[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል]
https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/
ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ብቻ የተመሠረተ መሆኑን እየገለጽኩ፣ በትችት መልክ ባቀረብኩት አስተያየትም ሆነ በወሰድኩት አቋም ግን እንደማልፀፀት ለመግለጽ እወዳለሁ።
ትዝታ በላቸው የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት ገደማ በተደጋጋሚ በቮይስ ኦፍ አምሜርካ ራድዮ ላይ ስለ አፍሪቃ ቀንድና፣ በተለም በመካከለኛው ምሥራቅ ይካሔድ የነበረውን የፖለቲካ ትርምስ በተመለከተ ሁለታችንን፣ ጃዋርንና እኔን በቃለ ምልልስ ግምገማ እንድናቀርብ አገናኝታን ነበር። ከዚህ ውጪ እኔ የግለሰቡን የሕይወት ታሪክ ለማወቅ ፈልጌ፣ ያገር ፖለቲካ ሒደቱንም ሆነ የውዝግብ ቦርሳውን ተከታትዬ አላውቅም
ፕሮፌሰር መረራ የላከለትን ስለ እሱ ያቀረብኩትን ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ የተባለ አዎንታዊ ችችት ካነበበ በኋላ “ጃዋር ኦሮሞዎች በአብላጫ ሙስሊም ናቸው” ብሏል ስል ያቀረብኩት ዘገባ ትክክል አይደለም ብሎ ከመካድ በስተቀረ በግምግማዬና በምሁራዊ አስተዋፅኦዬ እጅግ አወድሶኛል።
ከያቅጣጫው ግን፣ ‘ጃዋር ሀገሪቷ አሁን ያለችበትን ግጭት፣ ወታደራዊ አለመረጋጋትና የፖለቲካ ውዥንብር ለማራቅ፣ ሚዛናዊ ግንዛቤና ወሳኝ ምክሮችን መስጠት የጀመረ ቅን ኢትዮጵያዊ መሆኑን አስመስክሯል‘ ይምትለልው ያሁኑ የጃዋር የመታደስ ጨዋታ፣ በጥበብ የተሸመነ ማላገጫ ትርኢት መሆኑን ባታውቅ ነው፣ ምክንያቱም የዛሬ ፲፩ ዓመት ገደማ፣ እንደዚሁ የኦሮሞን ጠባብ ብሔሔርተኝነት አቋም አሽቀንጥሬ ጥያለሁ፣ ከዛሬ ጀምሮ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት ቆራጥ ጠበቃ ነኝ ብሎ ስለ ዛተ ቅንና ከልቡ ተቀስቅሶ የተነሳ መስሎን፣ ብዙዎቹ አገር ወዳድ ዜጎች በምስጋና ላይ ምስጋና አከናንበነው ነበር። ሌላው ቀርቶ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ዋና ስብሰባ ሲደረግ በሊቀ መንበርነት ይመራ ዘንድ ሾመነው ነበር። ጃዋር ግን ሳይውል ሳያድር ሾኬ ተጫውቶ አክሮባቲክስ በመሥራት ግልብጥ ብሎ ወደ ቀድሞው አቋሙ ተመለና በኢትዮጵያ ላይ ዛቻ በመሰንዘር ቪዲዮ ቀርጾ በያለበት በተነ። ይህንን ድርጊት አስከፊ የሚያደርገው፣ እሱና የሱ ተከታዮች የሀሰት ወሬ እንዲነዛ በማድረግ በአዲስ አበባ አካባቢ የነበሩትን የቄሮ ጀብደኞች አደፋፍረው በመቀስቀስ የብዙሃን ዜጎችን ሕይወት ሰለባ አድርገዋል።
ጃዋር አሁን ወደ ፖለቲካው የተመለሰው የሥር ነቀል ለውጥ መንፈስ አፍጦ መምጣቱን ስለተገነዘበ ነው። ይኸን እቅዱን ሥራ ላይ ለማዋል ተዛማጅም ለመሆን ከአማራ ልሂቃን የተወሰነ ድጋፍ ማግኘት እንዳለበት ያውቃል፣ የሚል ትችት ከአምስት እማኞች ነን ከሚሉ ከድያስፖራና ካገር ነዋሪ ምሑራን በተለያየ አጻጻፍ፣ መልዕክቱ ግን ተመሳሳይ ከሆነ ኢሜይል መልዕክት ደረሰኝ። ከዚህ በኋላ ነው ነቅቼ እንደ ተግባረኛ የፖለቲካ ሳይንቲስት