April 14, 2022
7 mins read

ደፍቶ መካር ያጣላል ፤ የዕብድ ገላጋይ ዱላ ያቀብላል – ማላጂ

ከሰሞኑ  የኢህዴግ ከፍተኛ ማዕከላዊ አመራር መካከል ከዘመነ ኢህዴን/ ህወኃት  ቅድመ ዉህደት አስከ ድህረ ፍች ከፍተኛዉን የትግል ድርሻ የነበራቸዉን አመራሮች በህዝብ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸዉን አመራሮች በሰበብ አስባብ ማስወገድ የትህነግ /ኢህአዴግ የባህሪ መገለጫ ነዉ፡፡

ለዚህም ከጫካ ትግል ጀምሮ ስለተወሰዱ የማግለል እና የበደል ግፍ በኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ላይ የሆነዉ  ዛሬ ላይ በከፍተኛ የዓማራ ግዛት አመራሮች ላይ ስለሆነዉ ብርቅ አይደለም ብርቅ የሚሆነዉ እንደባለፉት የህዝብ ልጆችን በህዝብ ከለላ እና ዕዉቅና መስጠት የሆነ እንደሆነ ብቻ ነዉ ፡፡

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የፖለቲካ ስልጣንን በጉልተኝነት መያዝ እና ኢትዮጵያዊነትን መገዝገዝ ከኢህዴግ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅ ነዉ ፡፡

የመጀመሪያዉ የዓማራ ግዛት ሊቀመንበር ሙሉዓለም አበበ ፣ ዶ/ር አምባቸዉ መኮንን ፣ ፕ/ር አስራት፣ጀ/ል አሳምነዉ ፅጌ…..እንዲሞቱ የፈረደባቸዉ የእነርሱ ጠላት ሳይሆን የኢትዮጵያዉያን /ዓማራ እና የኢትዮጵያ ጠላት ነበር እና አሁን ከዚያ ዛሬ መማር ያለብን እኛ ኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ነዉ ፡፡

አበዉ ነጋሪየ ሰዳቤየ እንዲሉ የኢትዮጵያዊነትን ጥቃት የሚያማቸዉን እና የሚሰማቸዉን የሚገለፁ ሁሉ የየዘመናቱ የፖለቲካ ስርዓት ጠላት የሚፈረጁ ኢትዮጵያዉን የኢትዮጵያ የህዝብ ልጆች መሆናቸዉን ሳንዘገይ ልንገነዘብ ይገባል፡፡

ደፍቶ መካር የዕብድ ገላጋይ የኢትዮጵያ እና ህዝቦች ጠላት መሆናቸዉን በመገንዘብ እኛ ኢትዮጵያዉያን ለየትኛዉም ኢትዮጵያዊ አንድነት እና ልዕልና ለቆሙት ሁሉ ከለላ ፣ዕዉቅና እና ጥበቃ ሊደረግላቸዉ ይገባል፡፡

በዚህ ዘመን  ጥቃትን ፣ ዉርደትን እና ሞትን ይሁን ብሎ ማሳለፍ በቃ የሚባል እና ማንኛዉም ነፃነት እና መብት ከየትኛዉም አካል መጠየቅም ሆነ መጠበቅ ከታሪክ እና ከሞት አለመማር ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ ህዝብ ተቀምጦ የሚያከብረዉን ሆነ ቆሞ የሚንቀዉን የሚያዉቅ መሆኑ በስነ ቃል የሚገለፅ ሲሆን በተግባር መኖር አለመቻሉ ሁሉን አሜን ማለት ነዉ ፡፡

ዓሜን ለዕምነት እንጂ ለሞት እና ለዉርደት እንዳልሆነ ከእኛ ኢትዮጵያዉን በላይ ሊናገር፤ ሊመሰክር አይችልም ፡፡

በጠላት የሚነገረዉ ዕዉነት ፤ በወዳጂ የሚነገር ሀሰት ብሎ እንደ በበቀን መጮህ መቆም አለበት ፡፡ የኢትዮጵያዊነት አንድነት እና ታላቅነት ሽግግር ዕወቁንነት ከዓማራ ህዝብ የነቃ አንድነት ፣ ህብረት እና ተሳትፎነት ዉጭ ከጭንጫ ላይ ዘር መድፋት ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ ለኢትዮጵያዉያን ቀርቶ ለጠላት ጥበቃ እና ከለላ የመስጠት  አኩሪ የማንነት መገለጫ እንደመሆኑ ለዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊነት ዕዉነቱን ለህዝብ ለሚያድርሱ እና ላደረሱ በየትኛዉም ደረጃ ከየትኛዉም ለሆኑት ጥበቃ እና ከለላ መስጠት ብቻ ሳይሆን ከነሙሉ ጥቅማቸዉ እና ክብራቸዉ ዕዉቅና እና ክብር መስጠት አለበት ፡፡

ዛሬ ላይ ሆነን ከግማሽ ክ/ዘመናት በላይ ለህዝብ እና አገር ከፍተኛ ተጋድሎ ላደረጉት ኢትዮጵያዉያን ስማቸዉን ከመልካም ስራወቻቸዉ ጋር ዞትር በትዉልድ ቅብብሎሽ የሚወሱት በበበጎ ተግባራቸዉ መሆኑን ከዚህ በተቃራኒ የህዝብ እና የአገር አደራ ለግል ጥቅም እና የፖለቲካ ስልጣን ርስት ለማድረግ የተመኙት ሁሉ የጉም ሽታ ከመሆናቸዉ አልፎ መሪ የነበሩ ስለመሆናቸዉ እንኳ ከስልጣን መንበር ከወረዱ በኋላ ቀርቶ በፖለቲካ ስልጣን መንበር ሳሉ በራሳቸዉ  በህዝብ የተረሱ  ነበሩ ፤ አሉ ፡፡

ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ሆና እንድትቀጥል እንዲሁም ሁለንተናዊ ህልዉና ዕዉን እንዲሆን የምንመኝ ኢትዮጵያዊነት በተለይም ዓማራ መሆን ጠላት ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ለይኩን መሆኑን በአስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን በተግባር መተሳሰር እና መተባበር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ እና መሪር ዕዉነታ ነዉ ፡፡

ለዕዉነተኛ እና ዘላቂ ለዉጥ ከክፉ እና አድርባይ ልማድ መዳን አለብን ፡፡ በእንገሊዝኛ ስንረገም አሜን ፤ በግዕዝ ስንባረክ ለምን የምንል የመስሎ አደር ሰለባዎች ከተጫነን አባዜ መላቀቅ አለብን ፡፡

ደፍቶ መካር እና የገላጋይ ድንጋይ አቀባይ የሚሰማ የሚጠላህ ጠላት እንጂ ወዳጂ እንዳልሆነ ሠዉ ሆይ መታወቅ አለበት ፡፡ የህዝብ አጋር የሆኑትን ከህዝብ ለመነጠል መሞኮር የፖለቲካ ስልጣንን ዋሻ የማድረግ ይትባህል መሪዉን የሚንቅ አይነ ስዉር እንደሆነ ህዝብን የሚንቅ የህዝብ ልጆችን የሚንቅ ነዉ ፡፡ይህም መልዕክተኞችን የማይቀበል ላኪዉን የሚያገል መሆኑ ሳይታለም የሚፈታ ህልም ነዉ ፡፡

ማላጂ

“ኢትዮጵያዊነት እና ነፃነት ሠባዊ ፀጋ እንጂ ችሮታ አይደለም ፡፡ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop