እኔዎች (እኔያት) – በላቸው ገላሁን September 21, 2022 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email እኔዎች (እኔያት)አንዱ እኔ ሲጠራኝአንዱ እኔ ሲልከኝሌላው እኔ ሲጥለኝአንዱ እኔ ሲያነሳኝ፣አንዱ ወደ ግራያአንዱ ባለጋራአንዱ ወደ ደጅየሌላው ወዳጅ፣ሌላኛው ወደ ቀኝሌሎቹን እንዲዳኝአንደኛው ወደ ታችለራሱ ሊያመቻች፣አንዱ ወደ ላይሊነካ ሰማይአንደኛው ወደ ፊትሌሎቹ እንዳይቀድሙትአንዱ ወደ ኋላሊያጣራ ሊያብላላ፤አቤት የእኔ መዓት የራሴ ብዛቱለየቱ እንቢ ብዬ ልታዘዝ ለየቱ?እኒህ ሁሉ እኔዎች ውስጤ ተከምረውሁሌ እየተጣሉ አልስማማ ብለውአንድ እኔ ባተለ ፍዳውን ቆጠረሌላው ኔ ደስ ብሎት ተኝቶ እያደረ። በላቸው ገላሁን (ነሓሴ 1998) (USA) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ