማለት ነው።
    4- በወለጋ በአርሲ በባሌ በሻሸመኔ በሲዳሞ በቤንሻጉል በአዲስ አበባ ዙሪያ በአብይ ሥልጣን ዘመን በእየለቱ የታረዱት በጎጆአቸው ታጉረው በእሳት የተፈጁትን በጥይት የተፈጁትን በረሃብ በበሽታ ያለቁት በሃሰት የአኖሌ ጦርነት ማካካሻ የሆኑትን እና ዛሬም በመፈጀት ላይ ያሉ በአማራ እና በአፋር ያስጨፈጨፈው ህዝብ ማን ይፋረድ ????
    አበበ አበበ አበበ የጅምላን ጭፍጨፋ ያስፈፀመ የፈፀመ የደገፈ ሁሉም እኩል በህግ ይጠየቃሉ።በመሆኑም ይህ በጉልበት በተረኝነት የተነጠቀውን ሥልጣን ደግፋችሁ አብራችሁ ያስፈፀማችሁትን ማንም በይቅርታ የሚተዎችሁ የለም የጊዜ ጉዳይ ነው።

  6. አባቶቻችን የአዋቂ ስህተት ጋራ ያህላል ይሉ ነበር : ዛሬም የጠቅላይ ምንስትር አብይ ስህተት ከተራራ ገዝፎ ታይቷል : ይህም ልክ አለመሆናቸውን እያወቁ ጫን ያለ ስህተት መሥራታቸው ነው :: የጠቅላይ ምንስትሩና በጥቅሉ የኢትዮጵያ መንግሥት የተንዛዛና የተደጋገመ ስህተት ለዚህ ግዙፍ የፍትህ ጉድለት ወይም እጦት አድርሶናል :: ህውሃት እንደድርጅት የጀርመኑ ናዚ ፖርቲ በአውሮፖና ብሎም በአለም ያደረሰው እልቅትና ፍጅት የናዚ ፓርቲ በህግ እንዲታገድ ከመደረጉም በላይ ወንጀል የፈፀሙ አባላቱ እስከ አሁን ድረስ እየታደኑ በየደረሱበት እየተያዙ ለፍርድ በመቅረብ ላይ ናቸው : : ህውሃት የከናዚ ፖርት በባዕዳን/የጀርመን ዜጋ ባልሆኑት ላይ ከፈፀመው ወንጀል የሚስተካከል ወንጀል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፈፅሞ እያለ በህግ ለዘለዓለም አልታገደም ንብረቱም አልተወረሰም : እነ ስብሃት ነጋ አሁን ሊረከቡት ነው ይባላል ::
    ለማሳጠር ያህል ይህ ጠቅላይ ምንስትር ባዶ ዲስኩሩን እንዲያቆምልንና በህግና በግልፅ : ሥራ አስፈፃሚውን እያሳተፉ ጦርነቱን እንዲመሩ ልጠይቅ እወዳለሁ :: ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!

  7. We know what you guys are crying for;. And it’s clear that you Nefitegnas prefer to die than to see a free man Jawar Mohammed walking out free.
    You like or not Jawar Mohammed is going to be he best leader of Ethnically federated Republic of Ethiopia and don’t forget that there would be a new neighboring country called the Republic of Tigray!!
    Get used it criminal dummies.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share