አድዋ ድሌ ተሽከረከረች! – በ ገለታው ዘለቀ February 27, 2022 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ያምማል እያለ የከተተውጉሮ ወሸባው አባተውየጅግንነት የውኃ ልኬትየህብር ክንዳችን ጉልበትየትብብራችን ብርታትመልህቅ ያገር አንድነትአድዋ……ማሳያ ልኬታችንንየአብሮነት ቃል ኪዳን ውላችንንየነፃነትን ዋጋ ክብራችንንአድዋ ክብሬ ናት ኩራቴታሪኬ እምዬ ስስቴአያ ሆ ሆ ተሽከረከረች…..አንቺ እርግብ ሆይ ብረሪየአድዋ ተራሮችን ድል አብስሪየድል ዝማሬን ዘምሪላለም ህዝቦች ሁሉ መስክሪ!በቅኝ ግዛት ብትር ቆስለውአንገታቸውን ቀልሰውየሃዘን በርኖስ ደርበውተከፍተውና ቆዝመውጉልበታቸው መሬት ጠቅሶ ከንፈራቸው መሬት ልሶ ብሶት ሆዳኛቸውን አብሶየደም እምባ ሲያለቅሱሃዘን ተጭኗቸው ሲተክዙእነሆ ከአፍሪካ ቀንድ ላይከአድዋ ተራሮች ላይየምስራች ድምፅ ተሰማነጋልህ ጭቁን ቀናበልማመፅናናት ይሁን ለራማያምማል እያለ የከተተውጉሮ ወሸባው አባተውየቅኝ ግዛቱን ጉልበቱ ራደውየግዛት ዘንጉ በረደውበምስራቅ አፍሪቃ ኮከቦችበኢትዮጵያ ድንቅ ልጆችእነሆ ……አዲስ ምእራፍ ተከፈተየነፃነት ብርሃን አባተያምማል እያለ የከተተውጉሮ ወሸባው አባተውአድዋ ድሌ…..አያ ሆሆ ተሽከረከረችሞገሴ አድዋ ዛሬም ከበረችአያ ሆ ሆ ተሽከረከረችዛሬም ኢትዮጵያ አንድ ናት አለችአድዋ…..እናንት የአድዋ ተራሮችየአንድነታችን ህያው ምስክሮችብርሃናችሁ ዛሬም ይብራይፈንጥቅ የንጋቱ ጮራግለጡ የተፃፈባችሁንአሳዩ ማተማችሁንአያ ሆ ሆ ተሽከረከረች…..ዘመኑ ሄደ ዘመኑ ጠባየአድዋ ፅዋ ከቤቴ ገባአያ ሆ ሆ ተሽከረከረችየአድዋ ድሌ ዛሬም ከበረችአያ ሆ ሆ ተሽከረከረችዛሬም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ‘ያለች!አያ ሆ ሆ ተሽከረከረችእኔ ከኢትዮጵያ ወይ ፍንክች አለች!ድል ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት! መጋቢት፣ 2013 Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ