መቅድም
ከሰሞኑ ከአማራ ፋኖ ትግል ተያይዞ ከሚነሱ አወዛጋቢ ጉዳዮች አንዱ በህወሃት እና በአማራ ፋኖ መካከል ሊፈጠር ይችላል ወይም በአንዳንዶች እሳቤ ተፈጥሯል ስለሚባለው የፖለቲካ ወይም የወታደራዊ ጥምረት ነው። ጥምረቱ “ጽምዶ” በሚል ስያሜ ሌሎችንም የታጠቁ ሀይሎች ያካተተ ቢሆንም ከህወሃት ጋር ያለው ጉዳይ ግን የበለጠ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ይህ ውዝግብ የተነሳው በባዶ ሜዳ ላይ አይደለም። የብልጽግና መንግሥት ከፋኖ ጋር የገባው ጦርነት፣ በአማራ ክልል ውስጥ የተፈጠረው የደህንነት ችግር፣ ከትግራይ ጦርነት በኋላ የተቀየረው የኃይል ሚዛን፣ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ በተደጋጋሚ የታዬው አንዲት ቅጽበትን መሰረት ያደረገ ጥምረትና መልሶ የመፈራረስ አዙሪት ይህንን የጽምዶ አጀንዳ ወደ ፊት አመጥቶታል።
የጥምረቱ ደጋፊዎች የሚያቀርቡት መሠረታዊ አመክንዮ ሁለቱም ኃይሎች ከአሁኑ የብልጽግና አገዛዝ ጋር በተለያዩ ምክንያቶች ግጭት ውስጥ ስለሆኑ “የጋራ ተቃዋሚ ካለ የጋራ የትግል መድረክ መፍጠር ለምን አይቻልም?” የሚል መከራከሪያ በማቅረብ ነው። እስካሁን ከአማራ ፋኖ በሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወይም ከህወሃት በኩል የሰማነው የጋራ ትግል መድረክ እንደተፈጠር ሚየረጋገጥ አዋጅ/አቋም በይፋ አልተነገረም፡፡አልፎ አልፎ በአንዳንድ አመራሮች እና ደጋፊዎች “ጥቅማችንን አስከብረን ከማንም ጋር ቢሆን አብረን እንሰራለን” የሚል ድፍን አቋም ከመግለጽ ያለፈ ህወሃት ይሄን ጥቃም ያስከብራል እኛም ይሄን ጥቅማችን አናስከብራለን ተብሎ በይፋ ለህዝብ የተነገረም የታወቀም አጃንዳ የለም፡፡ ስለዚህ ዋናዎቹ ጥያቄዎች መሆን ያለበት ህወሃትና ፋኖ የጋራ ተቃዋሚ አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለው ሳይሆን ሁለቱ ኃይሎች ሚያስከበሩት የትኛውን ጥቅማቸው ነው? የአማራ እና የህወሃት ጥቅም ቢጻረር እንዴት ይፈታል? ሁሉቱም ሀይሎች ቀይ መስመሮቻን ምኪሏቸው ምንድናቸው? ሁለቱም ሀይሎች ስለሀገራዊ ራዕይ፣ ስለ አማራ ሕዝብ ደህንነት፣ ስለማንነት እና እርስት ጥያቄዎች፣ ስለህገ መንግስት እና አሁን ስላለው ብሔር ፌዴራሊዝም እና በሌሎች አንኳር የፖሊሲ እና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚጋሩት ተመሳሳይ ራዕይ እና አቋም አላቸውን? የሚሉት ናቸው።
እነዚህ ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ ቢቻል ጥምረቱን ለመገምገም የበለጠ አመቺ ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን ለጥያቄዎቹ ምላሽ ለማግኘት አሁን ባለው ሁኔታ በሁለቱም በኩል ይፋዊ የሆነ የጥምረት አጀንዳ ባለመኖሩ ከተለያዩ የፋኖ የትግል መሪዎች እና ከአንዳንድ የትግሉ ደጋፊዎች ከተሰማው በመነሳት ከህወሃት ጋር የሚደርገው ጥምረት አደገኘቱን መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ የዚህ ጽሁፍ ውና አላማም ከታች በተዘረዘሩት ስምንት ምክንያቶች ከህወሃት ጋር የሚደረግ የትኛውም ጥምረት ከአማራ ጥቅምና ፍላጎት አንጻር መቃኘት ነው፡፡ — ሙሉውን ያንብቡ።—የህወሃት ፋኖ ጥምረት ለአማራው