ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻፲፰
October 11, 2025
(ዶ/ር መኮንን ባይሴ mekonen.bayssie@gmail.com
ጠ/ም ዐቢይ አህመድና ዘንዘርጡ ዳንኤል ክብረት በአቡነ ሳዊሮስ ታዝለው፤ አቶ ጌታቸው ረዳም በአባ ሠረቀና በአቡነ ሳሙኤል ታዝለው ወደ ቤተክህነት ገቡ!
የቀሲስ አስተአየ ፅሁፎችን በቅርብ የሚከታተል ስለሆነ አንባቢያን ያተርፋባቸዋል ብሎ ይህንን መጠቆሚያ አቅርቧል።)
ማሳሰቢያ:– ከዚህ ቀደም የካህናቱን ጥምር ንቅናቄ ይረዳ ይሆናል ብየ በመገመት ቀሲስ እያቀረቡ ሳይሳኩ የቀሩትን ሁሉ ውዝግቦችን የሚያሳዩትን መዝገቦች በማሰናሰል አመስከረም 20 ቀን 2018 ዓ/ም አቅርቤ ነበር፡፡ (ሙሉዉን ሃሳብ ይህንን ሰንሰለት በመጫን ያንብቡ)።
የዚህችኛዋ ማሳሰቢያነት ጠ/ም ዐቢይ አህመድና አማካሪው ዘንዘርጡ ዳንኤል ክብረት በአቡነ ሳዊሮስ ታዝለው ወደ ቤተ ክህነቱ መግባታቸውን፤ የቀድሞው የዐቢይ ጠላት፣ የዛሬው የዐቢይ አማካሪ የሆነው አቶ ጌታቸው ረዳም በአባ ሠረቀና አቡነ ሳሙኤል ታዝሎ ወደ ቤተ ክህነት መግባቱን ለማስገንዘብ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ቢያንስ ለሶስት አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ክብር ባዋረደና ሰባዊነት በጎደለበት ቦታ ሁሉ ሳያሰልሱ አባታዊ ተግሳፅና ምክራቸውን መለገስ ብቻ ሳይሆን የሚያቀርቧቸው ዕይታዎች አንዳንዴም ትንቢት ይመስላሉ። ስለዚህ የሚቀርቡትን መዛግብትና ቃለመጠይቆች በትግስትና በማስተዋል አንብቧችው፤ አዳምጧቸው። በመዛግብቶች የቀረቡት ማብራሪያወች ቀሲስ አስተርአየ ከፃፏቸው ዉስጥ የተወሰዱ ናቸው፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት በነሐሴ 14 ቀን 2015 ዓ/ም (August 20, 2023) “የኢትዮጵያው ፓትርያርክ በቀንዱ በጅራቱ መካከል፣ በኮርቻ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በፊት በኩል በሳዊሮስ አማካይነት ዐቢይ ቀንዱን ይጎትታል፡፡ በኋላ በኩል ጌታቸው ረዳ በትግራይ ካህነት አማካይነት ጅራቱን ይጎትታሉ፡፡ ፓትርያርኩ በመሐል ተቀምጠዋል” ብለው በዚያን ወቅት የነበረውን ውዝግብ ቀሲስ አስተርአየ ገልጸውት ነበር፡፡
በዚያው ዓመት ጥቅምት 3 ቀን 2015 “ኢትዮጵያ ወደ ሕገ አረሚ ተገለበጠች” በሚል ርዕስ ጦማር ጽፈው ነበር፡፡ በዚህ አስደንጋጭ ርዕስ (ሙሉውን ጽሁፍ ይህንን ሰንሰለት በመጫን ያንብቡ) የጻፉት የቤተ ክህነቱ አቋም መንገዱን የሳተ ድጋፍና ተቃውሞ በሚል አደራጀተው ጽፈውታል፡፡
ቀሲስ አስተርአየ በዚህ ጽሑፍ በዚያው ዓመትና ወቀት በሕዝብ ላይ በመፈጸም ላይ የነበሩትን ሁሉ ግፎች አስፍረውታል፡፡ በጽሑፉ ላይ የቤተክህነት ም/ክትል ስራ አስኪያጅ ሆኖ የእሬቻን በዓል ሲመራ የነበረው ‘ቄስ በላይ’ (ዛሬ እስር ቤት ያለው) እና ከሱ ጋራ ዋና ሥራስኪያጅ ሆነው በመተባበር ሲያስፈጽሙ የነበሩት አቡነ አብርሃም ነበሩ፡፡ ቀሲስ አስተርአየ እነ በላይ ይህንን ስህተትና ክህደት ሲገልጹ:- ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን አራቱን ስርዓቶችን ገልጸው፤ የእሬቻን ገኖ መውጣት ለመግለጽና ለማሳየት ባቀረቡት ጦማር ላይ ታላቁ አባት አብርሃም ካራን (Haran) ላይ አራግፎት ወደ ወጣውና ወደ ከለዳውያን የጣዖት አምልኮት መግባቷን ከ3ሺ ዓመታት በፊት ወደነበረችበት ዘመን ተገለበጠች ብለው ነበር፡፡
የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራአስኪያጅ የነበረው በላይ የእሬቻው ረ/ቀዳሚ መሪ ሆኖ በመሰለፉ “አስደንጋጩ የቤተ ክህነቱ አቋም” ብለው ቄሱ ገልጸውት ነበር፡፡ በዚያ ዓመት ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ወደ አሜሪካ መጥተው ፍልሰታን ባንድ ቤት ነበሩ፡፡ የፍልሰታን ማለቅ ምክንያት አድርገው ቃለ ቡራኬ ሲያቀርቡ አቡነ ሳዊሮስ በጥጋቸው ተቀምጠው ነበር፡፡ የአቡነ ሳዊሮስ ከአቡነ ማትያስ ጋራ መምጣታቸው ለሕዝበ ክርስቲያኑ አልተነገረም ነበር፡፡በድብቅ ወደ አሜሪካ መጥተው የቆዩት ‘አዱኛ ፈይሳ’ በሚል ስም ቤተ ክርስቲያን ከመሠረተው ሳሙኤል ብርሃኑ ከሚባለው ጋራ ነው፡፡
ሳሙኤል ብርሃኑ የሚባለው ከደብረሰላም ዲሲ ቅድስተ ማርያም ተገንጥሎ ከጀዋር መሐመድ ጋራ ተሰልፎ “አማራ የምኒልክ ሠፋሪ ነው፡፡ ሳሙኤል ጀዋር በሳለው ገጀራ ቢጨፈጨፍ ተገቢ ነው” እያለ የሰበክ አረመኔ ሰው ነው፡፡
ቀሲስ አስተአየ “የኢትዮጵያው ቅዱስ ጳትርያርክ በቀንዱ በጅራቱ መካከል ሆነው ውዣ ውዦ ይጫወታሉ” በሚል ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ቀንዱን አቶ ጌታቸው ረዳ ጅራቱን ይጎትታሉ ብለው ያቀረቡት በዚሁ ወቅት ነበር፡፡ ቪዲዮውን አዳምጡ፡፡ በዚህ ሳምንት ፓትርያርኩ “ደክሞኛልና አቡነ ሳሙኤልን እንደራሴ አድርጉልኝ” ብለው ሀሳብ ማቅረባቸው ከተሰማና ሰው ከተቃወመ በኋላ ማስተባባያ ተሰማ፡፡ “እባባ ያየ በልጥ በረየ” እንደሚባለው ራሳቸው ፓትርያርኩ “አቡነ ፋኑኤል ጵጵስናውን በገንብ ገዝተው መግባታቸውን እየመሰከሩ የሲኖዶሳቸው አባል ካደረጉት፡፡ በዝሙት ከነበሩበት ት/ ቤት የተባረሩትን የአቡነ ኤወስጣጢወስን ጵጵስና ከተቀበሉና ቤተ ክርስቲያን ክፍለው ሰው አጋድለው በደም መከሰስ የሚገባቸውን ሳዊሮስን ጥቅላይ ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን ከተስማሙ አቡነ ሳሙኤል በእንደራሴነት እንዲሰየሙ አያደርጉም ብሎ የሚያምን ካለ በሳቸው የተፈጸሙትን ሁሉ ስህተቶች ያልተረዳ ሰው መሆን አለበት፡፡፡
በየጊዜው አቅጣጫቸውን እየቀያየሩ ሕዝቡን የሚያጋድሉት የትላንቱን ስምቡሌወች የዛሬ ሽታየ፣ ሽታየ ተባባዮች ጌታቸው ረዳና ዐቢይ የትላንትናቸውን መስመር ቀይረው ይመጣሉ፡፡ ጌታቸው ረዳ እነ እነ አባ ሠረቀን ይዞ ወደ አዲስ አበባ መጣ፡፡ ዐቢይ እነ አባ ሳዊሮስን ይዞ ወደ ቤተ ክህነት ገቡ፡፡ ቢዚያን ጊዜ በመካከል ተቀምጠው ውዣ ውዦ የተጫወቱት አባ ማትያስ አሁንም ጨዋታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት ቀሲስ አስተአየ የተናገሩት ሙሉውን ቃለመጠይቅ በትግስት ይህንን ሰንሰለት በመጫን አዳምጡት፡፡ የካህናቱን ጥምር ንቅናቄ እንመራለን የምትሉት ቄሶች ቀሲስ “ኢትዮጵያ ወደ ሕገ አረሚ ተገለበጠች” ብለው የጻፉትን ብታነቡት “የኢትዮጵያ ፓትርያርክ በቀንዱና በጅራቱ ላይ ናቸው” ብለው የተናገሩትን ብታዳምጡት በቤተክህነት ውስጥ የገባውን የብልጽግናውን የፖለቲካ ሁኔታ በሚገባ ልትረዱት ትችላላችሁ፡፡ ንቅናቂያችሁም ዓላማውን እንዳይስት ሊረዳችሁ ይችላል።