August 27, 2024
7 mins read

የውጭ ሀገር ነጋዴዎች በጅምላም ሆነ በችርቻሮ ንግድ ሂደቱ መመርመር አለበት

ሙሼ ሰሙ

የውጭ ሀገር ነጋዴዎች በጅምላም ሆነ በችርቻሮ ንግድ ላይ እንዲሰማሩ የኢትዮጵያ ገበያ ክፍት መደረጉ ወደ ነጻ ገበያ ስርዓት ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ እመርታ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ሂደቱ መመርመሩና መፈተሹ እንደተጠበቀ ሆኖ።

ዛሬ ሸገር ላይ አንድ ጉምቱ የኢንቨስትመንት ባለሙያ ገበያው ለውጭ ነጋዴዎች መከፈቱ ኢትዮጵያዊ ነጋዴዎችን ከገበያ ሊያስወጣቸው ስለሚችሉ መንግስት ያግዛቸው፣ ይደግፋቸው የሚል ጥሪ ሲያደርጉ አደመጥኩ። ገበያው ክፍት የመሆኑን ዓላማ ጠንቅቀው የሚያውቁ ነጋዴም ምሁርም ስለሆኑ ጥሪያቸው ግር የሚያሰኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ነጋዴው አይዋከብ ማለት በስርዓት አይመራ እንደልቡ ገበያውን ያምስ ማለት አይደለም።

የኢትዮጵያ ገበያ ለዓለም ገበያ ክፍት የሚሆነው ገበያው ውስጥ የገነገነውን ስርዓተ አልበኝነት፣ አርቲፊሺያል እጥረትንና የዋጋ ንረት በመቅረፍ አቅርቦትና ፍላጎት በማሳለጥ የዋጋ ንረትን ለመግታት እንጂ በድጋፍና በድጎማ ሕገ ወጥ አሰራሩ አጠናክሮ በመቀጠል ያልተገባ ጉልበት አግኝቶ ችግሮችን ይበልጥ እንዲያወሳሰባቸው ሊሆን አይገባም። ድጎማና ድጋፍ ከታሰበ ብዙ መደጎምና መደገፍ ያለባቸው ተቋማዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች አሉን።

በአንድ በኩል በገበያ ውድድር ላይ የተመሰረተ፣ ስልጡን፣ በእወቀትና በሕጋዊ አሰራር የሚመራ፣ የሸማቹን መብትና ጥቅም ከግምት ውስጥ ያስገባ የገበያ ስርዓት እንዲፈጠር እየተመኙ፣ በሌላ በኩል ነጋዴው እራሱ በፈጠረው ምስቅልቅል ውስጥ እየዋኘ ሸማቹ ከዋጋ ንረት ወደ ከፍተኛ ዋጋ ንረት እየተላተመ እንዲቀጥል ለነጋዴው ድጋፍ፣ ድጎማና የፓሊሲ ማሻሻያ ይደረግለት ማለት ታጥቦ ጭቃ መሆን ነው።

እንደሚታወቀው በርካታ የኢትዮጵያ ነጋዴዎች አሰራራቸውን በማዘመን በአቅርቦትና በፍላጎት መካከል ያለውን ክፍተት በመሙላት ትርፍን ከብዛት ከማግኘት ይልቅ ግብርን በመሰወር፣ አርቴፊሽያል እጥረትን በመፍጠር፣ ቫት ባለመክፈልና ደረሰኝን ባለመቁረጥ ዋጋ ቆልለው አለአግባብ ትርፍ ማትረፋቸው ሳያንስ፣ መለስ ብለው ከግብር ከፋዩ ኪስ ከተሰበሰበ ገንዘብ ላይ ድጎማና ድጋፍ እንዲያደርግላቸው፣ መሬት በነጻ እንዲሰጣው፣ የውጭ ምንዛሪ በተለይ እንዲፈቀድላቸውና ግብር እንዲቀንስላቸው ጠዋትና ማታ የሚማጸኑና የሚወተውቱ እንደሆነ የሚታወቅ ነው።

በሕግ ወጥና በኦሊጎፓሊዎች የተተበተበውና በጥቂት ነጋዴዎች (የኮንትራባንድ ሕገ ወጥ ንግድ፣ የሹመኛ ቤተሰቦችና የክልል የንግድ ኢምፓየሮችን ጨምሮ) ቁጥጥርና ተጽእኖ ስር የወደቀውን የኢትዮጵያ ገበያ ነጻ ማውጣት የሚቻለው በቁጥጥር፣ ተመን በመጣል፣ በአስስተዳደራዊ እርምጃ፣ ነጋዴውን በማሰርና ሱቅ በማሸግ ሳይሆን አስተማማኝ አቅርቦት እንዲኖርና ዋጋ እንዳቀንስ ዘመናዊ፣ ሕጋዊ አሰራርና ውድድር እንዲሰፍንና የውድድር ሜዳውን ነጻና ፍትሐዊ እንዲሆን በማገዝ ነው።

ድጎማ፣ ድጋፍና ምጽዋት መስራት ለማይችሉ አቅመ ደካሞችና የሚሰራ እጅና እግር እያላቸው ስራ ለመስራት እድሉና ሁኔታው ያልፈቀዳላቸው ዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል የሚውል ነው። ሰርቶ የመለወጥና የመለወጥ እድል (Opportunity) ያገኙና በገዛ አቅማቸወ የፈጠሩ፣ ነግደው እያተረፉ ሐብት ያፈሩ ነጋዴዎች እራሳቸውን ማዘመን፣ መለወጥና ከወቅቱ ጋር መሄድ ሲገባቸው በለመዱትመንገድ በመቀጠል መወዳደር ባይችሉ መደጎምም ሆነ በተለይ መንገድ መደገፍ የለባቸውም።

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ከውጭ ነጋዴዎች ከለላና ሽፋን አግኝተዋል። ገበያውን ማዘመን፣ ሕጋዊ ግዴታቸውን በአግባቡ መወጣት፣ አቅርቦትን በማሻሻል ዋጋ እንዲቀንስና ሸማቹ ተረጋግቶ እንዲገበያይ ግዴታቸውን አልተወጡም። ለዘመናት የነገዱና አቅም የፈጠሩትም ማስመጣትን በማምረት መተካት አልቻሉም።

በጥቅሉ ነጋዴው ማህበረሰብ ቆም ብሎ ማሰብ የሚገባው ጊዜ ላይ ያለ ይመስለኛል። ገበያው የሚታመሰውና የሚመሰቃቀለው በሌላ ምክንያት ሳይሆን በአልጠግብ ባይነት፣ ኦሊጎፓሊ ፈጥሮ አዳዲስና ዘመናዊ ነጋዴ ወደ ገበያ እንዳይገባ በመገደብ፣ የግብርና የታክስ ስርዓቱን በማዛባት፣ አርቴፊሽያል እጥረት በመፍጠር፣ ዋጋን በማናርና የግብይት ስርዓቱ በሕግ እንዳይመራ በማደረግ ወዘተ ነው።

የውጭ ነጋዴዎች በከፍተኛ አቅምና ዘመናዊ አሰራር ገበያውን ሲቀላቀሉ ሀገር በቀል ነጋዴው ከሚገጥመው ተጽእኖ መዳን የሚችለው በድጎማ፣ በእርዳታና ሌላውን አግላይና እሱን ብቻ የማደግፍ ፓሊሲ በመቅረጽ አይደለም። በነጻ ገበያ ስርዓት ተወዳድሮ የግብይት ስርዓቱን አዘመኖ፣ አስተማማኝ አቅርቦትና ተመጣጣኝ ዋጋን ማረጋገጥ ብቻ ነው።

5 Comments

  1. TPLF was ready to sell most Ethiopian assets to whoever paid the highest. However, even TPLF suffered from nausea and dizziness at the mention of selling strategic economic assets to foreign entities. If they had to be sold, TPLF was getting ready (accumulating economic muscle) to ‘purchase’ these assets for itself. However, the lord of the gamblers, the pirates of the Global North, were not going to allow this. So they kicked TPLF out, brought in Mammush, and made their move to buy out not only the strategic big-price-tag items, but also the gullit and Arkebe-suq. The complete reversal of the Adwa victory and our being sold into bondage has arrived.
    All the grooming for Mammush and company (what with the fake Nobel Peace Prize award, the cajoling into war with the TPLF, the encouragement to invade Amhara region) as well as bankrupting the economy, was to get OPDO willing to submit to any arm-twisting that was necessary. All the illiterate OPDO bunch really needed was time and access to plunder and did not care about safeguarding any strategic interest of a country that in their minds has long ceased to exist.
    All the noise (mass murder, massacres, mass-graves, mass-evictions, war etc ) was to serve as a smokescreen and distraction for the economic plunder deals of the West; the contract on Ethiopia.

  2. ይሄ ሰውዬ ማደናበር ነው ማስተማር የያዘው ባለፈው ድንቅ ውሳኔ ነው የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች አይደገፉ ውናው ደመኛ የሀገር ውስጥ ባለሀብት ነው እቃ እየደበቀ ብሎ ሲነግረን ነቡት ዛሬ ምን ተገኘ?

  3. አቶ ሙሼ ሰሙ የነፃ ገበያው ዕምርታን እንዲያገኝ የግዴታ ገበያውን ለውጭ ነጋዴዎች ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል ሲል ስለአጠቃላዩ የኢኮኖሚ መሠረተ ሃሳብ ግልጽ ያልሆኑለት ነገሮች አሉ። እንደሚታወቀው አንድ አገር ወደ ነፃ ገበያ መድረክ ተቀንሶ ሊታይ አይችልም። በህብረተሰብ ግንባታ ታሪክ ውስጥም የውጭ ነጋዴዎች የአንድን አገር ኢኮኖሚ ያሳደጉበትና ህዝብንም ከድህነትና ከኋላ-ቀርነት ያላቀቁበት ጊዜ በፍጹም የለም። የአንድ አገር ህዝብ ዕድልና ከድህነት ተላቆ ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት በራሱ በህዝቡ ታታሪነት ዕውን ሊሆን የሚችል ነው። ለዚህ ደግሞ የግዴታ የሰለጠነ የአገዛዝ መዋቅርና የአገርን የሰውም ኃይል ሆነ የጥሬ ሀብት ለማንቀሳቀስ የሚችሉ ልዩ ልዩ ተቋማት ያስፈልጋሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ነገር የአንድ አገር ኢኮኖሚ መሠረት ንግድ ሳይሆን ሰፋ ያለ በስራ ክፍፍል ላይ የተመሠረተ የምርት ክንውን ነው። ልዩ ልዩ ምርቶች ሲመረቱና በገበያ ላይ ወጥተው የመሸጥ ዕድል ሲያገኙ ኢኮኖሚው በጥልቀትም ሆነ በሰፋት ሊያድግ ይችላል ወይም ዕምርታን ያገኛል። ለዚህ ደግሞ ሰፊው ህዝብ ተቀጥሮ የመስራት ዕድል ያስፈልገዋል። በተከታታይም የመግዛት ኃይሉ ማደግ አለበት። ምክንያቱም አምራቹ ራሱ ያመረተውን ገዝቶ የማይጠቀም ከሆነ ኢኮኖሚው ማደግ ስለማይችል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ጉዳይ የመንግስት ሚናን በሚመለከት ነው። በአንድ አገር ውስጥ መንግስት እንደ ባይተዋር የሚታይ ሳይሆን እንደ አለኝታ መታየት ያለበት ነው። ኢኮኖሚው በስፋት እንዲያደግ ከተፈለገ የጣልቃ-ገብ ፖሊሲ መከተል አለበት። በማደግ ላይ ያሉ ኢንዱስትሪዎችም ከውጭ በሚመጡ ተመሳሳይ ምርቶች እንዳይጠቁ የግዴታ የዕገዳ ፓሊሲ መከተል አለበት። በዚህ መልክ ብቻ ነው በምርት ክንዋኔ ላይ የተመሠረተ የገበያ ኢኮኖሚ ማደግ የሚችለው። የኢኮኖሚውም ዋና ዓላማ የነፃ ንግድን ለማስፋፋት ሳይሆን ህዝቡን ከድህነትና ከኋላ-ቀርነት ለማላቀቅና በራሱ ላይ ዕምነት እንዲኖረው ማድረግ ነው። ለዚህ ደግሞ ዕውቀት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው።
    በአንፃሩ የሙሼ ሰሙን ምክር የምንቀበል ከሆነ ህዝባችን በምንም ዐይነት ከድህነት አይላቀቅም። የተከበረ አገርም መገንባት በፍጹም አይቻልም። በአጭሩ የሙሼ ሰሙ አስተሳሰብ ተቀባይነት አይኖረውም። በሳይንስም የሚደገፍ አይደለም።

    ፈቃዱ በቀለ

  4. ዶር/አቶ ሙሼ ሰሙ ሃሳቦን ሰንዝረዋል ዶር በፍቃዱም ምልከታውን አጋርቷል እንደእርሶ ሃሳብ ከሆነ ገበያ እራሱን እያስተካከለ ይራመድ ገበያ ውስጥ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም ነው የሚሉን እንደገባኝ ከሆነ ገበያዎም በትክክል እንዳይሳለጥና እድገት እንዳይኖረን ባለሃብቱ እቃ እየደበቀ ሰው ሰራሽ እጥረት በመፍጠር ዋጋውን ያንረዋል ነው የሚሉን። እንደገባኝ በገበያ ላይ ጣልቃ ያልገባ የምእራብ ወይም የመስራቅ አለም መንግስት የለም ለምሳሌ በአሜሪካ ስቶክ ማርኬት እያሽቆለቆለ (ዳይቭ ሲያደርግ) መንግስት አስቁሞታል ከዛም በተረፈ የቻይና ገበያ አሜሪካን ሲያጥለቀልቀው መንግስት በታሪፍ ፍልሰቱን አዛብቶታል የእርሶን ምልከታ በድጋሚ ሰፋ አድርገው ቢያስነብቡን መልካም ይሆናል። የዶላሩ ዋጋ ሲንር በጥቂት ዶላር ብዙ እቃ ይገዛሉ የዶላር ፍሰቱ ወደ ሃገር እንዳይጨምር ገዥዎቹ የሃግራችንን እቃ ለመግዛት ጥቂት ዶላር ብቻ ይሆናል የሚያስፈልጋቸው በዛም አለ በዚህ ኢትዮጵያ ኤክስፖርተር አገር ስላልሆነች የዶላሩ ክምችት እየቀለለ እንጅ እየከበደ ወይም እየበዛ አይሄድም ያ ሲሆን ደግሞ ብዙ ብሮች ጥቂት ዶላሮችን ያሳድዳሉ እንደገና የዶላር ዋጋ ሰማይ ይነካል ማለት ነው ይህንን ፓራዶክስ ጊዜ ወስደው ቢያስታርቁልን መልካም ይመስላል። እውቀቱ የሚያንሶት አይመስለኝም ምናልባትም ከተከተሉት የኢኮኖሚክስ መንገድ ሊሆንም ይችላል።

    በታላቅ የኢኮኖሚክስ ምሁርነታቸው አብዝተው የሚያስነግሩት ብርሃኑ ነጋም በኢኮኖሚክስ ከዚህ የቀለለ ሃሳብ የሚሰጡበት አርእስት ስለሌለ ምልከታቸውን ብንሰማ ጥሩ ነው። እሳቸው መተቸትን ምነው ፈሩ? ትችትን አንድ ሰው ከፈራ ለትችቱ ማስተካከያ ሃሳብና እውቀት ያጠረው ሲሆን ነው። ባለፈው አሩሲ ኦሮሙማ ላደረጉለት ትውልድ አምክን ስራ ጀግናችን ብለው ቡሉኮና ክትፎ ሲጋብዟቸው ተመልክተናል። ሃገሪቱ የሃሳብና የአመራር እጥረት ሲኖርባት ለምን ወደ መድረክ ቀርበው ሃሳብ ካላቸው የማያስረዱን ይህ ፍቃደኝነት ሳይሆን የያዙት ቦታ ስለሚያስገድዳቸው ነው። በተከታታይ ይህ ሁሉ ተማሪስ ሲረፈረፍ መቅዳት አስቁሜ ነው ብለው ከሚያላግጡ ለምን ስራቸውን በአግባብ አይሰሩም?በእርግጥ ለአብይ እስከሰገዱ ድረስ ምንም ላይነካቸው ይችላል ግን ህሊናቸውንም ቢያዳምጡ መልካም ይመስለናል ታውቋቸውም ሆነ ሳይታወቃቸው ስፍር ቁጥር የሌለው ወጣት በጥይት እየረፈረፉ ነው።

  5. አቶ ሙራድ እዚህ ላይ የብርሃኑ ነጋን ስም ለምን እንደጠቀስክ በፍጹም አልገባኝም። ብርሃኑ ነጋ ወያኔ 27 ዓመት ያህል ተግባራዊ ያደረገውን የኒዎ-ሊበራል የኢኮኖሚ ፖሊሲንና አሉታዊ ተፅዕኖውን አስመልክቶ የሰጠው አንዳችም ሀተታ የለም፣ አቋሙም ምን እንደሆነ በፍጹም አይታወቅም። አቢይ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የእጅና ጓንቲ ሆኖ ይሰራል። ብርሃኑ ነጋ ስልጣን በማግኘቱ የሚደሰትና የሚዝናና እንጂ ለህዝብና ለአገር አሳቢ አይደለም። ደሀንም የሚንቅ ነው። ከኢትዮጵያ ይልቅ አሜሪካንን የሚናፍቅ ነው። ጠ/ሚኒስተር የመሆን ዕድል ቢያጋጥመው የአሜሪካን አሽከር ነው የሚሆነው። ስለሆነም የእሱን ስም መጥቀስህ ለምን እንደሆን አልገባኝም። በተለይም በአለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ምድር ምን እንደሚካሄድ በፍጹም አልገባህም ማለት ነው። በእኔ ዕምነትና ሳይንሳዊ ግንዛቤ ዛሬ በአገራችን ምድር ፋሺሽታዊ አገዛዝ ሰፍኗል። ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ነው። በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እየታዘዘ ተግባራዊ የሚያደርገው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አገር አፍራሽ ነው፣ ህዝባችንን የባሰ ደሀ ያደረገውና የሚያደርገው ነው።

    እንደሚታወቀውና በተግባርም እንደተረጋገጠው በአንድ አገር የተስተካከለ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊመጣ የሚችለውና ድህነትም የሚቀረፈው የህግን የበላይነት የሚያከብር አገዛዝ ስልጣን ላይ ያለ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ዐይነት ሁኔታ በሌለበት አገር ውስጥ ስለኢኮኖሚ ማውራቱ ተገቢ አይደለም። በመጀመሪያ የመንግስትና የአገዛዝ ጉዳይ መፈታት አለበት። የፖለቲካ አወቃቀርም መተንተንና መልክ ማግኘት ያለበት ጉዳይ ነው። የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰብ እጅግ ወደ ኋላ የቀረ ነው። የተገለጸለት አመራር ሲኖር ብቻ ነው ድህነትንና ኋላ-ቀርነትን ለመቅረፍ የሚቻለው። ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ ይህን ያህልም ስለኢኮኖሚ የሚያጨቃጭቀን ምክንያት የለም። እዚህ መድረክ ላይ ስለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሚጻፈውን ስመለከት አገራችን ምድር ምን እንደሚካሄድ አናውቅም ማለት ነው። እንደዚህ ስል ግን ስለኢኮኖሚ አይጻፍ ማለቴ አይደለም። አገዛዙ በውጭ ኃይሎች እየተመከረ ተግባራዊ የሚያደርገውን ፖሊሲ የመተቸት ሞራላዊ ግዴታ አለብን።

    ፈቃዱ በቀለ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

193342
Previous Story

ከባቡጂ ሞት ጀርባ እነማን ነበሩ | ጀግኖቹ ጎንደር ጥሰው ገቡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተያዙ | በሸዋ ፋኖ ድል አደረገ/ከፍተኛ ደህንነቱ ተሸኘ.. | አገዛዙን ያስደነገጠ ውይይት በጎንደር ተደረገ

ዋለልኝ መኮንን
Next Story

ዋለልኝ መኮንን ዳግም ሞቷል! – ሙሉዓለም ገ/ መድህን

Latest from Blog

የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን

 የአብይ አስተዳደርና የዶ/ር ብርሃኑ አኒ-ሚኒ-ማኒሞ

የጠ/ሚ አብይን የ2017 ዓ.ም. እንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ አነበብኩት፡፡ዘመኑ ላይ ተፈላሰፉበት ወይስ ምንድን ነው ነገሩ? ዘመን እድል ነው አሉን፡፡ እድል ማለት እንደ አማርኛው መዝገበ ቃላት ትርጉም ከሆነ እጣ ክፍል፣ ግንባር
Go toTop

Don't Miss

ዋለልኝ መኮንን

ዋለልኝ መኮንን ዳግም ሞቷል! – ሙሉዓለም ገ/ መድህን

“ዋለልኝ መኮንን” የሚለው ሥም በኢትዮጵያ (የቅርቡ) የሃምሳ ዐመት ፖለቲካዊ ትርክት