ያልተገራ ምላስ የክፉ መንፈስ አንደበት ነው። ቃል ተግባር ይሆናል፤ የተንኮል ቃል ደግሞ ደም ያፋሳሳል፤ ንብረት ያወድማል፤ የጃዋርን ተክብቢያለሁ ያስታዉሷል። ቃሉ አንድ ነው እርኩስ መንፈስ የተጫነው በመሆኑ ለአያሌ ሰወች እልቂት ምክንያትት ነበር። ከጉራፈርዳ፤ አርባጉጉ እስካሁኗ ሰአት ያለው የሰው ልጆች ሞትና ስደት ያልተገራ ምላስ ውጤት ነው። ያልተገራ ምላስ ቋንቋ አለማወቅ አይደለም፤ ክፋት፤ ጠላትነት፤ ተንኮል ነው። በውስጥ ያለን የልብ ቁስል ወደውጭ ማስወጫ የአንደበት ተጠሪ ነው። ችግሩ ከተፈጥሯዊው የሰውነት አካል ከምላሱ ላይ አይደለም። ችግሩ ያለው ከአስተሳሰቡ ነው፤ ከክፋቱ ነው። በእንግሊዝኛው malice የሚሉትን እመርጣለሁ፣ “the term malice is defined as ‘having an intent to harm’ and is usually associated with printed or spoken words that defame someone’s character, accuse them falsley or to cause