የተካደ ትውልድ (በእውቀቱ ስዩም) June 6, 2022 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የተካደ ትውልድአይዞህ ባይ የሌለውታዳጊ የሌለውወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለውደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤የተካደ ትውልድአብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየእድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለትአምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍት የተቀማአልጋው ያጋም እሾህ፥ ምኝታው የሳማ፤የተካደ ትውልድሞቶ እንኳን ሬሳው፥ አይላላለት ቀንበርበዘብ እጅ ተገድሎ ፥ በሹም የሚቀበርከጡት አስጥል በላይ፥ ኑሮ የመረረውእንዳይሄድ ጎዳናው ፥ የተደናገረውድል ያልሰመረለት ፥ትግል ሳይቸግረው: :የተካደ ትውልድበስጋ በነፍሱበቀልቡ በገላውከቶ ምንድን ይሆን?ምንድን ይሆን መላው?(የማለዳ ድባብ፥ 28) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ