ጥቅምት 3 ቀን 2019ዓም( 13-10-2026)
በመጀመሪያ ህልውና የሚለውን ቃል ፍች እንመልከተው።የመኖር ዋስትና፣ዕድል ወይም የወደፊት እጣ ፈንታ፣(‘Existence,Desstiny) ማለት እንደሆነ እንረዳለን።የሰው ልጅ ስላለበትና ወደፊት ስለሚኖረው ኑሮ ማሰቡና መጨነቁ የተፈጥሮ ግዴታው ነው።በችግር ውስጥ የሚኖር ከድህነት የሚላቀቅበትን፣በበሽታ የሚሰቃይ የሚድንበትን ፣በአምባገነኖች መዳፍ የሚማቅቅ ሕዝብ ነጻነት፣ፍትሕ፣እኩልነት በሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚኖርበትን መንገድ የማሰላሰሉና የመከተሉ ውሳኔ ከጥያቄ ውስጥ የሚገባና የሚቃወሙት አይሆንም። ከዚህም ባሻገር የአንድ አገር ሕዝብ አንድነቱና ሰላሙ ሲናጋ፣በጎሳና በሃይማኖት ሰልፍ ውስጥ ገብቶ እርስ በርሱ ሲጋጭና ሲጨፋጨፍ ብሎም ተበታትኖ አገር አልባ የመሆን አደጋ ሲደቀንበት የራሱንና የአገሩን ህልውና ለማስጠበቅ ይነሳል።ለመበታተን ምክንያት የሆኑትን ጸረ አንድነትና ጸረ አገር የሆኑትን ይፋለማል፤ድንበር ጥሶ የመጣውን ጠላትና በውስጥ ተባባሪ የሆነውን ባንዳ ይከላከላል። በዚህ መስፈርት አኳያ አሁን በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ በህልውና ስም የሚካሄዱ ትግሎች ጎልተው ይታያሉ። (የPDF ቅጂ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ-ህልውና ሲሉ ህልውና ስንል! )