ከ50,000 በላይ የቤት እንስሳት አልቀዋል ፤ዛሬም ድረስ በእየቀኑ ከ200በላይ እንስሳት እየሞቱ ነው ።
30/12/2018ዓ.ም መኢአድ /አዲስአበባ
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በተለይ በጃን አሞራ፣በየዳ እና ጠለምት ወረዳዎች አሰቃቂ ድርቅ ተከስቷል ።
የክረምት ወራት በገባበት በዚህ ወቅት ጭምር በሽዎች የሚቆጠሩ እንስሳት በእየ ቀኑ እያለቁ ነው።
የአካባቢው ሕዝብ ለዓመታት በቀጠለው ጦርነት የሚደርስበት መከራ ሳያንስ በተፈጥሮ አደጋም ስቃይ ውስጥ ወድቋል ። “ከበሬው የተለዬ ገበሬ ከሞተ ቁጥር ነው” የጃን አሞራ እና ጠለምት ማሕበረሰብ በተከሰተው ድርቅ አካባቢውን ለቆ እየተሰደደ ይገኛል ። በዚህ ፈጣን ዘመን የአንድ አካባቢ ማሕበረሰብ በድርቅ ሲያልቅ ዝም ብሎ መመልከት ከገዳይነት አይተናነስም ።
ስለሆነም ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ለአካባቢው ማሕበረሰብ በአስቸኳይ እንዲደርስ መኢአድ አስቸኳይ ጥሪ ያቀርባል ።
የጃንአሞራእና አካባቢው ማሕበረሰብ ያለ አንዳች ድምፅ እየጠፋ ነው ።ስለሆነም
#የሚዲያ ተቋማት እና ግለሰቦች
#ግብረ ሰናይ ድርጅቶች
#የፌዴራል እና የክልሉ የአደጋ ጊዜ ተቋማት
#የፓለቲካ ድርጅቶች እና ሌሎች ተቋማት ሁሉን አቀፍ አስቸኳይ እርዳታ እንድታደርጉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል !
በመጨረሻም መኢአድ አስቸኳይ እርዳታ ለሚያደርጉ አካላት የሚቻለውን ትብብር የሚያደርግ መሆኑን እየገለፀ በዚህ የነፍስ አድን ጥሪ ላይ ሁሉም የድርጅቱ አባላት ተሳታፊ እንድትሆኑ ያሳስባል