August 11, 2022
9 mins read

ከኦሮሙማ የብልፅግና መንግሥትና የወያኔ ህገመንግሥት ለዐማራ መፍትሄ አይገኝም – ሞረሽ ወገኔ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሐሙስ፣ ነሃሴ ፭፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Aug. 11, 2022) ቅጽ  ቁጥር ፯

Moresh

ዐማራ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን አጥብቆ የሚታገልለት ግቡ መንግሥትን ከነህገመንግሥቱ መቀየር ብቻ መሆን አለበት።

ኢትዮጵያን ከድጡ ወደማጡ ለመውሰድ የሚያንደረድረው ኦሮሙማ የአዲስ አበባን ህዝብ በፍርሀት ሸብቦ መያዙ ሳያንስ በወለጋና በመተከል የተጀመረው ጥቃት ጎልብቶ አዲስ አበባ መግባቱ እየታየ ነው። መሀል አዲስ አበባ መኪና ለመውሰድ ሲባል ወጣት የመኪና አሽከርካሪዎች እየታረዱ እንደሚጣሉና ከፍተኛ ወንጀል እንደሚሰራ በተደጋጋሚ ታይቷል።ወንጀለኞቹ ለህግ ቀርበው ፍርድ አለማግኘታቸውና አዲስ አበባ የሰው ህይወት ቀጥፎ መኪና የሚዘርፍ ወንጀለኛ በመበራከቱ የብዙዎች ቤት እየተፈታ፣ ህዝቡን በሰቀቀን ያለዋስትና እንዲኖር ተፈርዶበታል።

አብይ አህመድ የኦሮሞ ህዝብ መዝሙር በአዲስ አበባ መዘመር የለበትም። ለሚለው የህዝብ ጥያቄ የመለሰው መልስ ኦሮሞን የሚጠላ ሕዝብ በአዲስ አበባ እንዳለ ለማስመሰል የተውገረገረበትና ፍፁም ከጠቅላይ ሚንስትር የማይጠበቅ ጠብ አጫሪ መልስ እንደሆነ አይተናል። ነገር ግን ህዝቡ ተቃውሞው በቋንቋው ብቻ ሳይሆን መዝመሩ ያዘለው ኢትዮጵያን የሚከፋፍል መርዝ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ አሁንም መላው የአዲስ አበባ ህዝብ “የአመታትን ጭቆና በደም አጥበንልሻል” የሚል ይዘት ያለው የኦሮሙማ መዝሙር መቸም ቢሆን አዲስ አበባ ላይ መዘመር ስለሌለበት በአቋሙ ፀንቶ ሊታገል ይገባዋል።

አብይ አህመድ የኦሮሞ ህዝብ መዝሙር በአዲስ አበባ መዘመር የለበትም። ለሚለው የህዝብ ጥያቄ የመለሰው መልስ ኦሮሞን የሚጠላ ሕዝብ በአዲስ አበባ እንዳለ ለማስመሰል የተውገረገረበትና ፍፁም ከጠቅላይ ሚንስትር የማይጠበቅ ጠብ አጫሪ መልስ እንደሆነ አይተናል። ነገር ግን ህዝቡ ተቃውሞው በቋንቋው ብቻ ሳይሆን መዝመሩ ያዘለው ኢትዮጵያን የሚከፋፍል መርዝ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ አሁንም መላው የአዲስ አበባ ህዝብ “የአመታትን ጭቆና በደም አጥበንልሻል” የሚል ይዘት ያለው የኦሮሙማ መዝሙር መቸም ቢሆን አዲስ አበባ ላይ መዘመር ስለሌለበት በአቋሙ ፀንቶ ሊታገል ይገባዋል።

የዐማራ ህዝብ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ተፈርዶበት ቀደም ሲል በህወሓት ወያኔ፣ አሁን ደግሞ በኦሮሙማ ብልፅግና በዘርፈ ብዙ መከራና እልቂት ላይ ይገኛል። መቋጫ ያጣው የዐማራ መከራ ከ 30 ዓመት በኋላም ተጠናክሮ በመቀጠሉ ምክንያት በአውቶብስ ተሳፍሮ የመጡ መንገደኞች መታወቂያቸው ከምስራቅ ዐማራ መሆኑ ከተረጋገጠ አዲስ አበባ ጫፍ ከደረሱ በኋላ በኦሮሚያ የፀጥታ ኃይሎች እንዲመለሱ፣ እንዲጉላሉ መደረጉ ልብ ሰባሪ ግፍ ነው። ዛሬ አዲስ አበባ አትግቡ የተባለው ነገ ከአዲስ አበባ እንዳትወጡ እንደማይባል ምንም ማረጋገጫ አይገኝም፣ አብይ አህመድና ብልፅግና ከወያኔ ጋር ባለው ጥልድረሱልኝ ባለ ሰዓት የሕዝብን እልቂትና የሀገርን የመፍረስ አደጋ ከመንግሥት ጋር ቆመው፣ ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው፣ ደማቸውን አፍስሰው፣ ህይወታቸውን ገብረው ከአደጋ የታደጉትንና ከሞት የተረፉትን ጀግና የዐማራ ፋኖዎች በመክዳት እያፈኑ እንዲጠፉ መደረጉ የኦሮሙማን ብቻ ሳይሆን የአዴፓና የአብንንም ሆድ አደር ባለስልጣናት ፀረ ዐማራ ሰልፍ ማሳያ ነው። ለዐማራ ደግሞ ብቸኛ የመዳኛ አማራጩ ፋኖነት ብቻ ነው።

በመተከልና በወለጋ በዘር ማጥፋት ወንጀል በጅምላ ተፈጅተው በፈጣሪያቸው እርዳታ ከሞት የተረፉ ተፈናቃዮች እስከአሁን ድረስ በቂ ድጋፍና እርዳታ ሳይደረግላቸው እየተንገላቱ ይገኛሉ። በአንፃሩ ከሱዳን የመጡና አሶሳ የሰፈሩ ስደተኞች በውጪ ድርጅቶች ሳይቀር ድጋፍ እንዲደረግላቸው ተደርጎ የኢትዮጵያ መንግሥትም ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ ይታወቃል። የሰው ልጅ ክቡር ስለሆነ የሱዳን ስደተኞች መደገፋቸው ጥሩ ሆኖ ሳለ በሰሜን ሸዋ፣ በወለጋ፣ በመተከል ወ ዘ ተ ተፈናቅለው በየመጠለያው ያሉት የዐማራ ልጆች ድጋፍ የማያገኙበት ምክንያት ዐማራ በመሆኑ የሚከፈል የግፍ ፅዋ እንደሆነ ልብ ልንለው ይገባል።

የኦሮሙማው መንግሥት ባዘዘውና ባወጀው ጦርነት የአማራና የአፋር ህዝብ እንደቅጠል ረግፏል። ሀብት ንብረቱ ወድሟል። ከትግራይ ወያኔ ጋር ድርድር ለማድረግ ከተፈለገ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑትን አፋርንና ዐማራን ያማከለ መሆን ይኖርበታል። አዋሳኙ አፋርና አማራ ያልመከረበት በጎን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሐሙስ፣ ነሃሴ ፭፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Aug. 11, 2022) ቅጽ ፱ ቁጥር ፯
2 www.moreshwegenie.org [email protected] ከወያኔ ጋር ድርድር የሚባል ነገር ካለ ይህ ድርድር የሽፍንፍን እርቅ ይሆናል። ስለዚህ ዐማራና አፋርን ያላማከለና የወልቃይትና የራያ ጉዳይ በአግባቡ እልባት ሳያገኝ፣ ቅንነት የጎደለው ሽምግልናም ሆነ እርቅ መረጋጋትና ሰላም እንዳይኖር ፈንጅ እንደማስቀመጥ ይቆጠራል። ስለዚህ መንግሥት የዚህ ሁሉ ጥቃት አድራጊና ተባባሪ አካል መሆኑ ታውቆ፤ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝምታውን እንዲሰብር ፣ ከአዲስ አበቤና ከዐማራ ህዝብ ጎን በመቆም የብልፅግና ሎሌ እንደ አዴፓ ያሉ ግልገል ብልፅግናዎችን ሳይተማመን በራሱ ቆሞ ታግሎ ራሱን ከኦሮሙማ አገዛዝና ከወያኔ ህገ መንግሥት ነፃ እንዲያወጣ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop