የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ዋዜማ – ፫ በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)
(ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ. ከ 1950-1975 ‹‹… ጭንቅ ብሎኛል ኢትዮጵያዊ ማን ነው? ወጣት ሽማግሌው አገር ሲጠየቅ፤ አንዱ ጐጃም ነኝ ሲል ሌላው በጌምድር፤ አንዱ ኤርትራ ሲል ሌላው ተጉለት፤ አንዱ መንዝ ነኝ ሲል ሌላው ጋሙ ጐፋ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ብፈልገው ጠፋ፤ እስቲ አዋቂዎች እናንተ ንገሩኝ፤ እኔን ያስጨነቀው ኢትዮጵያዊው ማን ነው…?!›› (በ1950ዎቹ በዛን ጊዜው ቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ፤ የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረው ኢብሳ