አሰፋ ወዳጆ ብዙዎቻችሁ በፌደራሊስቶች ጉባኤ የዛሬ ሰባት አመት አካባቢ ወላይታን በመወከል(እራሱን ወክሎ ነው የሚሉ አሉ) መቀሌ የተገኘው ሰው ማለት ነው።የዲላ ዩንቨርስቲ የአንትሮፖሎጂ መምህር ፣ ልክ እንደ ሰለሞን ዋዳ ደንጋጣ በመሆኑ ዲላ ብዙ ቀልደውበታል።መላ ከተማው መላ ዲላ የሚዋጋው ይመስለው ነበር።በመጨረሻ ሶዶ ላደረገው ትግል ዋጋ በመስጠት እዛው ሶዶ መድባው በምክር ቤቱ ፊት ቀርቦ በክብር ጋቢ ለብሶል፤ያሳዝናል።
ይህ ሰው ፅፎ አይቼው አላውቅም፤አንድ ሌክቸር የመሰለ በስህተቶች የተሞላ ከአራት ሰዐት በላይ የፈጀ ልጥፉን አገኘሁ።በዚሁ ልጥፉ በብርሃኑ ድንቄ የተዘጋጀውን ቄሳርና አብዮት የተባለችውን መጽሐፍ በማንሳት በወላይታ ላይ የደረሰውን በደል አንስቶ ይጮሃል።አንድ አንትሮፖሎጂ ነጠላ ድርጊትን ይዞ ብቻ አይራመድም፤በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱ ሁኔታዎችና ድርጊቶች ጋር አያይዞ ነው የሚያየው።
ከጣልያን ወረራ በኋላ በስደተኛና በአርበኛ መሓል ታላቅ ቅራኔ ነበር ።የንጉሱ ውሳኔ ለስደተኞቹ የሚያደላ በመሆኑ አርበኞቹ ስደተኞቹን በቀና አያዮቸውም ።አርበኛው ፊታውራሪ ተሰማ ጉርጂ የመንግስት ተሾሚ ለሆኑት ሰዎች ክብር አልሰጡም።አርበኞቹ ስደተኞቹን ከጣልያን እኩል ነው የሚያዮቸው። ያጣላቸው ዋናው ነገር በወላይታ ላይ የተካሄደው ጭፍጨፋ ነው፤አይመስለኝም።በአንድ ቀን ብቻ ሰላሳ ሰው ተፈጅቷል።ከመቶ በላይ የሚሆኑ ባላገሮችና ባላባቶች ተይዘው ታስረዋል።ይህንን ጣልያንም ያለምክንያት አይፈፅምም።የወላይታ ነገስታት ፊታውራሪ ደስታና ገብረ ሥላሴ አይናቸው እያየ ነው ሰዎቹ የተገደሉት።
እዚህ ላይ የዛሬ መቶ አመት አይደለም፤ አሁን አሁን በወላይታ ከመቶ ሃምሳ ሺ በላይ ባሮች አሉ።የሚደርስባቸውን ግፍ እራሳቸው ቢገልጡት፣ ቢያወሩት እመርጣለሁ።ዋናው ችግር እኔ ባርያ ነኝ በማለት በግንባር ቀደምነት የሚወጣ፣ የሚፅፍ፣ የሚናገር ማግኘት ነው።የሚፅፍ ከጠፋ እኔው እመለስበታለሁ።ይህን ለማረጋገጥ ወላይታ ላለ ሰው መደወል ብቻ ነው።እንግዳ እንኳ ቢሆን በጥቂት ደቂቃዎች እውነታውን አጣርቶ ይነግራችኋል።የሚገርመው ገርማሜ ሆነ ወልደ ሰንበት የሰሩት ስራ አለ?ወልደ ሰንበት ሊያወሩበት ይገባል።
ለወላይታ ባሮች የኢጣልያ ወረራ ምርጡ ጊዜ ነው።ጣልያን፣ መሬት ለገዢም ለባርያም እኩል አካፈለቻቸው።ባርነትን አስወገደች።የባርያውን መብት የነካን ጣልያን በካልቾ አገላበጠው።አንዴ አንዱን ሽማግሌ’’ ከጣልያን ምን ትዝ ይለዎታል?’’እንደ ማሰብ አሉና ’’የመንገድ ስራውና ካልቾው አይረሳኝም፤በመንገድ ስራው ያላገጠ ካለ በካልቾ ተመቶ የተረፈ አለ ብለህ ነው’’አሉኝ።
ጣልያን እንደወጣ ታላቅ እልቂት ነው የተፈፀመው ።ሰላሳ አይደለም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ባሮች ነው የተጨፈጨፉት።የራስ አበበ አረጋይ ተወካይ ሆነው በ’’ አሳሽ ’’ነት ሲሰማሩ ባሎቻቸው የተገደሉባቸው ሴቶች ጩሐትና እንባ ተሰማ ጉርጂን እየተከተለ ያን የመሰለ የጭካኔ ድርጊት ያስፈፀማቸው ይሄው ነው።
አቶ አክሊሉ ገሰሰ በቦረዳ ወረዳ የተከበሩ ሽማግሌ ነበሩ።እሳቸው እንደነገሩኝ ‘’ወላይታ ጣልያን እንደወጣ ባሮቹን ጨረሳቸው፤መሬቴን ተካፈልክ፤ሰደብከኝ እያለ ነው የፈጃቸው።የተረፈ ባርያም ያለ አይመስልም።ሁለተኛ የወላይታ ሴቶች ከእንግሊዝ ጋር የመጣ ኪኪዩ የሚባል ሻንቅላ ደግሞ ግዙፍ ናቸው እያገቧቸው ሄዱ።ለወላጅ አልነገሩ ሽማግሌ የለ ሴቶቹ በመኪና አብረዋቸው ተጫኑ ።የተመለሰም የለ።ጠፉ ጠፉ።’አሁን ስንት ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን ኬንያ’
እኝን የተከበሩ ሽማግሌ ማቅረቤ ነገሩን ለመጠቅለል አይደለም፤ነገሩን የሚያዳብሩ ሽማግሌዎች ለማግኘት ይረዱናል።አባታቸው የተገደሉባቸው እጅግ ጥቂት፣ አያቶቻቸው የተገደሉባቸው ብዙ ሽማግሌዎች ምርምር ለሚያደርጉ ሰዎች ማግኘት ይቻላል።
ወላይታ አማሮችን ጠብቆ አኑሯል፤ሽማግሌዎቹ እንኳ ምንም ሳይሆኑ ነው የተረፉት።ለዚህ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።በ1937 እ ኢ አ ሐይለ ሥላሴ ወላይታ ለጉብኝት በሄዱበት፣ ሽማግሌዎቹን ካዩ በኋላ መሬት የያዙትን ከዚህ የተሻለ መሬት እሰጣችኋለው በማለት አነሷቸው።ለወላይታ ብድር መለሱ።በእርግጠኝነት ሓይለ ሥላሴ ለወላይታ ምርጥ ወዳጅ ነበሩ።
ፊትአውራሪ ተሰማ ጉርጂ ሰማዕት ሊሆኑ ይሆን እስር ቤት በገቡ በጥቂት ቀናት የሞቱት።እውነት የሰው ልጅ ነፍስ እኩል ነው በማለት የተጋደሉት።በብዙ ሺ ሰዎች መገደላቸውን ቢያረጋግጥ፣ ገዳያቸውን ቢይዝ ሞት መፍረድ ተገቢ ነው።ይህ ከዘጠና አመት በላይ የሆነው ታሪክ ነው።ይልቁንስ ራስ አበበ አረጋይና አፄ ሓይለ ስላሴ የተለየ ግንኙት አላቸው።የሸዋ አርበኞች ንጉስ አንግሰን መዋጋት አለብን በማለት የልጅ እያሱን ልጅ አነገሱት።ከጥቂት ቀናት በኋላ ንጉሱ ሞቱ።እኝህ ንጉስ እስከ ድል ቢቆዩ ችግሩን እዩት።ከዛ በኋላ ስለንጉስ ተነስቶ አያውቅም።ራስ አበበ የሸዋን አርበኞች የሚመሩ ነበሩ።
ፌደራሊስት አሰፋ ወዳጆ ሚኒልክ አንድ መቶ ሀምሳ ሺ ባሮች ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው?ይህንንም በደምብ እናወራበታለን።አሁን ፊታውራሪ ተሰማ ጉርጂ ሰማዕት ነው ወንጀለኛ የሚመለስ ጥያቄ ነው።ፊታውራሪ ተሰማ ተገደሉ ወይስ ሞቱ?ዘመዶች ይኖራቸው ይሆናል?መቃብራቸው ይታወቅ ይሆናል?ጥሩ ተመራማሪዎችንም እናገኝ ይሆናል።ታሪክ መውጣት አለበት።
===========================
የዛሬ ዘጠና ዘጠኝ አመት የቃለ ህይወት ቤተ ክርስትያን ተመሰረተች።ላስታውሳችሁ መቶ አመቷ 2020 በሚቀጥለው አመት ነው።ይህን እንዳስታውሳችሁ ያረገኝ የዚች ቤተ ክርስትያን መሰረት የሆነው ታላቁ ዋንዳራ ነው።ፈረንጆቹ የቤተ ክርስትያናችን ቅዱስ ጴጥሮስ ነው ይሉታል።አሁን ቤተ ክርስትያንዋ የወላይታ ማላ ሆናለች የሰማሁት ወሬ ነው።ይህ ሰው ግን ባርያ ነበር።
የዛሬ ዘጠና ዘጠኝ አመት ዴቪድ ላምባ የተባለ ወንጌላዊ ጅማ ሊሄድ መንግስትን አስፈቅዶ እሱ ግን የሚሄደው ወላይታ ነበር።የሀገር ውስጥ የወንጌል መሪዎቹ ዋንኛው የዳውሮ ሰው ናቸው።የሚገርመው ግን ወላይታንም አስበዋት ይሆናል።ከብዙ ታሪክ ጋር ኦቶና ደረሱ።ህክምና መስጠቱ ታዋቂ ቢያደርጋቸውም ሀይማኖቱ እንዳሰቡት አልተስፋፋም።የወላይታ ባሮች ዘንድ ግን ከፍተኛ ተቀባይነትን አገኘ።የሀይማኖቱ ሰዎች ዘንድ ያለው ትህትና ነው ይህን ያደረገው።ዋንዳራ የተባለ ወጣት ስለሰዎች እኩልነት ቤተ ክርስትያንዋ የምታደርገው ሰበካ ሳበው።የሚያደርጉት ነገር ከሚያወሩት እንደማይለይ አረጋገጠ።ሀይማኖቱን ተቀበለና ዋና ሰባኪ ሆኖ ተገኘ።ዋንዳራ ሰብኮልኝ ጌታን ተቀበልኩ የሚሉ ሰዎች በዙ።ኦርቶዶክሶች’’ ከደህናው ሰው ይህን አዲስ እምነት የተቀበለ አለ ‘’ይጠይቃሉ።
‘አረ የለም!!’’ነበር መልሱ።ዋንዳራ በቤተ ክርስትያን ፣በመንገድ፣በገበያ ባገኘው ቦታ ሁሉ ይሰብካል።ከዚህ ውስጥ በመንገድ ላይ ያረጋት ሰበካ ውጤት አስገኝታለች።ጣልያን ልትገባ በአይሮፕላን ወረቀት ትበትናለች። ዳና መጃ ያን ግዙፍ የሰማይ ላይ አሞራ አይተው ይደነግጣሉ።ያ ልጅ ያለው ይህን ነው።ራሳቸው ሄደው ጌታን ይቀበላሉ።እኝህ ሰው በወላይታ ታላቅ ከሚባሉት ጎሳዎች ወላይታ ማላ የሚወለዱና ሹመኛም ናቸው።ዳና ማለት ምስለኔ እንደ ማለት ነው።ዋንዳራ ለዚህ ቀን ለመድረስ ስምንት ዐመት ፈጅቶበታል።እሱ ስለእኩልነት ሲል እኚህ ታላቅ ሰው ደግሞ በፍርሀት ጌታን ተቀላቅለዋል።ሁለቱም የቤተክርስትያንዋ ታሪክ ናቸው።
በኢጣልያ ወረራ የቃለ ህይወት ቤተክርስትያን ሀገር ለቃ እንድትወጣ ተደረገ።አምስት ዐመት ቆይተው ወንጌላውያኑ ሲመለሱ እነዋንዳራ ተጠናክረው ጠበቆቸው።እጅግ ተገረሙ።አንዳንድ የተለየ የራሳቸው የሆነ ነገርም ፈጥረው ነበር።በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘’ከፍየሎች ተጠንቀቍ’እንዳለው አባሎቻቸው ፍየል እንዳያረቡ አድርገው ነበር።ወንጌላውያኑ ይህን በተረዱ ጊዜ የነገሩን ትርጉም አስረድተዋቸው ፍየል ማርባት ጀመሩ።
ዋንዳራ ወንጌል ለመስበክ ለጠንቆይም ቢሆን አይፈራም፤መንገድም አይፈራም፤አህዛቦችንም አይፈራም፤ለሁሉም ጌታን ይሰብካል።የዋህ ፊት ነው ያለው፤ግን እጅግ የሚገርም መንፈስና ጥንካሬ ያለው ነው።ይህ ሰው በኦርቶዶክስ ቢሆን ቅዱስ ነው።በፕሮስቴስታንት ቢሆን ክብር ሊሰጠው ይገባል።የልጅ ልጆቹ ተፈልገው እናመሰግናለን ሊባሉ ይገባል።
የቃለ ህይወትን መቶኛ ዐመት በወላይታ የሚገኙ የወንጌል አማኞች ሁሉ ይመስለኛል።የወንጌል አማኙ ከ80% እስከ 90% ከወላይታ ህዝብ የሚደርስ ነው።ይህ ታላቅ ክብረ በዓል ከወላይታ አንስቶ ሌሎች ብዙ ህዝቦችንም የሚመለከት ይመስለኛል።ሙዝየም ማቆቆም ዋንኛው ትልቁ ተግባር ነው።ምርምሮች ሊሰሩ ይገባል።አቅም ያለው ሁሉ ሊሰማራበት የሚገባ ጉዳይ ነው።በቀበሌ ደረጃ እንዴት እንደተስፋፋ ሌሎችም ጉዳዮች ካሉ ምርምር መስራት ይቻላል።መቶኛ ዐመቱን በአዳዲስ መዝሙሮች ፣ ጉባኤ ፣ በምርምርና ጥናት አውደ ጉባኤዎች በአይምሮችን በሚመጡ ሀሳቦች መጨመር እንችላለን።የመጀመርያዋ ቤተ ክርስትያን የቷ ናት?የመጀመርያዋ መፅሓፍ ቅዱስ የቷ ናት?እንዲህ አይነት ጥያቄም ማንሳት ይቻላል።የዛሬ መቶ ዐመት የነበሩ ፈረንጅ ወንጌላውያን የልጅ ልጆች መጋበዝ ትልቁ ስራ ነው።
ክብር ለዋንዳራ
========= =================== ===========
ታላላቅ ሰዎች ባቆሙት ባለጌዎች ይመጡና ይፈናጠጡበታል።የእነዋንዳራን ታሪክ አንብብ።የድህነት ጠባቂ አይደለንም።እንዲህ አይነቱ ፍልስፍና ይመቸኛል።ግን ክርስትና ውስጥ እንዲህ አይነቱ ነገር የለም።ልመናን ጥላ፤ድሀን አትጥላ፤ድህነትን ግን የፈለከውን አርገው።ራስህን ወደታላቅነት አትውሰድ፤የእግዛብሔር አገልጋይ ከሆንክ ጠባቂ ለምን ያስፈልግሀል!!ድሆች እንዲሰሩ አበራታቸው፤ብዙ ጊዜህን ከድሀ ጋር አሳልፍ፤አንተ ድሀ እንዳትሆን ተጠንቀቅ፤ሀብታምና ድሀውን አገናኝና ለድሀው ስራ ፍጠር።አንተ ጥሩ ወንጌላዊ ፣ ነብይ፣ ሰባኪ ነህ።
ስለ ወላይታ ስናነሳ በኢትዮጵያ ሀይለኛው የባርያው ስርዓት የነበረበት መሆኑ ነው።ሩቅ አይደለም፤ካዎ ጦና መላ ደቡብን ያስጨነቀበት ነው።ያልወጋው የለም ፤ያላሸነፈውም የለም።ምኒሊክ ባይደርስ ስንት ብሄረሰብ ይጠፋ ነበር።እግዚአብሔር ይወቅ!
የደቡብ ክልል ዋና ከተማ ወላይታ ሶዶ እንዲሆን ብልጠታችን አገዘን አትበሉ፤ማን እንደረዳችሁ ታውቁታላችሁ፤ወይ የተደረገላችሁን አታውቁትም።እናንተማ ብቻችንን ክልል እንሆናለን ብላችሁ ነበር፤የዚህ አቀንቃኞች ደግሞ የተማሩት ናቸው።የበቀለ ገርባን ጨርቅ ይስሙ ነበር።ድንገት መገንጠል የሚባል ጉድ ቢመጣ ምን ሊሆኑ ነው።ወላይታ ለም ነው!!ለም ነው።የመሬቱ ስፋት 4200ሜ.እስኬር አሁን 4500ሜ.እስኬር አድርስውታል(እድሜ ገርማሜና ወልደ ሰንበት)።የኢትዮጵያን 1/250 የቆዳ ሽፋን የሚይዝ ቦታ ነው።ወላይታ ነጻ ብትወጣ በአፍሪካ የባህር በር የሌላት ትንሿ ሀገር ትሆን ነበር።ለሓይለ ማርያም መረዳትና ለአብይ ርህራሄ ወላይታ እጅግ ጥሩ ነገር አገኘች።የደቡብ ክልል ርዕሰ ከተማ ሶዶ ሆነ።የተመረጡት የደቡብ ኢትዮጵያ መሪ ጎፋ ሲሆኑ የሚያድሩት አርባምንጭ ጋሞ ዞን ነው።በየቀኑ የሚያደርጉት ነው።በሚመሩት ሀገር ባለማደር የአለም ሪከርድ ይመስለኛል።ለምን ወላይታ አያድሩም?ረጋ ብላችሁ እስቲ ሁላችሁም አስቡ።
ፕሮቴስታንቶች ተለውጠዋል።መጋቢ ፣ሐዋርያት፣ነብዮች ተለውጠዋል።ራሳቸውን ወደነገስታት ለውጠዋል።በአጃቢ ነው የሚንቀሳቀሱት።የልብሳቸው ፣የመኪናቸው ውበት የሚገርም ነው፤የቴሌቭዥን ጣቢያ ከፍተዋል፤ጌቶች ሆነዋል።የእየሱስ ባርያ ሲያጋጥምህ የግልህ ባርያ አታድርግ ።ሀይማኖት ከባህል መውሰዱ የሚቀርለት አይደለም።የባርያው አሳዳሪ በወላይታ ባህል ውስጥ ትልቅ ድርሻ አለው።ከዛ የወጣ ነው በቤተ ክርስትያን የሚታየው እብጠት።ብዙዎቹ መሪዎች ከወላይታ የወጡ ናቸው።
ፕሮቴስታንቶች የሚወደዱት ባላቸው ትህትና ነበር።ትዕቢት አይደለም።ይህ መንገድ የጥፋት ነው።ፕሮቴስታንት በዚሁ ከቀጠለች የውድቅት ዘመንዋን ጀመረች ማለት ነው።ቤተ ክርስትያንን ወደ ትህትና መንፈስ የምትለውጡ ወጣቶች መነሳት አለባችሁ።ካልሆነ ውጤቱን ታዩታላችሁ።
አሰፋ ወዳጆ አያቶ በአንድ ባንዲራ ተውበው ንግግር እያደረጉ ነው።የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እያስፈራሩበት ነው።መለስ ዜናዊ እንደሚያስፈራራብት ማለት ነው፤ይገርመኝ ነበር።ወላይታ ሁለቴ ለማልቀስ ሲፈልግ ነው እንዲህ የሚያወራው።ግድግዳው ላይ የለጠፉት ባንዲራ ቀይ ፣ቢጫና ጥቁር ነው።የቀይና ቢጫው ትርጉም በሀገራችን የታወቀ ነው።የጥቁሩ ትርጉም በባሮቻችሁ ላይና በጎረቤታችሁ ላይ ላደረሳችሁት በደል ይቅርታ የምትጠይቁበት ነው? መብሰል እንደዚህ ነው።
=== ==== ===== ======