ሀገራዊ ምክክር የጥንሰሳ ምዕራፍ መጠናቀቅን አስመልክቶ – ከኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነት ለዘመናት ሲነሳ ቆይቶ አሁን በደረስንበት ደረጃ ዝግጅት መጀመሩ ኢዜማ እንደ ትልቅ ቁምነገር የሚያየው ጉዳይ ነው፡፡ ኢዜማ ሀገራዊ ምክክርን እንደመፍትሄ ሲቀበል ወቅታዊና አንገብጋቢ ችግሮችን ከመፍታት ባሻገር ያሉብንን ውስብስብ መዋቅራዊ ማነቆዎች