April 14, 2022
35 mins read

ለአማራ አይመጥንም ዘፋኞች ሆይ! ለአማራ እማይመጥነው በአገሩ እንደ ደን መጨፍጨፍና ስደተኛ መሆን ነው!

በላይነህ አባተ ([email protected]

የበደኖው የአማራ ፍጅት፡- https://www.youtube.com/watch?v=J3WywOm_eMA

አማራ ከአርባ አምስት አመታት በላይ የዘር ፍጅት ወንጀል ተፈጽሞበታል፡፡ በዚሁም ተብሶ የአማራን ዘር ፈጅዎችን ሲረዱ የነበሩት መንግስታትና እንዳላዩ ሲያልፉት የነበሩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች የአማራን ጩኸት ቀምተው አማራን በበዳይነትን እየከሰሱት ይገኛል፡፡ ይህ ሁሉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነ መከራ በአማራ እየደረስ ያለው አማራ ራሱንና ሌሎችንም ለመከላከል የአካል፣ የጥበብና የዲፕሎማሲ አቅም አንሶት ሳይሆን የአማራ ምሁራን “ለአማራ አይመጥንም” የሚለውን የሞኝ ዘፈን እየዘፈኑ አማራን በማንቃት፣ በማድራጅትና በዲፕሎማሲ ሥራ ስላልተሰማሩ ነው፡፡

የአማራ አይመጥንም ዘፋኞች ሆይ! ለአማራ እማይመጥነው በአገሩ እንደ ደን መጨፍጨፍና በባዶ ሆድ ተሜዳ አዳሪ ስደተኛ መሆን ነው፡፡ ለአማራ እማይመጥነው ከነነፍሱ እንደ በደኖ ባሉ ገደሎች መወርወር፣ የእናቱ፣ የሚስቱና የእህቱ ማህፀን እየተሰነጠቀ የአረገዘችው ፅንስ ሲገደል ማየት ነው፡፡

888999ለአማራ አይመጥንም ዘፋኞች ሆይ፦ አይናችሁን ጨፍናችሁና ጆሯችሁንም ወትፋችሁ ታልሆነ ጣኦቶች ተዓባይ ወንዝ በስተደቡብ የሚፈጥሙትና የሚያስፈጥሙት የዘር ማጥራት ዘመቻም እያያችሁ ነው፡፡ ለገሰ ዜናዊና ሽፈራው ሽጉጤ የጀመሩትን አማራን የማጥዳት ዘመቻ ደቀመዛሙርቶቻቸው ከሮኬት በበበለጠ ፍጥነት እያስፈጠሙትና እየፈጠሙት ነው፡፡ መጪዎች ዘመናት ለአማራ ከዚህም እጅግ የከፉ ናቸው፡፡

እሚያሳዝነው እግዚአብሔርንና ጥረቱን አምኖ በገጠረም ሆነ በከተማ የሚኖረው አማራ ይኸንን ሁሉ ደባ የሚረዳበትና የሚተነብይበት መንገድ አለመኖሩ ነው፡፡ ይኽ ሕዝብ የጪፍጨፋውንም ሆነ የስደቱን መከራ የሚያውቀው ሳያስበው ግፉ እንደ ዶፍ የወረደበት እለት ብቻ ነው፡፡ የዓለምንም ሆነ የአገሪቱን ያለፈና የሁኑን ሁኔታ ተገንዝቦ የወደፊቱን ተንብዮ እድሉ ለሌለው ሕዝብ ማሳወቅና ማደራጀት ያለበት ፊደል የቆጠረው የአማራ ምሁር ብቻ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በአማራ ሕዝብ ለደረሰው የሰላሳ ዓመት የዘር ማጥፋትና ማጥዳት ዘር አጥፊዎቹ ብቻ ሳይሆን የዓለምንና የአገሪቱን ሁኔታ አገናዝበው ያልተነበዩና ሕዝባቸው ራሱን እንዲከላከል ዝግጁ ያላደረጉ የአማራ ምሁራንም በታሪክና በትውልድ ተጠያቂ ናቸው፡፡

ቲሞቲ ስናይደር የተባለ የየል ዩንቨርሲቲ ሊቅ እንደሚያስተምረው ዛሬ እሚታየው ምልክት የነገውን እውነታ ያሳያል*፡፡ ፕሮፌሰር ስናይደር እንደፃፈው ናዚዎች አይሁዳውያንን ለመጨፍጨፍ ሲወጥኑ  እንደ ለገጣፎና ሱሉልታ ገዥዎች በአይሁዶች ግድግዳዎች “አይሁድ በጀርመን ቦታ የለውም” የሚል ምልክት ለቀለቁ፡፡ ይኸንን የተለቀለቀ ምልክት ያነበቡ አይሁድ ምሁራን ግን እንደ ዛሬው አማራ ምሁራን “የጥቂት ጋጠ ወጦች ተግባር!” እያሉ አለፉ፡፡ እንደዚህ እይነቱ ጋጠወጥ ጋጠወጥን ከሚደግፍ ማህበረሰብ ውጪ እንደማይኖር ረሱ፡፡ በዚህ ችልታቸውም አይሁዳንን ሳያስጠነቅቁ በመደዳ አስጨፈጨፉ፡፡

ለገሰ ዜናዊ ወንበር እንደተፈናጠጠ የአማራውን ግድግዳ ትምክህተኛና ነፍጠኛ የሚል ቀለም ቀባው፡፡ የዚህን የቀለም ቅብ ምስጢር የአማራ ምሁራን መመርመር ሰነፉ፤ ሕዝቡም ችላ አለ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ለአማራ ምልክትነት የተቀቡትን ነፍጠኛንና ትምክህተኛን እነ ታምራት ላይኔና ስዬ አብርሃ በሃረር በአሩሲና በሌሎችም ሥፍራዎች ሰበኩ፡፡ ይኸንን ተከትሎም አማሮች በበደኖ ገደል ተወረወሩ፣ በአርባ ጉጉ፣ በአሩሲ ነገሌና በሌሎች ሥፍራዎች ታረዱ፡፡ ይህ እልቂት ለመጪው የአማራ የከፋ እልቂት ምልክት መሆኑን የተረዱት ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስና ወጣት ጓዶቻቸው አማራን ለመከላከል ሲጥሩ አሽሟጣጭና ተመጻዳቂ የአማራ ምሁራን ዘመቱባቸው፡፡ እርሳቸው ሕክምና ተከልክለው አለፉ፤ እንደ ተሾመ ቢምረው ያሉ የትግል ልጆቻቸው ታፍነው እስከ ዛሬ የደረሱበት እንዳይታወቅ ሆኑ፡፡

የትናት በስቲያው የአማራ እልቂት ለትናንቱ እልቂት ለአማራ ምሁራን ቦቃ ምልክት በሆነ ነበር፡፡ የትናንትናው የእልቂት ቁስልም ዛሬ ለሚታየው የአማራ እልቂትና ስደት ፍንትው ያለ ምልክት በሆነ ነበር፡፡ የዛሬው መጠነ ሰፊ እልቂትና ስደትም ለነገው የከፋ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ቦግ ያለ ምልክት ሆኖ በታዬ ነበር፡፡ ነገር ግን ከትናት በስቲያና ትናንት ያየነውን የአማራ ቁስል ኢትዮጵያ፣ አንድነት፣ ተጋብተንና ተዋልደን በሚል ዝተት ፋሻ እየሸፋፈኑ ቁስሉን የባሰ አነፈረቁ፡፡ በዚህም ምክንያት ወልቃይት፣ ራያና ጉራፈርዳ ያየነው ሞትና መፈናቀል ዛሬ ምዕራብና መሐል ጎንደርን ፣ ምዕራብ ጎጃምን፣ ወሎንና ሙሉ ሸዋንም አዳረሰና አረፈው፡፡

ይህ አገር ምድሩን የሸፈነው ቁስል ነገ ለሚመጣው እጅግ የከፋ እልቂት ምልክት አድርጎ መዘጋቸት ሲገባ ይኸንን የነፈረቀ ቁስል አሁንም ወንድማማችነት፣ ተጋብተንና ተዋልደን በሚል ደም ማፍሰስን በማያቆም ፋሻ እየሸፈኑ አማራው ራሱንና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን እንዳይረዳ እንደ ፀጋዬ ገብረመድህን የማይነጋ ሕልም ያልማሉ፡፡ ሲነጋም ህልሙን እንደ ከብት እያመነዠኩ ሲንዘላዘሉ ይውላሉ፡፡ ከመንዘላዘልም አልፈው ክቡር ፕሮፌሰር አስራትንና የትግል አጋር ልጆቻቸውን ያጠፏቸውን ጆሮ ጠቢዎች እያመለኩ ከእግራቸው ሲደፉና በካድሬነት ሲላላኩ ይውላሉ፡፡ አማራ ቢደራጅ ኖሮ ተዚህ አዘቅት እንደማይደረስ፤ ኢትዮጵያ እንዳትፈስ የአማራው ጥንካሬ ወሳኝ መሆኑን ይክዳሉ፡፡

ከአመታት በፊት አማራን በጠላትነት የፈረጁ ቡድኖች አማራውን አድቅቀው እንደፈለጉት ለማድረግ የጣሩት ለአንድ ኢትዮጵያና ለአማራ የቆመ ድርጅት እንዳይፈጠር በመከልከል ነበር፡፡ ለአንድነትና ለአማራ የቆመ ድርጅት በከለከሉባቸው ሃያ ሰባት ዓመታት እንወክለዋለን የሚሉትን ወጣት በፀረ-አማራነት ውቂያኖስ ዘፍዝፈው አይምሮውን በመበረዝ የፀር-አማራ መሰረታቸውን አጠናከሩ፡፡ ፀረ-አማራ መሰረታቸውን ካጠናከሩ በኋላ የለበጣ አንድነት ፖለቲካን አቀነቀኑ፡፡ በዚህ የለበጣ የአንድነት ፖለቲካም ኢትዮጵያ ሲባል ልቡ እንደ ለጋ ሺል የሚንፈራገጠውን አማራ እንደገና ጠለፉ፡፡ በዚህ ጠለፋም የአማራን አቅም የማድቀቅ ሴራውን ቀጠሉ፡፡ በፀረ-አማራ ስብከት ተነቅረው ያደጉት ሱሰኛ “ሙሴዎች”ና ባርጩማውን የለቀቁት ክፉዎች ግን ተዘራቸው ተጣብቀው ዘረፋውን ቀጠሉ፡፡

አማራ ጅቦች የማይሰሙትን “ኢትዮጵያና አንድነትን” ሲጨፍር ጅቦቹ ፀረ-አማራንና ክልልን ሲደልቁ ሰላሳ አመታት አለፉ፡፡ በዚህም ግርግር የዛሬዎቹ ጅቦች እንደ ትናንትናዎቹ ጅቦች የአገሪቱን ወታደራዊ ሐይል፣ ስልጣንና ምጣኔ ሐብት ያለ ሐፍረት ጠራርገው ወስደው መሰረታቸውን አጠናክረው በመላ አገሪቱ አማራን ባለቤት እንደሌለው ጫካ ሲጨፈጭፉ ይውላሉ፡፡ የአማራ ቅርሶች እየፈረሱ ከቅርሶቹ የሚመጣውን ገንዘብ እነሱ ይልፋሉ፡፡ አማራ የታሪካዊ ቅርስ እሳት አጥፊ ከውጪ እየለመነ እነሱ የአገሪቱን የባንክ ገንዘብ በወንበዴ ክንፎቻቸው ያዘርፋሉ፤ የተረፈውንም ለቢሮና ለከተማ ውበት እያሉ ይዘርፋሉ፡፡ ይኸ ሁሉ ሲሆን የአማራ ምሁራን የበሬን ቆለጥ ስትከተል እንደኖረቸው ቀበሮ የሙሴአቸውን ስብከት ሲያዳምጡ ይውላሉ፡፡

አማራ ምሁራን የሕዝባቸውን እልቂት የሚተነብዩ ጉልህ ምልክቶችን እንዳላዩ አልፈው በአማራ ለደረሰው የዘር ማጽዳት ወንጀል አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ “አይሆንም ትተሽ ይሆናልን አስቢ” የሚባለውን ብሂል ዘንግተው “በእስቲ እንያቸው!” ዘልዛላ አስተሳሰብ ሕዝባቸውንና አገራቸውን ለዚህ አብቅተዋል፡፡

የትግሬ ነፃ አውጪን ፀረ-አማራ ግቦች መፈተሽ ሰንፈው አማራ ለሃያ ሰባት ዓመታት የገሃነብ ኑሮ ኖሯል፡፡ ይህ ቡድን ኤርትራን እንደሚያስገነጥል፤ ለም ምሬታችንንም ለጡት አባቱ ለሱዳን እንደሚያስረክብና የተፈውንም በክልል እንደ በሬ ቅርጫ እንደሚከፋፍል አማራ ምሁራን ለመተንበይ ሰንፈዋል፡፡ በዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ራሱን ለመከላከል ያልተዘጋቸው አማራ እንደ ቅርጫ በተከፋፈለች አገር በማያውቀው “ሕገ-መንግስት” እንደ ደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች እንዲገዛ ተገዷል፡፡ ከሌሎች በከፋ መልኩ ሲታሰር፣ ሲገረፍ፣ ሲሰለብ፣ ሲሰደድ፣ በርሃብና በበሽታ ሲረግፍ ኖሯል፡፡ ፀረ-አማራ ገዥዎች የራሱን ባንዳ ልጆች ዛቢያ አድርገው ከደጁ ሞፈር ቆርጠዋል፤ ታሪኩና ቅርሱን አፈራርሰዋል፡፡ ከቅየው እያፈናቀሉ በእርዳታ ነፍሱን የሚያሳድር ሜዳ አዳሪ ሕዝብ አድርገውታል፡፡

ህሊና ያለውና ማፈርን የሚያውቅ አማራ ምሁር ለአምሳ ዓመታት በአማራ የደረሰው ግፍ እሳት እንዳየው ላስቲክ ሊያሸማቅቀው ይገባል፡፡ “በሞቴ አፈር ስሆን” እያለ እያጎረሰ ያሳደገውን ማህበረሰብ በጥቅም ታስሮ ወይም ሆዱን መርጦ በጅቦች ማስበላት መረገም መሆኑን ማጤን ይገባዋል፡፡ ፈገግ ሲል ሲል እየሳመ የታቀፈውን፣ ሲወድቅ ያነሳውን፣ ሲማር መቀነት እየፈታና ኪሱን እየፈተሸ ኮቢ የገዛለትን፣ ሲዳር ደግሶ የዘፈነለትንን፣ ሲሞት ፍታትና ተስካር የሚያወጣለትን ሙሉ በኩሉሔ ሕዝብ ለጅቦች አሳልፎ በመስጠቱ ሊፀፀት ይገባል፡፡ ከእነ ድንበሯና ክብሯ አገር ያስረከበውን ሕዝብ እንደ ይሁዳ ክዶ እልቂትን ካመጡበት ክፉዎች ጎን መቆም ሲኦል የሚከት ግዙፍ ኃጥያት መሆኑን ማመን ይኖርበታል፡፡

የአስኳላው፣ የቤተክህነትና የቤተ መስጊድ ምሁራን አማራ ዛሬ ከሚደርስበት እልቂት ወደፊት ሊደርስበት የሚችለውን አደጋ መተንበይ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምሁራን በትናቱ ምልክት የዛሬውን መተንበይ ስላልቻሉ አማራ ዛሬ በመላ አገሪቱ እየታረደና እየተሰደደ ይገኛል፡፡ ምሁራን በዛሬው ምልክት የነገውን እየተነበዩ ስላልሆኑ አማራ ገና ብዙ ችግር ይጠብቀዋል፡፡ እንደ አለመታደል የአማራ ምሁራን ከዛሬው ምልክት የነገውን በመተንበይ ፋንታ በሱሰኛ የላቲን ሙሴዎች ቀንበር ተጠምደው በካድሬነት ሲያገልግሉ ይታያል፡፡ ለአማራ ህልውና አስተዋፅኦ ከማበርከት ይልቅ አማራን ለመታደግ የሚፍጨረጨሩትን ወጣቶች በማብጠልጠልና በመጥለፍ ተጠምደዋል፡፡

ወጣቶቹ ለዚህ መከራ የተዳረጉት እኛ ታላላቅ ወንድሞችና አባቶቶች ሐላፊነታችንን ስላልተወጣን መሆኑን የላቲን ሙሴዎች ተከታዮች ዘንግተዋል፡፡ እኛ ሐላፊነታችንን ብንወጣ ኖሮ ወጣቶቹ ሥለሰማይና ሥለምድር ሲመራመሩ ይውሉ እንደነበር ማስተዋል ተስኗቸዋል፡፡ ወጣቶቹ የህልውና ትግል የሚያደርጉት እኛ ከከተትናቸው ገደል ለመውጣት መሆኑን የሚያመልኩት የላቲን ሙሴ አስረስቷቸዋል፡፡

የህልውና ትግል የሚያደርገውን ወጣት የአማራ ምሁራን እየጠለፉ ከሚጥሉባቸው ወጥመዶች አንዱ “ኢትዮጵያ፣ ዜግነት፣ ማህበራዊ ፍትህ!” የሚባል ዘፈን ሆኗል፡፡ ይኸንን ዘፈን ማዘውተር አማራን ለሰላሳ ዓመታት አሳርዷል፡፡ እንዲያውም በዚህ ዘፈን ወጣቱን መጥልፍና መጣል አማራው ለሌላ ዙር የዘር ማጥራት አጋልጦ እንደመስጠት ይቆጠራል፡፡

ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ፣ አንድነት፣ ዜግነት” እያሉ በሰፋፊ አዳራሽ የዘፈኑ ፓርቲዎች አማራን በበደኖ ገደል ከመወረውር፣ በአርባ ጉጉ ከመታረድ፣ ከወልቃይት፣ ከራያ፣ ከመተከልና ከጉራ ፈርዳ በችፍርግ ከመጠረግ አድነዋል ወይ? ኢትዮጵያ፣ ዜግነት ማህበራዊ ፍትህ እያሉ እሚደልቁት ቡድኖች ዛሬ አማራ ካድራ ወንዝ፣ ሀረር፣ ወለጋ፣ መተከል፣ ከሚሴ፣ ሸዋና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ሲታረድና ሲሰደድ እንኳን ሊከላከሉ ድርጊቱን የሚያወግዝ ትንፋሽስ ቱስ ብሏቸዋል ወይ? ሲሞዳሞዱ የሚውሉት ከገዳዮችና ከአስገዳይዎቹ ጋር አይደለም ወይ?

ኢትዮጵያ፣ አንድነትና ዜግነት በሚል ፋሻ የአማራን ቁስል እየሸፋፈኑ አማራ ሳይደራጅ በተደራጁ ሐይሎች እንዳለፉት አርባ ሁለት ዓመታት እንዲያልቅ ማድረግ በምድርና በሰማይ የሚያስጠይቅ የወንጀሎችና የኃጥያቶች ቁንጮ አይደለም ወይ? የአማራን የመከላከል ሐይል ለማዳከም የዜግነት ፓርቲ አቋቋምን ብለው የውሸት መሐላ በየወንዙ ከሚማማሉት አብዛኞቹ በድርጅቶቻቸው አማራን አስበልተው በመጨረሻም አማራን ከበላው ድርጅት እግር የወደቁ ይሁዳዎች አይደሉም ወይ? እነዚህ ይሁዳዎች አማራ ነገ የሚደርስበትን ችግር ይከላከላሉ ተብሎ ይጠበቃል ወይ?

ለስድሳ ዓመታት በፀረ-አማራ መንፈስ የተደራጁ ክፉ ቡድኖች ተከታዮቻቸውን በአንድ ፊሽካ ሲነዱ አላየንም ወይ? ትናንት ነፍጠኛና ትምክህተኛ የተቀባው አማራ ዛሬ ደሞ እንደ ናዚ ዘመን አይሁዳውያን “መጤና ሰፋሪ” የሚል ቀለም አልተቀባም ወይ? ታዲያ በዚህ ዘመን አማራ እንዳይደራጅ ጋሬጣ መሆን የሂትለር ተባባሪ ከመሆን ይለያል ወይ?

በአማራ መቃብር ሪፐብሊክ ለመገንባት በተነሳው ለገሰ ዜናዊና በቅኝ-ግዛት ታሪክ አቀንቃኙ ላቲኑ ሌንጮ ለታ ተሰብከው ያደጉ ከአርባ ዓመት በታች የሚገኙ ወጣቶች በአጪር ጊዜ ውስጥ ወደ አህዳዊ ፖለቲካ ይመጣሉ ብሎ ማሰብ ግብዝነት አይደለም ወይ? እንኳን የለገሰና የሌንጮ ተከታዮቹ መራራ ጉዲናስ ተአክራሪ አማራ ጠሎች ጋር እግሩን አምቧትሮ ሲቆም አላየነውም ወይ?

የአማራ ምሁራንን ከንቱ ድስኩርና ስብከት እየሰማ ያልተደራጀው የአማራ ወጣት ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ከመከራ ወጥቶ ያውቃል ወይ? የአማራ ምሁራንን ከንቱ ስብከት ተማምኖ ወጣቱ ዛሬም እንደ ትናንቱ ለመገረፍ፣ ለመሰለብ፣ ለመሰደድ፣ ከትምህርት፣ ከጤናና ከስራ ተገሎ ለመኖር እጁን አጣጥፎ ይቀመጥ ወይ? ድርጅት እንደ አፈር ሲቆልሉና መልሰው ሲንዱ፣ ፓርቲ እንደ ፍሪንባ ሲተለትሉና እንደ ክትፎ ሲከታትፉ የኖሩ ፖለቲከኞችን ዛሬም አምኖ ራሱን ተመከላከል ይታቀብ ወይ? አማራ ሲታሰር፣ ሲገረፍና ሲሞት የኖረው በእነዚህ ፓርቲ እንደ ጪቃ ሰርተው በሚያፈርሱ ፖለቲከኞች አይደለም ወይ? እነዚህ ፓርቲ በመሰንጠቅ እጥፍ ድርብ ፒ ኤች ዲ ያላቸው ከሀዲ ፖለቲከኞች እንኳን የኢትዮጵያን ሕዝብ ራሳቸውንስ አንድ ያደርጋሉ ወይ? እነዚህ ፖለቲከኞች እንደ ሳሙኤል አወቀ ተቀጥቅጠው የተገደሉትን በማተባቸው አዳሪ ወጣቶችና በድርጅቶቻቸው ስም የተሰለቡትንና አካለ ስንኩላን የሆኑትን ዜጋዎች ክደው ዛሬ ከገዳዮችና ከገራፊዎች የሚሞዳሞዱ ይሁዳዎች አይደሉም ወይ?

ለአማራ አይምጥንም ኪነቶች ሆይ! በዓለም ማህበራዊምና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን ለማስፈን የቻለ ቡድን የለም፡፡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህ በምድር ሰፍኖም አያውቅም፡፡ ወደፊትም ሕዝብ እየበዛና  እንደ መሬትና ውሀ ያሉ መሰረታዊ እሴቶች እየጠበቡና እያነሱ በሄዱ ቁጥር የማህበረሰባዊና የኢኮኖሚ ስርጭቱ ከፍትህ እየራቀ የሚሄድ ነው፡፡ እስካሁን እንደታየው ዓለም ወደ ማህበራዊ ፍትህ ፊቷን የምታዞረው በማህበረሰቡ መካከል የጉልበትና የጥበብ ሚዛን ሲኖር ብቻ ነው፡፡ አንዱ እንደ ገመድ ወፍሮ ሌላው እንደ ክር ቀጥኖ ማህበራዊ ፍትህ አይሰፍንም፡፡ ዓለም ተቻችላ ያለችው በሐይል ሚዛን ነው፡፡ አገርም ተቻችሎ እሚኖረው በኃይል ሚዛን ነው፡፡ የፍትህ ስብከት ህፃናትን የሚጨፈጭፍና የሚሰልብ ጭራቅን ግብር ያከፋዋል እንጅ አያሽለውም፡፡ ምክርና ትዕግስት የላም አሸናፊን እንደ ፌንጣ  የበለጠ ያቅበጠብጠዋል እንጅ አያስታግሰውም፡፡ በሬ ለላም አውቆ ከተሸነፈላት በተኛበት ሄዳ ትወጋዋለች፡፡ ታግሶ ቦታ ሲለቅላትም ተከትላ ትወጋዋለች፡፡ ትግስቱ አልቆ በቀንዱ ሰቅስቆና በሻኛው አንስቶ ታፈረጣት በኋላ ግን ታከብረውና ታጠገቡም ድርሽ አልል ትላለች፡፡

ጠንካራ ዲሞክራሲና ሕግ አላቸው በሚባሉት አውሮጳና አሜሪካ ሳይቀር የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ ፍትህ ዛሬም የለም፡፡ ቀለማሙ ሕዝብ ሊፈጥር በሞከረው የኃይል ሚዛን ትግል ከቤት ባርያነት ቢላቀቅም ዛሬም የውጪ ባርያ ነው፡፡ ባርያው ያደረገው መጠነኛ ትግል ፈቀቅ ያደረገው ከቤት ወደ ውጪ ብቻ ነው፡፡ ይህ የውጪ ባሪያ ዛሬም መንገድ፣ ሽንት ቤት፣ ሆስፒታልና ቢሮ ጠራጊ ነው፡፡ ይህ የውጪ ባሪያ ዛሬም የጡረተኞችንና የአካለ ስንኩላንን ሽንት እየጠረገ የሚጦር ባርያ ነው፡፡ በየትኛውም ዓለም የማህበራዊ ፍትህ ያለው ከወረቀትና ከውሸታም ፖለቲከኞች ላንቃ ብቻ ነው፡፡

ዓለምን ሲገዛት የኖረው፣ ዛሬም የሚገዛት ወደፊትም የሚገዛት የአካላዊና የአይምሮ የበላይነት ወይም ጉልበት ነው፡፡ ዓለምን የሚያሽከረክራት የከዳነው የመለኮት ትዕዛዝ ሳይሆን የተቀበልነው የሳጥናኤል መንፈስና ዳርዊን የቀመረው የጉልበት አሰላለፍ ብቻ ነው፡፡

አማራ በአጥንቱ ግድግዳነትና በደሙ ምርግነት ባቆማት አገሩ ቤቱ በግኒደር እየፈረሰና ንብረቱ እየተቀማ ተገድሎ በጅምላ በግኒደር ታፍሲ የሚቀበረው የውጪ ጠላትን ያንበረከከበትን የጉልበትና የጥበብ ሕግ ለውስጥ ጠላቱ ስላልተጠቀመበት ነው፡፡ አማራ እየተገደለ ገደልና ሽንት ቤት የተጣለው ሊበላው የመጣውን ጅብ ኢትዮጵያ፣ አንድነት፣ ዜጋ፣ ፍትህ በሚባሉ ለጅብ በማይገቡ ጽንሰ-ሐሳቦች ሊመልስ በመሞከሩ ነው፡፡ አማራ ህልውናው አስጊ ደርጃ የደረሰው ምሁሮቹ ለጅብና ጭራቅ በማይገቡ ቋንቋዎች ቀፍድደው እንዳይደራጅ ስለከለከሉት ነው፡፡ ዛሬም አማራን ለእልቂት የሚያጋልጡት ከትናንቱ ምልክት ዛሬን ከዛሬውም ነገን መተንበይ የማይችሉ ከአብራኩ የወጡ ድስኩራም እድሜ ጠገብ ምሁራን ናቸው፡፡

ለአማራ አይመጥንም ዘፋኞች ሆይ! አማራን በጠላትነት የፈረጁ ሐይሎች እስተ አፍንጫቸው ታጥቀው አማራን በየሥፍራው እየፈጁት ሳለ አማራ ራሱን እንዳይከላከል ገንዞ መያዝ ለባሰ እልቂት መዳረግ መሆኑን እንዴት አጣችሁት? በሂትለር ዘመን የአይሁዳውያን ግድግዳ ይቀባ እንደነበረው ዛሬ የአማራ ቤት በመጤና የሰፋሪ ቀለም እየተቀባ ሲጨፈጨፍ ምነው ባቄላ እንዳነቀው ዶሮ ጭጭ ማለትን መረጣችሁ? አማራን በጠላትነት ፈርጀው ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን ከስድሳ ዓመታት በላይ የሰበኩ ክፉዎችን በማህበራዊ ፍትህ ስብከት መመለስ የሞተን አስነስቶ በእግሩ የማስኬድን ያህል ከባድ መሆኑ እንዴት አጣችሁት?

ለአማራ አይመጥንም ኪነቶች ሆይ! “ሙሴዎች” ወልቃይትና ራያን መልሰው ለዘረፏችው ዘራፊዎች ሊሰጡ የማህበረሰብ ምህንድስና ደባ እየፈጠሙ ነው፡፡ የምህንድስና ሴራው ታልተሳካም አማራን እጁን አስረው ለሌላ ዙር ጦርነት ሊዳርጉት ቁማር እየተጫወቱ  ነው። ይህ የማህበረሰብ ምህንድስና ደባ አማራን ከአባቶች እርስት ለመንቀል አዲስ አበባን ጨምሮ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍልም በፍጥነት እየተከናወነ ነው፡፡  ይኸንን ደባ ተረድቶ ለመደራጀት የሞከረውን ፋኖም ሊበታትኑት እያሴሩ ነው፡፡ ይኸንን ከምንጊዜውም የከፋ ቁማር ተረድቶ ሁሉም የአማራ ምሁር አማራን ተዘር ፍጅት ለማዳን በሚችለው ሁሉ አስተዋጽዎ ማድረግ ትውልዳዊና ታሪካው ግዴታው ነው፡፡ አለበለዚያ ትናንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ በአማራ ሕዝብ ለደረሰውና ለሚደርሰው ቸነፈር የአማራ ምሁር በምድር፣ በሰማይና በታሪክም ተጥያቂ ነው!

 

 

* on tyranny: Twenty Lessons from The Twentieth Century chapter 4

ተጨማሪ ጽሑፎች፡

1. A Message to Amara Elites: Never Allow Ethnic Cleansing of Amara Again! https://www.zehabesha.com/a-message-to-amara-elites-never-allow-ethnic-cleansing-of-amara-again/?fbclid=IwAR39-VVEyK9B3K4qyv40xVyKLFAQ4yQd3NZ5gdVLLEIf-OL3BW8pyuuTAWI

  1. Please Stop Predisposing Amaras to Continue Perishing in Cities and Rural Areas!

https://www.zehabesha.com/please-stop-predisposing-amaras-to-continue-perishing-in-cities-and-rural-areas/?fbclid=IwAR0Qk8s_L_KBHRRXn9o_pr0Uu5fVnyDhkI4MuXMye0enMnRcpwfc2owSorI

  1. The Ethiopian Elites Have Failed to Follow The Principles of Our Forefathers! https://www.zehabesha.com/the-ethiopian-elites-have-failed-to-follow-the-principles-of-our-forefathers/?fbclid=IwAR2vDSOkwZ2-A8HUa-iajOYFrvb49Z2rdD62jLkfLA_T7p2V6vWcco9gEIk

4. በስልጣን ሰክሮ ያበደን ካድሬ ውይይትና ምክር ሊፈውሰው ይችላልን? https://welkait.com/?p=19399&fbclid=IwAR1PGGrvShRVdWUA5_-QmXlhonXcdrFDR-J6pIJv3LWBYPyRq9vwJLcWYYY

 

5. አማራ ሆይ! ምን እስኪሆን ነው የምትጠብቀው?

https://welkait.com/?p=17552&fbclid=IwAR1eqGmFZYQ_aO5tKOaJXsFZzW–Hi6PULfLQMJuSvh067CnTy-MMzFduuo

 

6. ጨቋኙ አማራ ይኸው ነው!

http://amharic.abbaymedia.info/archives/29664?fbclid=IwAR0e_LnjBSS5a32RXriIAS3_laU5kG-7WR3yaAZLzygplOiqXGeGFxecv54

 

7. አማራ ዳግም አትታለል እንደ ላሜ ቦራ!

https://welkait.com/?p=16336&fbclid=IwAR3TucrZU-L98xi7BHvmfy72coFWall47VWRKXYQs3OAlGT3_yttzFuqEns

 

8. ወጣት ሆይ! እደግ! ተመንደግ! – በላይነህ አባተ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/94987?fbclid=IwAR16KT0YJujEAGRuw2Qum3Thw7GD6WvIp8TfLCXeETm6ptbZ2BRBzqJiL2g

 

9. ወጣት ሆይ! ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ! http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%89%B5-%E1%88%86%E1%8B%AD-%E1%88%88%E1%88%85%E1%88%8D%E1%8B%8D%E1%8A%93%E1%88%85%E1%88%9D-%E1%88%86%E1%8A%90-%E1%88%88%E1%8A%AD%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%88%85-%E1%8B%88%E1%8B%B0/?fbclid=IwAR0tsEDbDAQaE5BkeeJpzHCv3j30RxoxKtsV4ybfgBg8PTatn0eJmmIQSz0

10. አማራ ሆይ! ሰው እንሰሳም ነው! https://welkait.com/?p=19311&fbclid=IwAR15eJVKUJ_b6SBFd-Sz8_mJ4wDOCGfJ4a6gVy8HQJdTigeXypyWG7KTwSc

11. የአማራ ጨቋኙ አቀንቃኞች እምቢኝ አረፋውን ባህሪ! http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8C%A8%E1%89%8B%E1%8A%99-%E1%8A%A0%E1%89%80%E1%8A%95%E1%89%83%E1%8A%9E%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%88%9D%E1%89%A2%E1%8A%9D-%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8D%8B%E1%8B%8D/?fbclid=IwAR06hGmzfyvYp0pamjEv2M4Oo3U4k5Lh1ucqE_NFHVb1MGmMet2mr-YUpeU

12. አማራ ከጅብ መንጋጋ ተላቆ ከእስስት አፍ ገብቷል! (በላይነህ አባተ) https://www.satenaw.com/amharic/archives/64345?fbclid=IwAR186W_UWnfZoS9_NhCKQ6hRHdx-c_W7HT3r0oLNVu1fzZhmad9LwyAsndY

  1. ለአባትዮውለገሰቦንድ ለልጁ ፓስተር አቢይ ፈንድ! https://welkait.com/?p=19088&fbclid=IwAR1mqyYRoNVg3ZCVPhEbSzxYZU3FGf1QH5siUhRwKdaKla-0Q6Ly4lKx7dY
  2. ሕዝብእንዲሰማህሰፊ አፍ ይኑርህ! http://www.zehabesha.com/amharic/archives/94149?fbclid=IwAR0531t6KCkF-TywMIFjVmqx-jZyabuh_Ourw5vqSlrFVACc8DH6ROXJgA8

15. በአማራ ሰማእታት የተፈጠመው ግፍ በቅዱሳን ሐዋርያት ከተፈጠመው ግፍ ይከፋል! (በላይነህ አባተ)

https://www.satenaw.com/amharic/archives/63706?fbclid=IwAR1Jz8X8rmn5Sxgbt9b-r_7VJ5P6stU0n79czhwp83hq9kB19i5_hiBhDRc

16. ይሁዳ ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር ሸጠው! (በላይነህ አባተ )

https://www.satenaw.com/amharic/archives/61148?fbclid=IwAR2x5wsTnwsME1ckDTJJfBg1VI_TgjoH0Wvba8dq_PjEyqkEcm32hq2cu5I

17. Urgent Message to Amara Elites: Speak Up Against The Ethnic Cleansing of Amara!

https://www.zehabesha.com/urgent-message-to-amara-elites-speak-up-against-the-ethnic-cleansing-of-amara/?fbclid=IwAR1XeFACxW_EiJB03BjvYZrMtNL0J7TFUgBO9OMGAGpGvGOsDQmryq4UJ4c

 

ሚያዚያ ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ.ም.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop