ለዘመኑ የሀገራችን ቤተ-መንግሥቱን ለተቆጣጠሩት መንደርተኛና ጎጠኛ ‘ቦልታኪዎች‘ / እ’ስራና ቅል …….. አፈጣጠራቸው፣ ቢሆንም ለየቅል፤ እንደ አቅማቸው፣ ሠርተው በሀሳብ – ተግባር፣ ተግባብተው፤ ሰላም አግኝተው፣ አንድነት ይኖሩ ነበር፣ በአንድ ቤት። በፍቅራቸው፣ የሚቀናው ዱባ ግን፣ ጉረቤታቸው፤ ያሴር ነበር ሴራ፣ የሚያሥር ይሸርብ ነበር ነገር፣ የሚያደናግር፤ ያጠምድ ነበር፣ ወጥመድ ባረፉበት ቤት፣ ሳይቀር በመንገድ። እ’ሰራን ሲያገኘው፣ ብሎ ጎንበስ – ቀና የሰላምታ አይነት፣ ያዥጎደጉድና፤ በማር የተቀባ፣ የመርዝ ቃላት ይነግረው ነበረ፣ መስሎ ተቆርቅሪ፣ ለሱ ያዘነለት። ቅልንም ሲያገኘው ወይም ቤቱ ሄዶ ከአስረደው በኋላ፣ እንደሚፈልግው በፍቅሩ ተገዶ፤ ምክር ነው እያለ፣ ነገር ይነግረዋል በማያውቀው ጉዳይ፣ ደሙን ያፈለዋል። ከለ’ታት አንድ ቀን፣ ሥራ በፈቱበት