ክፍል አራት
ኢትዮጵያን ልንታደጋት የምንችለው አንድ ስንሆን ብቻ ነው። አንድ ለመሆን ራሳችንን ከከፋፋዩ የዘርና የብሄር ፖለቲካ ማጽዳት አለብን። የዐብይ አሀመድ አምባገነንት፤ የብሄር ጽንፈኛነት፤ እ-ፍትሃዊነት እና ጎሳዊነትና ኢትዮጵያዊነት አብረው እንደማይጓዙ ማመን አለብን። ማመን በቂ አይደለም። መተግበር አለብን።
እነዚህ እሴቶችና ባህሎች ሁከት ፈጣሪ፤ ለሰላም፤ ለእርጋታ፤ ለልማት ማነቆ መሆናቸውን ባለፉት አምሳ አመታት አይተናል። ይህንን አገር አፍራሽ ሁኔታ የዐብይ አህመድ አሊ ፓርቲና መንግሥት አባብሰውታል። አገር ሲፈርስ የሞራል ልእልናም አብሮ ይናዳል።
እኔን የሚያሰጋኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በተለይ የወጣቱ ትውልድ የሞራል ልእልና ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ መዝቀጡ ነው። ይህ ሁኔታ የሚያንጸባርቀው የኢትዮጵያን ባለሥልጣናት ራስ ወዳድነት የበከለው የሞራል ውድቀት ነው ብል አልሳሳትም። ለሰብእነት እና ለአገር ዘላቂ ጥቅም የሚያስብ አመራር የለም። ሃሰት መናገር፤ መዋሸት፤ መካድ፤ ማገት፤ የዘር ጥላቻ፤ ሌብነት፤ ሙሰኛነት፤ አጭበርባሪነት የተለመደ ሆኗል። –—ቀጣዩን ያንብቡ —