ጥቅምት 2009
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የደረሰው ውድቀት ያሳሰባችሁ፤ ይህ ውድቀት ከመግባቱ በፊት የነበረውን የጥንቱን የጉባዔውን ትምህርት የተማራችሁ ወገኖች ይህች የጥሪ ድምጽ ትደረሳችሁ።
ለዚህች ጥሪ ምክንያት የሆነን ሰሞኑን አባ ፋኑዔል ለሲኖዶሱ አቅርበው ባስወሰኑት፤ አባ መአዛም “ግእዝ እናውቃለን የምትሉ ሁሉ ተመልከቱት” እያሉ ያቀረቡት ከኛም ተሻግሮ ሌላውን ሁሉ በማነጋገር ላይ ያለና ሁሉንም ያሰቀቀው ጉዳይ ነው። “እንደ ባእድ ዝም ብላችሁ ትመለከታላችሁ” እያሉ በተለያዩ ቦታወች ከሚኖሩት ወገኖቻችን በተከታታይ ከደረሰን ጥያቄ ጋራ፤ ያስተማሩን የጉባዔው መምህሮቻችን ይህ ፈተና ቢገጥማቸው ምን ይሉ ነበር? የሚለው ተደምሮ እንቅልፍ አሳጥቶናል።
ቅዱስ ጳውሎስ “እኔ የጻፍኩላችሁ ስለ በደለው ወይም ስለተበደለው አይደልም. . . .”2ኛ ቆሮ 7፡12)እንዳለው፦ያቀረብናት ጥሪ የበደለውን የተበደለውን አትመለከትም። ይህን ከመሰለ ከባድ ሀላፊነት ውስጥ ስንገባ፤ ከበዳይም ከተበዳይም የተለየን ንጹሀን ነን፤ ወይም በቤተ ክርስቲያናችን ካሉት ሊቃውንት እንበልጣለን ብለንም አይደለም። በቤተ ክርስቲያችን ላይ የደረሰውን ፈተና በመካፈል ድርሻችንን ለመወጣት ብቻ ነው።
ምንም እንኴ አሁን የተከሰተው ውዝግብ ከዚህ በፊት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ከደረሱት ውዝግቦች የከፋ ባይሆንም፤ ከመሰረቱ ጀምሮ እየተማርን አደግን የሚለውን ሁሉ የሚፈትን ነው።
ሲኖዶሱ ያቀረበውን መግለጫ የተከታተልን፤ አባ መአዛ ያቀረቡትንም ጥሪ የሰማን ይመለከተናል የምንል ሁላችንም፤ በተለይም ለኛ እንደደረሰን “ለምን እንደ ባእድ ቆማችህ ትመለከታላችሁ” የሚል ጥያቄ የደረሳችሁ ካላችሁና፤ የጉባዔውን ትምህርት በጥልቀት እንረዳለን ለምንል ይህን ፈተና ዝም ብለን ማለፍ ተገቢ መስሎ የሚታይ አይደለም። በበኩላችን ሀላፊነታችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል። በቤተ ጅርስቲያናችን ይህ ፈተና ከመግባቱ በፊት የነበረውን ከመሰረቱ ጀምሮ እየተማርን አደግን የምትሉ ሁሉ፤ ጉዳዩን ከኛ ጋራ ለማየት ፈቃዳችሁ ከሆነ ከዚህ በታች ባሰፈርናቸው ስልክ ቁጥራችን ግለጹልን።
”እግዚአብሔር ያብርህ አዕይንተ አልባቢነ“
ወገኖቻችሁ ፦ሊቀ ማእምራን ዶ ክተር አማረ
ቀሲስ አስተርአየ
240 374 2816
913 371 4422