አርሲ ክፍለ ሃገር የሚባለው፣ አሁን ለሁእት ዞን ተከፍላል፡፡ ከሸዋና ከቀድሞ ሲዳማ ክፍለ ሃገራት እንደ ሻሸመኔ፣ ሻሸመኔ አካባቢ ያሉ ሰፋፊ መሬቶች አካቶ፣ ግማሹን የአርሲ ክፍለ ሃር ምነሬት የያዘ፣ ዋና ከተማው ሻሸመኔ የሆነ፣ የምእራብ አርሲ ዞን አንዲ ሲሆን፣ ሌላው ዋና ከተማ አሰላ የሆነው የአርሲ (ምስራቅ አርሲ) ዞን የሚባለው ሌላው ነው፡፡
በምስራቅ አርሲ ዞን፣ ከ17 አመታት በፊት ይፋ በሆነው፣ ሆን ተብሎ የአማራ ቁጥር እንዲያንስ በተደረገው፣ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ኦሮሞ ተብለው እንዲቆጠሩም ተድርጎ፣ በአርሲ ከ20% በላይ ነዋሪው አማራ እንደሆነ ነው የተቀመጠው፡፡ እንደ አሰላ፣ ሁሩታ ያሉ ትላላ ከተሞች በብዛት አማርኛ ተናጋሪ ማህበረሰብ ያለባቸው ከተሞች ናቸው፡፡ ወደ አርሲ የመጡ ኦርቶዶክስ የሸዋ ኦሮሞዎችን ስንደምር፣ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በምስራቅ አርሲ ዞን ወደ ግማሽ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡
ከጥቅምት 17 ቀን ጀምሮ፣ በአርሲ ዞን በማንነታቸውና በኃይማኖታቸው ምክንያት ንጹህን ዜጎች በግፍና በጭካኔ ተገድለዋል፡፡ በአካባቢው በአገዛዙ የታጠቁና የተደራጁ አክራሪ ሙስሊም የኦሮሞ አሸባሪዎች አሉ፡፡ እነዚህ አሸባሪዎች የነ ዋቆ ጉቱ፣ ጃራ አባገዳ መንፈስ የተላበሱ ናቸው፡፡ በአማራ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያለባቸው ናቸው፡፡
እዚያ አካባቢ ያለው ፖለቲካ እራሱ በአማራ ጥላቻ የተሞላ ነው፡፡ ጃዋር ተከበብኩ ብሎ የነበረ ጊዜ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳም ሲገደል፣ ያንን ሁሉ ያደረጉት እራሳቸው የኦሮሞ ብልጽግናዎች ሆነው፣ በአርሲ ያሉ የብልጽግና አመራሮች ግን ያደራጇቸውን ጽንፈኞች በመጠቀም አማራው ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ነበር የፈጸሙት፡፡
እዚህ ጋር በዚያ ያሉ ጽንፈኞች አማራ የሚሉት ዘርና ብቻ በማየት አይደለም፡፡ የኦርቶዶስክ እምነት ተከታይ የሆነ በነርሱ እያት አማራ ነው፡፡ ስለዚህ ከሸዋ መጥተው በአርሲ የሚኖሩ ኦርቶዶክስ ቱለማዎች አማራ ተብለው እነርሱ ተጨፍጭፈዋል፡፡
በስፋት አልተዘገበም እንጂ፣ በተከታታይ በኦሮቶዶስክ እምነት ተከታዮች ላይ ግድያውና ጭፍጨፋው ያቆመበት ጊዜ የለም፡፡ በ2016 እና በ2017፣ ማህበረ ቅዱሳን እንደገለጸው፣ በሸርካ ወረዳ ብቻ፣ በ9 ቀበሌዎች ከ115 በላይ ምዕመን ተገድለዋል፡፡ በሺሆችም ተፈናቅለዋል፡፡
ሰሞኑን ከጥቅምት 16 ጀምሮ በተከሰተው አሰቃቂ ግድያ ፣
# በሙኔሳ ወረዳ የዳሙ መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን አገከጋይ ቀሲስ ደስታ ጨምሮ ዜጎች ሞተዋል፡፡
# ከ30 አመታት በፊት ጭፍጨፋ በተደረገበት በአርባ ጉጉ አካባቡ ። በመርቲን በጉና ወረዳዎች፣ ከ15 በላይ ኦርቶዶክሶች ታርደዋል፡፡ ከነዚህ መካከል የ2 እና የ73 አመት እድሜ የነበራቸው አሉበት፡፡
# በሸርካ ወረዳ ሶስት ኦርቶዶክሶች ተገድለዋል፡፡
# በሆንቆሎ ዋቤም እንደዚሁ 5 ኦርቶዶክስክ ክርስቲያኖች ተገድለዋል፡፡