ኢትዮጵያ ለፍተው ጥረው ኃብት ያካባቱ ሰዎች ነበሯት። እነ አቶ ከድር ኤባና በቀለ ሞላ ለሃገራቸው ብዙ ከለፉ ባለጸጋዎች መካከል ነበሩ። ትልቁ ነገር ለፍተው ጥረው አንቱ የተባሉትም ሆነ የሕዝብ ኃብት መዝብረው የከበሩ፣ ኃብቶቻቸው በስሞቻቸው ወይንም በልጆቻቸው ወይን በዘመዶቻቸው የተመዘገቡ ነበሩ። ዛሬ ለየት ይላል። ገና አስቀድሞ አምባገነንነትን ለመጣል ታገልን የሚሉት በብዙ ሺህ የትግራይ ልጆች ደም ተረማምደው መዲና ከተማዋን አዲስ አበባን የተቆጣጠሩት “ተጋዳላዮች” ዋነኛ ዓላማቸው የሃገሪቱን ኃብት ስልታዊ በሆነ መንገድ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ነበር። ኤፈርት የተባለው በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበው ትልቅ ኮርፖሬሽን ዋነኛ ሥራው የቱባ ባለስልጣናትን ኃብት ማጠራቀም ሲሆን ሌላኛው ስልት ደግሞ ሕንጻውን፣ የኮንስትራክሽንና የትራንስፖርት ድርጅቶችን፣ ፋብሪካውን፣ ሆቴሉን፣ እንዱስትሪውን፣ የቡናና ጫት ንግዱን፣ ጉዲፈቻውን፣ ወዘተ፣ በማይታወቅ ሰው ስም አዙሮ መቆጣጠሩ ነው። ይህ የነሱን ኃብት በስሙ አስመዝግቦ የባርነት አደራውን የሚወጣው “ተስፈኛ” ኃብታም ቢመስልም ኃብታም እንዳልሆነ ውስጡ ያውቀዋል። በሰው ፊት ቸርና ለጋሽ ሆኖ የመቅረቡ ስልታዊ አካሄዱ ደግሞ ስለሚያሳፍረው ዓዕምሮውን አንካሳ አድርጎታል። ኃብት ደክመው ለፍተው ሲያገኙት እርካታን ይሰጣል። በንጉሡና በደርግ ዘመን በሙሰናና በዓየር ባየር ገንዘብ ያካብቱ ኃብታሞች ቢኖሩም እንኳን እንዲህ እንደዛሬው አሳፋሪ ደረጃ ላይ አልደረሰም ነበር። በንጉሡ ዘመን የነበሩት ጥቂት በንጉሡ ልጆች ወይም በከፍተኛ ባለሥልጣኖች ተይዘው የነበሩ ኃብቶች በቀላሉ ተወርሰዋል። በደርግ ዘመን ባለሥልጣናት በራሳቸውም ይሁን በሌሎች ስም ያስመዘገቡት ኃብት እንደነበር ብዙም አልተነገረም። እንደውም አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት መኖርያ ቤት እንኳን አልነበራቸውም ይባላል። ዛሬ ሙስናን መዋጋቱ ከባድ የሆነው በርካታ ትላልቅ ተቋሞችና ድርጅቶች “በተስፈኞች” ስም ተመዝግበው መያዛቸው ነው። ወይዘሮዋ “ኃብት በስሜ ከተገኘ ይወረስ” ያሉት ከኤፈርት ውጭ ያለውን ጠቅላላ ኃብታቸውን በሚያምኗቸው ተስፈኞች ስም ስላስቀመጡ ነው። ቢሆንላቸው አብዛኛዎቹ ባለሥልጣናት የሥራ መልቀቅያ እያስገቡ ኃላፊነታቸውን ቢለቁና ቻይና ሄደው ያካበቱትን ቢበሉ ደስተኞች ነበሩ። እነሱም እኮ ሰው ናቸው፣ ትግሉ በፈረጠመ ቁጥር ይሰጋሉ። ከዚህ ቀደም አስራ ሰባት ዓመት በጦርነት ኋላም ሃያ ስድስት ዓመት አዲስ አበባ ውስጥ ሲኖሩ እንደ ሂሳብ ሹም በተለያዩ ሰዎች ያስመዘገቡትን የሙስና ኃብቶቻቸውን ቀንና ሌት ሲቆጣጠሩ ዓዕምሯቸው ባክኗል። የቀድሞዎቹ “ተጋዳላይ” የዛሬዎቹ “አካውንታንት” የሙስና ኃብቶቻቸውን ኃብት በአደራ የሰጡትን ተስፈኛ እስከመርሳት የደረሱም አሉ። ነገ አደራውን የሚረከበው መንግሥት በሙስና የተገነቡ ንብረቶች ወደ መንግሥት ኃብትነት ማዞሩ እጅግ ይከብደዋል። ከቱባው ሙሰኛ ባለስልጣን ጀርባ ያሉትን “ተስፈኞች” ለማወቅ የግለሰቦችን የኋላ የገንዘብ ታሪክ ማጥናቱ ራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ቀድሞ “ጋሪ ነጂ” ወይንም “ሱቅ በደሬቴ” የነበረ ጮሌ ሰው ባለትልቅ ፋብሪካ ሊሆን ይችላል። የዚህን ዓይነቱን ሰው የኃብት ክምችት ማጣራቱ ቀላል ሊሆን ቢችልም የሁሉንም ተስፈኞች ኃብት ማጣራቱ ደግሞ ሁሌም ቀላል ሊሆን አይችልም። በርካታ ኃብቶች ወደ ዶላርና ወርቅ እየተለወጡ ወደ ውጭ ሃገር ወጥተዋል። በውጭ ሃገራትም ሃብታም የሆኑ “ስውር ተስፈኞች” አሉ። ይህን ሁል ማጣራቱ ቀላልም ከባድም ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ እንዲህ ተመዝብራ፣ ሙሰኞች እንዲህ ቀልደውባት አያውቅም። “ተስፈኛው ባለኃብት” ኃብታም ለመባል በተስፋ የሚኖር ተላላ ነው። በስው ፊት ቸርና ለጋሽ በመምሰል አክብሮትን የሚፈልገው ተስፈኛ ዋነኛው የኃብቱ ምንጭ የሆነው ቱባው ባለስልጣን የሚሰነዝርበት ቁጣና ዘለፋ ደግሞ ያኮስሰዋል። “አንተ፣ ዋ፣ ገንዘቤን መጫወቻ አደረከው አይደል” የሚለው በየቀኑ በስልክ የሚሰማው የቱባው ሙሰኛው አለቃው ድምጽ ያስበረግገዋል። ሰዎች ኃብታም እየመሰላቸው በየምርቃቱና ስብሰባው የሚጋብዙት ይህ “ተስፈኛ” እየዛቀ የሚለግሰው ገንዘብ ጭብጨባ ብቻ አይደለም ታላቅ ቁጣና ዛቻንም ያስከትልበታል። እንደ አውሮፕላን የምትበር ዘመናዊ መኪና የገዛው “ተስፈኛ” ከፊት ለፊቱ በርካታ ሰዎችን ሲመለከት ልቡም እንዲሁ በስጋት ትበራለች። ታድያ ሙስና ላይ የሚደረገው ውጊያ እንዲከሽፍ በማድረግ ረገድ ደግሞ ከቱባው ሙሰኛ ባለሥልጣን የበለጠ ትግል ያደርጋል። ተስፈኛው ለሙሰኛ ገዢ ኅልውና ሲል በጽናት የሚታገል ባርያ ነው። የዚህ ዓይነቱ የመደብ ትግል በታሪክ የመጀመርያው ነው። የተስፈኛ የምጣኔ ኃብት ዘርፍን የፈለሰፈው ሂትለር ባይሆንም እንኳን እርሱ ግን በከፍተኛ ደረጃ በሥራ ላይ አውሎታል። ሂትለር ከእስራኤሎች ተሰብስቦ በአራት ማዕዘን እየተጠፈጠፈ ያሰራውን ወርቅ ስማቸው ለማይታወቅ ሰዎች አድሏል። እነዚህ ተስፈኞች በሂትለር የመጨረሻዎቹ የጭንቅ ሠዓታት ወደ ውጭ ሃገር በተለይም ወደ ደቡብ አሜሪካ ሸሽተዋል። እነዚያ ሰዎች እስከቅርብ ቀን ድረስ እየታደኑ ቢያዙም እስካሁን ያልታወቀ ኃብትም በወራሾቻቸው ስም በየሃገሩ ይገኛል። “ተስፈኛው ባለሃብት” ኃብታም ለመሆን ሲል ባዶ ተስፋን ሰንቆ የሙሰኛን ኃብት ተሸክሞ የሚዞር “ማሞ ቂሎ” ሰው