April 16, 2022
34 mins read

የዐማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል ርዕዮታዊ ዘርፍ – መስፍን አረጋ

ባለም ላይ ሁለት ኃይሎች አሉ፣ ሰይፍና መንፈስ፤ የመጨረሻው ድል ደግሞ ሁልጊዜም የመንፈስ ነው”

“There are only two forces in the world, the sword and the spirit. In the long run the sword will always be conquered by the spirit ” (Napoleon Bonaparte)

——————————

የአማራ ሕዝብ ሕልውና ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ማለት ያዋጁን በጆሮ ነው፡  እጅጉን አንጀት የሚያቆስለው ደግሞ የአማራን ሕዝብ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ ያስገባው የአማራ ሕዝብ አቅፎና ደግፎ ስልጣን ላይ ያወጣውና ስልጣኑን ያረጋጋለት ዐብይ አሕመድ ዐሊ መሆኑ ነው፡፡  ዐበይ አሕመድ ማለት ዳግመኛ እንዳያቆጠቁጥ ተደርጎ ካልተነቀለ በስተቀር አማራን ጨርሶ ገድሎ የሚያጠፋ ነቀርሳ ማለት ነው፡፡  ይህ አማራ ገዳይ ነቀርሳ ስልጣን ላይ እየቆየባት ያለቸው እያንዳንዷ ሰዓት የአማራን ሕልውና ፍጻሜ ይበልጥና ይበልጥ ታቃርበዋለች፣ እያቃረበችውም ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን መታደግ የሚችለው ነቀርሳውን ዐብይ አሕመድን እንደምንም ብሎ ባስቸኳይ መንግሎ ከጣለው ብቻና ብቻ ነው፡፡

ዐብይ አሕመድን መመንገል ግን ለአማራ ሕዝብ ፋታ ይሰጠዋል እንጅ የሕልውና አደጋውን ጨርሶ አያስወግድለትም፡፡  ዐብይ አሕመድን የመሰለ ፀራማራ ነቀርሳ የሚጠመቅበት ጋን እስካልተሰበረ ድረስ፣ አንዱ አተላ ሲደፋ ሌላው ይጠነሰሳል፡፡  ፀራማራ ነቀርሳ የሚጠመቅበት ጋን የሚሰባበረው ደግሞ በአካላዊ ትግል ሳይሆን በርዕዮታዊ ትግል ነው፡፡

የአካላዊ ትግል ዓላማ አስፈለጊውን መስዋዕትነት በመክፈል የወያኔንና የኦነግን ፀራማራ አረሞች መነቃቀል ሲሆን፣ ሁሉም አማራ ፋኖ ሁሉም ፋኖ አማራ መሆንን ይጠይቃል፡፡  የርዕዮታዊ ትግል ዓላማ ደግሞ የወያኔና የኦነግ ፀራማራ አረሞች የሚበቅሉባቸውን ማሳወች እንዳያበቅሉ ለማድረግ አስፈላጊውን ፀራረም እንዳስፈላጊነቱ በየጊዜው መርጨት ነው፡፡  ስለዚህም አብዛኛው ፀራማራ ዐረም የሚጠፋው በርዕዮታዊ ትግል ሲሆን፣ ከርዕዮታዊ ትግል የሚያመልጠው ደግሞ በአካላዊ ትግል ይነቀላል፡፡  በሌላ አባባል ርዕዮታዊ ትግል አካላዊን ትግል ቀላል ያደርገዋል፡፡  አብዛኛው ዐረም ገና ሳይበቅል በርዕዮታዊ ትግል ከተቀጨ፣ አልፎ አልፎ እዚህም እዚያም የሚበቅሉትን ዐረሞች ብቅ ባሉ ቁጥር በአካላዊ ትግል መንቀል እጅግም አያስቸግርም፡፡

የርዕዮታዊ ትግል ዋና ጥቅም ደግሞ የውጤቱ ዘላቂነት አስተማማኝ ከመሆኑም በላይ እንደ አካላዊ ትግል ድርጅት ወይም መሪ የማያስፈልገው መሆኑ ነው፡፡  ድርጅትና መሪ የማያስፈልገው በመሆኑ ደግሞ የወያኔና የኦነግ ሰርጎ ገቦቸ ወይም ቅጥረኞች ሊያዳክሙት ወይም ደግሞ ጭራሹን ሊያኮላሹት አይችሉም፡፡  በዚህ ረገድ ሲታይ ርዕዮታዊ ትግል እንደ መንፈሳዊ ትግል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፣ በሥጋ ላይ ሳይሆን በመንፈስ ላይ የሚደረግ ትግል ነውና፡፡  በሌላ አንጻር ደግሞ ርዕዮታዊ ትግል እከሌ የሚባል ድርጅት ወይም መሪ የሌለውና የማያስፈልገው የቤታደር እምቢተኝነት (civil disobedience) አካል ተደርጎም ሊወሰድ ይችላል፡፡

የአማራ ሕልውና ትግል ርዕዮታዊ ዘርፍ አያሌ ንዑስ ዘርፎች እንደሚኖሩት እሙን ነው፡፡  በኔ በመስፍን አረጋ ዕይታ ግን ዋናወቹ ንዑስ ዘርፎች ሦስት ሲሆኑ፣ እነሱም የቦታወችን ስያሜወች የሚመለከቱ፣ የግለሰቦችን ስያሜወች የሚመለከቱና የጠላትን ስያሜወች የሚመለከቱ ናቸው፡፡  ስለነዚህ ንዑስ ዘርፎች ከማውሳቴ በፊት ግን ንዑስ ዘርፎቹ በይበልጥ ስለሚያተኩሩባቸው ስለ ኦነጋውያን ጥቂት ልበል፡፡

ያለፈውን ታሪካችንን ለትምህርት ብቻ ተጠቅመንበት፣ ወይም ደግሞ ውሾን ያነሳ ውሾ በማለት ከናካቴው ረስትነው፣ ተከባብረን በሰላም እየኖርን አገራችንን እናስከበር ቢባሉ፣ አነጋውያን አሻፈረኝ ብለዋል፡፡  ወያኔ አማራንና ኢትዮጵያን ጎዳሁ ብሎ የከለላቸው በምንም መስፈርት ለነሱ የማይገባቸው ግዙፍ ክልል አልበቃ ብሏቸው ቤንሻንጉል ኬኛ፣ወሎ ኬኛ እያሉ ከመደስኮር አልፈው ወደ መተግበር ተሸጋግረዋል፡፡  በዚህም አላቆም ብለው ሚንጃርን ተመኝተዋል፡፡

 

ለመማማር ሳይሆን ለመቁጠር አበሳ

ያለፈው መከራ ቢጠቀስ ቢወሳ

ለምንም የማይበጅ ስለሆነ ሆሳ፣

ውሻ ይሁን ብለን ውሾችን ያነሳ

ሆድ ይፍጀው ብንልም የሉባን ጠባሳ፣

ኦነጋውያን ግን ያማራ ሕዝብ አሁን

ተዳክሟል በማለት እንደ ግራኝ ዘመን፣

የሉባን ወረራ ጀምረው እንዳዲስ

ተመኙ ለመግፋት እስከ ጣና ድረስ፡፡

 

ግማሽ ምዕተ ዓመት በሚበልጠው የእድሜ ዘመኑ ጨለማን ተገን አድርጎ ሕጻናትን፣ ሴቶችንና አረጋውያንን ከማረድ በስቀር፣ በታሪኩ አንድም ጊዜ ቢሆን ድል ማድረግ ይቅርና በቅጡ ተዋግቶ የማያውቀው ኦነግ፣ የአማራን ፋኖ አማራ ክልል ገብቸ እደመስሳለሁ እያለ መፎከር ጀምሯል፡፡  ባጭሩ ለመናገር ኦነጋውያን ከወያኔ የቀን ጅብ እጅግ የከፉ የቀትር ጅብ ሁነው አልጠግብ ብለዋል፡፡  አልጠግብ ያለ ደግሞ መትፋት ግዴታው ነው፡፡  የአማራ የሕልውና ትግል ርዕዮታዊ ዘርፍ ዋና ዓላማ ደግሞ አልጠግብ ያለውን የኦነግን የቀትር ጅብ በማስተፋት ጥጋቡን ለማብረድ ያንበሳውን ሚና መጫወት ነው፡፡  ኦነጋውያን ጎጃምን ሲመኙ ቢዛምን (ወለጋን) እንዲያጡ ማድረግ ነው፡፡

 

ሸኔም አሉት ኦነግ፣ ቄሮም አሉት ፎሌ

በድንገት አደጋ ጥሎ በቀበሌ

ከመግደል በስተቀር ሕፃን ሽማግሌ፣

ፊት ለፊት ተፋልሞ ከሚባል እገሌ

ተቆጣጥሮ እማያቅ አንዲትም ቀበሌ

እዚህ ግባ እማይሉት ነበረ አልባሌ፡፡

 

ዛሬ ግን ገነነ እድሜ ለትሕነግ

ያምደጽዮን ርስት ነው ብሎ የኦነግ

ኦሮምያ ብሎት ባገር ስም ማዕረግ

ስላመቻቸለት ያሻውን እንዲያደርግ፡፡

 

ግራኝ እያጸዳ ወደፊት ሲያመራ

እሱ ተከትሎ የከብቶችን ጭራ

የሰፈረበትን የሐበሻን ስፍራ

ፊንፊኔ፣ ጉለሌ ብሎ ስለጠራ

የራሱ አስመስሎ ኬኛ ብሎ ኮራ

አማራ ይውጣ አለ ካማራ በራራ፡፡

 

የቦታ ስሞችን የተመለከተ ርዕዮታዊ ትግል

በመጀመርያ ቃል ነበር፣ ቃልም ሥጋ ሆነ ይላል ክቡር መጽሐፍ፡፡  ማናቸውም ነገር በመጀመርያ የሚፀነሰው ናላ (mind) ላይ ነው፡፡  ናላ ላይ ተጸንሶ ይረገዝና ሥጋ ለመልበስ ምድር ላይ ይወርዳል፡፡  ኦነጋውያን የሌለ ትርክት ፈጥረው፣ ወራሪውን ኦሮሞ ተወራሪ፣ ተወራሪውን አማራ ደግሞ ወራሪና መጤ አድርገው ሙሐመድ ሐሰንን በመሰሉ ምሁር አስተኔወች (pseudo-intellectuals) የውሸት ትርክት ሲተርኩ፣ እነዚህ ወሸታሞች የት ይደርሳሉ ብለን ንቀን ተውናቸው፡፡  እነሱ ግን የኛን ንቀት ንቀው ውሸታቸውን እየደጋገሙ ዐብይ አሕመድን በመሳሰሉ መንጋወቻቸው ላይ መዝራታቸውን ቀጠሉ፡፡  እነ ዐብይ አሕመድም እነሆ በመደጋገም የተዘራባቸውን የነ ሙሐመድ ሐሰንን ውሸት ውነት ለማድረግ ተቃረቡ፡፡

ስለዚህም፣ የአማራ ሕልውና ርዕዮታዊ ትግል አንዱና ዋናው ዘርፍ ኦነጋውያን ለፀራማራ ትርክታቸው የሚጠቀሙባቸውን ቃሎች የአማራ ሕዝብ ከቋንቋው ውስጥ አንድ ባንድ እየነቀሰ አውጥቶ እንዲያስወግዳቸው ማድረግ ነው፡፡  ወሎ፣ ከሚሴ፣ ቢሸፍቱ፣ አዳማ፣ ፊንፊኔ፣ አሩሲ፣ ወለጋ የመሳሰሉት የግራኝን ዱካ ተከትሎ ከተከናወነ ጭፍጨፋ በኋላ የተፈጠሩ ቃሎች ከአማራ ሕዝብ አንደበት ላንዴና ለኻቹ መፋቅ አለባቸው፡፡  ከሚሴ፣ ወረምንትሴ፣ ወረቅብጥርሴ፣ ጉለሌ፣ ሰላሌ፣ ባሌ የመሳሰሉት ቃሎች አንዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉም ቆሸ ተጥለው በቀድሞወቹ ትክክለኛ ቃሎች መተካት አለባቸው፡፡

ለአማራ ሕልውና ይበልጥ የሚያሰጉት እነዚህ ኦነጋዊ ቃሎች እንጅ ውጊያ የማያውቀው፣ ቱሪናፋው የኦነግ ሠራዊት ስላልሆነ፣  ካሁን በኋላ ለሕልውናው የሚያስብ ማናቸውም አማራ እነዚህን ኦነጋዊ ቃሎች መቸም ቢሆን መጠቀም የለበትም፡፡  የአማራ ልጆችም እነዚህን የጨፍጭፎ ተስፋፊ ቃሎች እንዳይጠቀሙ ብቻ ሳይሆን እንዲጸየፏቸው መማር አለባቸው፡፡

በተለይም ደግሞ ወሎ ለሚባለው የአማራን ሕልውና ለማክሰም ኦነጋውያን በስፋት ለሚጠቀሙበት ቃል ከፍተኛ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡  ይህ ኦነጋዊ ቃል ቤታማራን የተካ ትናንት መጤ ቃል ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ይህን መጤ ቃል መጤነቱን እያወቀ በጸጋ ቢቀበለውም፣ ኦነጋውያን ግን አማራን ለመግደያነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡  ስለዚህም፣ ከራስ በላይ ንፋስ ነውና፣ የአማራ ሕዝብ በመጤ ቃል ሰበብ ከሚገደል ይልቅ ቃሉን መግደል አለበት፡፡

አንድን ላኮመልዜ (የላኮመልዛ ሰው) እራሱ እስካልፈለገ ድረስ ወሎየ ነኝ እንዲል ማንም ሊያስገድደው አይችልም፡፡  እሱ በማይፈልገው ስም ወሎየ ብሎ የሚጠራውን ኦነጋዊ ደግሞ እሱንም አምርሮ በሚጠላው ስም በመጥራት አጸፋውን መመለስ አለበት፡፡  አማራዊ ሚዲያወችም ወሎ የሚባለውን ኦነጋውያን ለእኩይ ተግባር የሚገለገሉበትን ቃል መጠቀም የለባቸውም፡፡  ማናቸውም ኦነጋዊ አውሮጳ ወይም አሜሪቃ ሲገባ ኢትዮጵያዊ ነህ ብለው ሲጠይቁት ኦሮሞ ነኝ እንደሚል ሁሉ፣ ላኮመልዜም ወሎየ ነህ ብለው ሲጠይቁት ላኮመልዜ ነኝ ብሎ መመለስ አለበት፡፡  ወሎ የሚለውን ቃል አማራ ካልተጠቀመበት፣ ካማረኛ ይጠፋል፡፡  ቃሉ ከጠፋ ደግሞ መዘዙም አብሮ ይጠፋል፣ ቃል ይቀትላልና፡፡  ሌሎችም የተስፋፊ ቃሎች እንደዚሁ፡፡

በኦሮሞ ወራሪ ስማቸው የተቀየረው፣ በድፍን ጦቢያ ላይ የሚገኙት የሁሉም ጦቢያ ቦታወች የቀድሞ ስም ዝርዝር ዜናሁ ለጋላን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቶ በቅረቡ እንደሚለቀቅ ተስፋ ይደረጋል፡፡  ኦነጋውያን የቆጡን ለማውረድ ሲሯሯጡ የብብታቸውን የሚጥሉበት ቀን ሩቅ አይሆንም፡፡

 

ዜናሁ ለጋላን አንብቦ ባርምሞ

የኦሮሞን ታሪክ ያጠና ገምግሞ፣

የሚከተለውን በእርግጥ ደምድሞ

መናገር ይችላል አደባባይ ቁሞ፡፡

 

የሉባው ሠራዊት የገዳው ኦሮሞ

ሐበሻን ሲያገኘው በግራኝ ተዳክሞ

ጨለማ ተላብሶ እያረደ አጋድሞ፣

ባበሻ ምድር ላይ በያቅጣጫው ተሞ

የተንሰራፋ ነው እንደ አረማሞ፡፡

 

በጦቢያ ምድር ላይ ከጣና እስከ ጫሞ

በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ

ከመስፋፋት በፊት ሁሉም አስቀድሞ

አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡

 

የኦነግ ሠራዊት የቆጡን ለማውረድ አጣየ ሲመጣ

መገንዘብ አለበት የብብቱን ነቀምት ሊችል እንደሚያጣ፡፡

 

ወያኔም ሲጣደፍ ሑመራን ሊበላ

ተንቤንን ይተፋል አቀርሽቶ  አመቡላ፡፡

 

አማራ እንደሚለው በድንቅ ተረቱ

ብዙ ቢዘገይም ቢሞላም ሺ ዓመቱ

ፍትሕ ባገር ሲነግስ ሲደርስ ሰዓቱ

ርሰት ይመለሳል ለሕግ ባለቤቱ፡፡

 

አሩሲና ከፋ፣ ወሎና ወለጋ

ፋኖ ከፍሎላቸው ንፁሕ የደም ዋጋ

ቀን ሲወጣላቸው ጨለማው ሲነጋ

በቀድሞ ስማቸው ይለብሳሉ ጸጋ፡፡

 

የግለሰብ ስሞችን የተመለከተ ርዕዮታዊ ትግል

ቀንደኛው ኦነጋዊ የቢዛሙ (የወለጋው) ዮሐንስ ለታ፣ ዮሐንስ ጥሎ ሌንጮን አንስቶ ሌንጮ ለታ ተብሏል፡፡  ማንነቱን በትክክል ቢያውቅ ኖሮ ግን መጣል የነበረበት ዮሐንስን ሳይሆን ለታን ነበር፡፡  ለዚህ የተዳረገው ደግሞ ከሸዌ፣ ከላኮመልዜ ወይም ከጎጃሜ ጋር እንጅ ከቦረኔ ጋር ምንም ዝምድና እንደሌለው ወዘናውን አይቶ መናገር የሚቻለውን ጉልህ ሐቅ ከልጅነቱ ጀምሮ የሚያስተምረው በማጣቱ ነው፡፡  ኦሮሞ ከሚባለው ውስጥ ዘጠና በመቶው የጉዲፈቻና የሙጋሳ ውጤት የሆነ ገርባ እንጅ በደሙ ኦሮሞ አለመሆኑን እውነተኞቹ ኦሮሞወች በግልጽ የሚመሰክሩት ሐቅ ነው፡፡

ስለዚህም የአማራ ሕልውና ርዕዮታዊ ትግል ሁለተኛው ዘርፍ ቂጢሳ፣ ጭብሳ የሚሉ ስሞች ስለተለጠፉበት ብቻ ኦሮሞነኝ ብሎ የሚያስብን በብዙ ሚሊዮኖች የሚቀጠር ሕዝብ ኦሮሞ አለመሆኑን በማስተማር ማሳመንና በራሱ ተነሳሽነት ቂጢሳን ከስሙ እንዲቀነጥስ ማድረግ ነው፡፡

 

በስሙ ኦሮሞ ከሆነው ሕዝብ ላይ

ዘጠና በመቶ ወይም ከዚያ በላይ

በደሙ ያይደለ ብሔሩን የረሳ

ወይ ጉዲፈቻ ነው አለያም ሞጋሳ፡፡

 

አንዳርጋቸው ብሎ ቢከተል ቂጢሳ

ቂጢሳን ከማለት የኦሮሞ ጎሳ

ማለት ያመዝናል ነበረ ሞጋሳ፡፡

 

ከወለጋ ኗሪ አንዱን ለናሙና

ወይም ከአሩሲ አንዱን በደፈና

በመመልከት ብቻ የደሙን ወዘና

ምንም እንደሌለው ከወደ ቦረና

መናገር ይቻላል በሙሉ ልቦና፡፡

 

ሽመልስ አብዲሳ ያልተገራው ስዱ

ነፍጠኛን ሰበርነው ሲል እንደልማዱ፣

የቦረና ውልዱ ሳለ የምጣዱ

አትንጣጣ በሉት አንተ የሰፌዱ፡፡

 

ዲኔግዴ፣ ጉበና ቢቂላ ወይ ባልቻ

ኦሮሞ እሚባለው በስያሜው ብቻ

አብዛኛው ቢታይ በደም መመልከቻ

ወላጆቹ ታርደው በሜንጫ ዘመቻ

የተለወጠ ነው ወደ ጉዲፈቻ፡፡

 

በስሙ ቢባልም ኤጀርሳ፣ ኤለሞ

በደሙ ያልሆነ ሐበሻና ጋሞ

እንዲሁም ወላይታ፣ ሐድያ፣ ሲዳሞ

እስኪ ተናገሩ የቱ ነው ኦሮሞ?

 

የሕልውና ጠላትን ስያሜ የተመለከተ ርዕዮታዊ ትግል

የሕልውና ጠላት ማለት የሞት ሽረት ጠላት ማለት ነው፡፡  የሕልውና ጠላትህን ወይ አንተ ታጠፋዋለህ፣ አንተ ካላጠፋኸው ደግሞ እሱ ያጠፋኻል፡፡  በሌላ አባባል፣ የሕልውና ጠላት ማለት ከማጥፋት ወይም ከመጥፋት ውጭ ሌላ አማራጭ የማይሰጥህ ጠላት ማለት ነው፡፡  ስለዚህም የሕልውና ጠላት ጭራቅ ብቻ ሳይሆን የጭራቆች ጭራቅ ነው፡፡

ኦነግና ወያኔ የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ የሕልውና ጠላታቸው አድርገው በይፋ ፈርጀውታል፡፡  በዚህ ፍረጃቸው መሠረት፣ የአማራን ሕዝብ ጭራቅ አድርገው በመሳል፣ ሠራዊታቸው በአማራ ሕዝብ ላይ ሲዘምት የሚዘምተው  በሰው ላይ  ሳይሆን በጭራቅ ላይ እንደሆነ፣ የሚገድለው ሰውን ሳይሆን ጭራቅን እንደሆነ በማስተማር፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ማናቸውንም ዓይነት ጭካኔ ቢፈጽሙ ምንም ዓይነት የህሊና ወቀሳ እንዳይሰማው ለማድረግ ብዙ ርቀት ሂደዋል፡፡  ጥረታቸው ምናልባትም ካሰቡት በላይ ስኬታማ እንደሆነ ደግሞ በቢዛም (ወለጋ)፣ በመተከልና በወልቃይት ላይ በተግባር ታይቷል፣ እየታየም ነው፡፡

የኦነግ ወንበዴወች አማራ ሲያርዱ ምንም አይሰማቸውም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት የሚያርዱት ሰው ሳይሆን አማራ ነውና፡፡  የኦነግ ሽፍቶች የአማራን ሕጻናት ጎጆ ውስጥ ሰብስበው ሲያንጨረጭሩ ምንም አዘኔታ አይሰማቸውም፣  ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት የሚያንጨረጭሩት ሕጻናትን ሳይሆን የአማራ ሕጻናትን ነውና፡፡  የኦነግ ቄሮወች ከአማራ አስከሬኖች በተቆረጡ እጆና እግሮች ሲጨፍሩ ደስታውን አይችሉትም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት እነዚህ እጆችና እግሮች የሰው ሳይሆኑ የአማራ እጆችና እግሮች ናቸውና፡፡  የኦነግ አክራሪወች የአማራ ሬሳወችን በሞተር ሳይክል ሲገትቱ ምንም አይሰቀጥጣቸውም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት ሬሳወቹ የሰው ሳይሆኑ የአማራ ናቸውና፡፡  የኦነግ ታጣቂወች የአማራ ነፍሰጡሮችን ማሕጸኖች ሲዘረክቱ ድሪቶ የቀደዱ አይመስላቸውም፣ ምክኒያቱም በነሱ እይታ መሠረት የሚዘረክቱት የሰው ነፍሰጡሮችን ሳይሆን፣ የአማራ ነፍሰጡሮችን ነውና፡፡

የኦነግን የፈጠራ ትርክት እየተጋተ ወዳደገው ወደ ቀንደኛው ኦነጋዊ ወንበዴ ወደ ዐብይ አሕመድ ስንዞር ደግሞ አማሮች ላይ የሚካሄደው ዘግናኝ ጨፍጨፋ ለዚህ ወንበዴ ዴንታ አይሰጠውም፣ ምክኒያቱም በሱ እይታ መሠረት የሚጨፈጨፉት ሰወች ሳይሆኑ አማሮች ናቸውና፡፡  ለዚህ ነው ባማራ መጨፍጨፍ ማዘኑን ለይምሰል ያህል እንኳን አንድም ጊዜ ያልገለጸው፡፡  በተቃራኒው ግን አማራ በተጨፈጨፈ ዕለት ወይም ማግስት ሕንጻ እየመረቀ ወይም አበባ እየተከለ በጭፍጨፋው መደሰቱን በተግባር ይናገራል፣ በአማራ ሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት ይሰዳል፣ ጨው ይነሰንሳል፡፡

ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በምን ዓይን እንደሚመለከተው ፍንትው አድርጋ የምታሳየው፣ አማራን የሚጨፈጭፈውን የኦነግን ሠራዊት የወለጋ አርሶ አደሮች ለምን ይደግፉታል ብለን መጠየቅ አለብን በማለት በፓርላማ ውስጥ እንደዋዛ ጣል ያደረጋት ዐረፍተ ነገር ናት፡፡  በዚች ንግግሩ ዐብይ አሕመድ ለማለት የፈለገው የአማራ ሕዝብ በዘግናኝ ሁኔታ በኦሮምያና በመከተል የሚጨፈጨፈው፣ በዘግናኝ ሁኔታ እንዲጨፈጨፍ የሚያበቁትን ወንጀሎች ስለሠራ ነው ነው፡፡  በሌላ አባባል በዐብይ አሕመድ እሳቤ መሠረት ኦነጋውያን አማራን የሚጨፈጨፉት ምክኒያት ስላላቸው ስለሆነ፣ ጥፋተኞቹ ተጨፍጫፊወቹ እንጅ ጨፍጫፊወቹ አይደሉም፡፡

የትግሬና የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት አይደለም፡፡  ስብሐት ነጋና ወያኔወች፣ ዐብይ አሕመድና ኦነጋውያን ግን የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ናቸው፡፡  የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች መሆናቸውን ደግሞ አለመካድ ብቻ ሳይሆን ይኮሩበታል፡፡  የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ስለሆኑ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ ጭራቆች ናቸው፡፡  ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው ሲል፣ ስብሐት ነጋንና ወያኔወችን፣ ዐብይ አሕመድንና ኦነጋውያንን መሰየምና መጥራት ያለበት በጭራቃዊ ባሕሪያቸው ነው፡፡  ጨርቅ ለማድረግ ቆርጠህ የምትነሰው በጭራቅነት የፈረጅከውን ብቻ ነው፡፡

ለአማራ ሕዝብ ሕልውና እንታገላለን የሚሉ ድርጅቶና ግለሰቦች፣ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት የሆነውን ጭራቁን ስብሐት ነጋን አቦይ ስብሐት የሚሉት ለምንድን ነው?  ስብሐት ነጋ ለአማራ ሕዝብ አባት የሆነው ከመቸ ወዲህ ነው?   የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት የሆነውን ስብሐትን ጭራቁ ስብሐት እያሉ እንጅ አባታችን ስብሐት እያሉ ከስብሐት ጋር የሞት ሽረት ትግል ማድረግ እንዴት ይቻላል?

በተመሳሳይ መንገድ ዐብይ አሕመድ ለአማራ ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን፣ የሕልውና ጠላት መሆኑን በዐራት ዓመት የስልጣን ዘመኑ በግልጽ አስመስክሯል፡፡  የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት ስለሆነ ደግሞ የአማራ ሕዝብ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ዶክተር፣ እሳቸው፣ እርስወ እያለ በክብር ሊጠራው አይገባም፣ በክብር የምትጠራውን በጽኑ አትታገለውምና፡፡

ስለዚህም የአማራን ሕልውና ለመታደግ ቁመናል የሚሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ዐብይ አሕመድን መጠራት ያለባቸው በመንበሩ ሳይሆን በግብሩ ነው፡፡  እነዚህ ድርጅቶችና ግለሰቦች እውነትም የአማራን ሕልውና ለመታደግ የሚታገሉ ከሆነ፣ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቱ የሆነውን ጭራቁን ዐብይ አሕመድን ዙርያ ጥምጥም ሳይሄድ ጭራቁ ዐብይ አሕመድ እያለ እየጠራው፣ በጭራቁ ላይ ሆ ብሎ እንዲነሳ መቀስቀስ አለባቸው፡፡  ጭራቁን ዐብይ አሕመድን ጭራቁ ወይም ፋሽስቱ ለማለት ድፍረት ካጡ ደግሞ በትክክለኛ ማዕረጉ የወያኔው ኮለኔል እያሉ መጥራት አለባቸው፡፡

በዚህ ረገድ ደግሞ ከራሳቸው ከኦነጋውያንና ከወያኔወች ትምህርት መውሰድ ይችላሉ፡፡  ወያኔና ኦነግ መንግስቱ ኃይለማርያምን ባማራነት ይፈርጁት ስለነበር፣ አንድም ቀን ሊቀመንበር መንግሰቱ ወይም ፕሬዜዳንት መንግስቱ ብለውት አያውቁም፡፡  ኮለኔል መንግስቱ ይሉት የነበረው ደግሞ በተዛዋሪ ጭራቅ ለማለት ነበር፡፡

የወያኔው ኮለኔል ዐብይ አሕመድ ደግሞ ባማራ ሕዝብ አንደበት አንቱ መባል የለበትም፡፡  እሱም ራሱ በአማራ ሕዝብ አንደበት መከበር አይፈልግም፡፡ አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ያበሳጨዋል፡፡  የአማራ ደም አለበት ተብሎ በኦነጋውያን እንደሚጠረጠር ስለሚያውቅ፣ እሱ የሚፈልገው የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ራሱ የአማራ ሕዝብ በግልጽ እንዲመሰክርለትና፣ በኦነጋውያን ዘንድ ሙሉ በሙሉ እንዲታመን ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ፋሽስት ሲለው ቀንደኛ ኦነጋዊነቱን እየመሰከረለት ስለሆነ ውስጥ ውስጡን ደስ ይለዋል፡፡  ሙሴ የሚሉትን አማሮች ቀን እየጠበቀ ተራ በተራ የሚያዋርዳቸውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡

በወያኔና በኦነግ ዘንድ ጨዋነትና ትሕትና የፈሪነት መግለጫወች ስለሆኑ፣ የአማራን ሕዝብ አስጠቁት እንጅ አላስከበሩትም፡፡  እየየም ሲደላ ነውና፣ ለሕልውናው የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ያለው የአማራ ሕዝብ እከሌ ይቀየማል፣ እነከሌ ቅር ይላቸዋል የሚለው ጉዳይ ቅንጣት ሊያሳስበው አይገባም፡፡  ከራስ በላይ ንፋስ ነውና፣ ሕልውናውን ለማስጠበቅ የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል የሚያስቀይመው ወይም ቅር የሚያሰኘው ካለ ገደል ይግባ፡፡  ጎጠኞች በጨዋ ቋንቋ ተደጋግሞ ሲነገራቸው ፈሪነትና መለማመጥ እየመሰላቸው አልሰማም አልለማም ስላሉ፣ ካሁን በኋላ መነገር ያለባቸው በሚገባቸው በግልጽ ቋንቋ ነው፡፡  በምክር አልመከርም ስላሉ በመከራ መመከር አለባቸው፡፡

 

ያማራ ሐለወት አደጋ ላይ ወድቆ

እየተቀበረ በማሽን ተዝቆ፣

ጽንፈኛ ኦሮሞ ጉቱም ሆነ ዋቆ

ይቀየማል ብሎ ማውራት ተጠንቅቆ

ትርፉ መዋረድ ነው ፈሪ አስብሎ አስንቆ፡፡

 

እየየም የሚባል ነውና ሲደላ

እየተሰየፉ እርጉዝና ጨቅላ

እየተቃጠሉ ሕጻናት በጅምላ

እየተሰደደ ሕዝብ በጠቅላላ

ትሕትና በቃ ከንግዲህ በኋላ፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop