ኢትዮጵያን ከመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማውጣት ፕሮጄክት – (ሉሉ ከበደ)

በ 2017 ኢትዮጵያ ስሟ ከመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲሰረዝ ዋናውን ስራ የሰራው ኢትዮጵያዊ በኩራት ምክንያቱን ይነግረናል የኢዮጵያ ገዳዮቿ ልጆቿ እንዴት ሊሆኑ ቻሉ? ስንት ሺህ ዘመን ስንት ሺህ ወራሪዎችን አሳፍራ ፤ስንት መቶ ጦርነቶችን አካሂዳ ያልተንበረከከች፤ ተገንብታ እዚህ የደረሰች ምድር፤ ከአብራኳ በወጡ የበሰበሱ ልጆቿ ክፋት ለመውደቅ በቃች።ዛሬ ኢትጵያ ወድቃለች። መንግስት የላትም። ሉአላዊነቷ ተደፍሯል። ህዝቧ ጠባቂ አቶ ለጥቃት ተጋልጧል። ተሰቃይቷል።ተለያይቷል። ይህን ሁሉ አደጋ ያመጡባት ባእዳን አይደሉም። ልጆቿ ናቸው።

አንዲት እኔ ዘወትር በኢትዮጵያ የምመስላቸውን እናት እውነተኛ ታሪ እነሆ። እኒህ እናት ስምንት ልጆች ወልደዋል ። ሰባቱ ልጆቻቸው የተባረኩ ፤ የተመሰገኑ ፤በግብረገብነትና በፈሪሃ እግዜብሄር የታነጹ በመሆናቸው በሰፈር ፤ በትምህርትቤት በሁሉም አቅጣጫ ተወዳጅና ተቀባይ ነበሩ። መጨረሻ ላይ የተወለደው ስምንተኛው ልጃቸው ግን ከቤተሰቡ ለየት ያለ ባህሪ ይዞ ብቅ አለ። ከህጻንነቱ ጀምሮ ውሸታም ፤ ነውጠኛ፤ አታላይ ፤ሌባ ፤ተደባዳቢ ሆነ። ለትምህርትም አስቸጋሪ ሆነ። ቅጣት የማይበግረው ሞገደኛ ሆኖ አረፈው። ስምንትና ዘጠኝ አመት ሆኖት የመንደሩ ህጻናት ጨውና ስኳር እንዲገዙ ሱቅ ሲላኩ መንገድ ላይ እየጠበቀ ፍራንክ ቀምቷቸው ይሮጣል።ሰው ሁሉ የሚረግመውና የሚያዝንበት ልጅ ሆነ።ከቤቱም ከጎረቤቱም ያገኘውን ሁሉ የሚሰርቅ ሆነ። አድጎ ወደህብረተሰቡ ሲቀላቀልም ስራው ሁሉ ከህግ ጋር የሚያላትመው ሆነ። እናቱ ታዲያ በዚህ ልጅ በጣም ያዝናሉ ። ያለቅሳሉ። ስንት ልጆች እንዳላቸው ለጠየቃቸው ሰው ሁሉ “ስምንት ወልጄ አንድ አገማሁ” ይላሉ።ገማብኝ የሚሉት ይህን የተበላሸውን ልጅ ነው። ዶሮ እንቁላል ታቅፋ ጫጩት ያልሆነው እንደሚገማባት ማለት ነው። ኢትዮጵያም ታዲያ ወልዳ ወልዳ ያገማቻቸው ልጆቿ የሚያጠፏት ሆኑ።

ሰሞኑን ኢትዮጵያ ካገማቻቸው ልጆቿ መካከል አንዱ ከጀርመኖች ጋር ተስማምቶ ስሟ ከመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲሰረዝ አድርጓል። ይህ ሰው በቅርቡ የዶክትርና ትምህርቱን የጨረሰ የጀርመን ኢቫንጀሊካን ቤተክርስቲያን ፓስተር ነው። ዶክተር በንቲ ኦጁሉ ይባላል። በ2017 የታተመው የጀርመን ኢቫንጀሊካን ቤትክርስቲያን መጽሃፍ ቅዱስ ታርሞ ባዲስ ተተረጎመ ሲባል የኢትዮጵያ ስም እንዲወጣ ዋናውን ስራ የሰራው ይህ ሰው ነው።ስለ ድርጊቱም በኩራት ይናገራል።”ኦፕራይድ ” ለሚባል ድረገጽ ጋዜጠኛ መርጋ ዮናስ በእንግሊዝኛ ጉዳዩን አስመልክቶ ከሰውየው ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርጓል። ቃለ ምልልሱን ውዱ ወዳጄ እና የሙያ ወንድሜ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ከአመስተርዳም አድርሶኛል። እኔም አንብቤ ዝም ማለቱ አይጠቅምም አልኩና ይህን ቃለ ምልልስ ለሁላችንም በቀላሉ እንዲገባን ብየ ከእንግሊዝኛ ወደአማርኝ በመመለስ ላካፍላችሁ ወደድኩ።ሁሉም እንዲያቀው ሼር ብታደርጉት ደስ ይለኛል። ወደ ቃለ ምልልሱ እንግባ።

መርጋ :፤የዶክትርና ትምህርትዎን በማጠናቀቅዎ እንኳን ደስ ያለዎት ልልዎ እወዳለሁ። የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሁፍዎ እንደሰማሁት “የኦሮሞ ሃገር – በቀል( ነባር ) ሃይማኖትና የኦሮሞ ክርስትና ፤ የሚቃረኑ ወይስ የሚስማሙ ፤( አብረው መጓዝ የሚችሉ) ” በሚል ርእስ ላይ ያተኮረ ነው።ይህን ርእስ ለመምረጥ ምን አመላከቶት? የሚቃረኑባቸው ነገሮች ምንድናቸው የሚስማሙባቸውስ?አንድ የሚያደርጋቸው።

መልስ፤ከዚህ ፕሮጀችት ጀርባ ያለው ምክንያት ብዙ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች፤ ኢቫንጀሊካኖች እና ፓስተሮች የኦሮሞ ህዝብ ስለ እግዜብሄር ሃሳቡ ፤ እውቀቱ የለውም እና ሃይማኖታቸውም በጣኦት ማምለክ ወይም በሴጣን ማመን ነው ብለው ይገምቱ ነበር። በአካባቢ አህጉራችን የክርስትናና እስልምና ሃይማኖት ከመምጣት በፊት የነበረውን የኦሮሞ ሃገር በቀል ሃይማኖት መመርመር መመልከት ጀመርኩ። ስለዚህ ከስነመለኮት እይታ አኳያ የመመረቂያ ጽሁፌ የማነጻጸር ሃይማኖታዊ ጥናት ነው። እመለከት የነበረውም ነገር የኦሮሞ ነባር ሃይማኖት ከክርስትና ጋር ይጻረራል ወይስ ይስማማል የሚለውን ነው። በጥናቴ ወቅት በኦሮሞ ነባር ሃይማኖት (ዋቄፈታ) እና በክርስትና መካከል ብዙ ተመሣይነትና ጥቂት ልዩነቶችን አግኝቻለሁ። ደስ የሚል ግኝት ነው።የእስልምናም የክርስትናም ሚሽነሪዎች የኦሮሞ ነባር ሀይማኖት ከነሱ እምነት የተለየ ነው ብለው ይገምቱ ነበር።የሆነሆኖ በብዙ መንገድ ምንም ልዩነት የሌለው ሆኖ አግኝቸዋለሁ። እግዜብሄር ከሚለው መጠሪያ ጀምሮ ይታያል። እግዚአቤር በኦሮምኛ “ዋቃ” ወይም “ዋቀዮ” ይባላል። ምድርና ሰማይን የፈጠረ። ከእስልምናም ሆነ ከክርስትና መምጣት በፊት ኦሮሞ ለረጂም ጊዜ የሚያምንበት ነው። መጽሃፍቅዱስን ወደ ኦሮሞኛ የተረጎሙ የተጠቀሙበትም ይኸው ቃል ነው።” God” የሚለውን “ዋቃ” በሚለው በመተካት።እና ዋቃ የሚለው ስም በመሰረቱ ከክርስትና ሳይሆን ከኦሮሞ ነባር ሃይማኖት የተወሰደ ነው።እንዲህ ወደ ዝርዝሩ ከገባህ ጥቂት ልዩነት ብዙ ተመሳሳይነትን ታገኛለህ። ጥናቱን ለማካሄድና ለመጻፍ ብዙ ጊዜ ወስዷል። የሆነው ሆኖ አሁን የመመረቂያ ጽሁፉን ጨርሻለሁ።ዲሴምበር 2016 ሒልደሺም ዩኒቨርሲቲ ቀርቧል። ጥናቱን አስመልክቶ የቀረቡ ፈታኝ ጥያቄዎችን ክርክሮችን ጁን 2017 በተሳካ ሁኔታ አስተናግጃለሁ።

ጥያቄ፤ እርሶ እያገለገሉ ያሉበት ቤትክርስቲያን ኢቫንጀሊካል ደችላንድ አዲስ መጽሃፍ ቅዱስ አሳትሟል።ቀደም ሲል በነበረው ቅጂ ውስጥ ስህተት እናም ጊዜ ያለፈባቸው ናቸው ያላቸውን ትርጓሜዎችና ቃላትን አርሟል።
“ኢትዮጵያ ” የሚለውን ቃል “ኩሽ” በሚለው መቀየርን ያጠቃልላል። ከዚህ የስም ለውጥ በስተጀርባ እንደምክንያትነት የሚቀርበው ምንድነው ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  በግሎባል የምሁራን መድረክ ላይ የምዕራቡን ካፒታሊዝም የፖለቲካ አስተሳሰብና አካሄድ በሚመለከት በፕሮፌሰር መሳይ ከበድና በዶ/ር ዮናስ ብሩ ኢ-ሳይንሳዊ በሆነ  መልክ የተሰነዘረውን አስተሳስብ የሚቃወም ትችታዊ አቀራረብ!

ዶክተር በንቲ፤ መልካም ። የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እየተካሄደ ያለ ነገር ነው። ከየትርጉም ስራው ጀርባ ያለው ሃሳብ በቀድሞዎቹ ህትመቶች ውስጥ የተወሰኑ ጉድለቶችና ግድፈቶች ይኖራሉ የሚል ነው።የተለያዩ የመጽሃፍቅዱስ ማህበረሰቦች መጽሃፍ ቅዱስን ሲተረጉሙ ኖረዋል። ይህ የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ማርቲን ሉተር መጽሃፍ ቅዱስን ከ ላቲን ወደ ጀርመንኛ ከተረጎመበት ጊዜ ጀምሮ የቋንቋና የሃሳብ ትርጉም እየተካሄደ እንዳለ ነው።በነዚያ ትርጉሞች ውስጥ ስህተቶችነበሩ።አንዳንዶቹ የቋንቋ ሊሎቹም ግንዛቤያዊ ነበሩ። አሁን እየተካሄደ ያለው ትርጉም ምክንያቱ እነዚያ ያለፉ ስህተቶች ናቸው ። እነሱን ማረም ነው።

ለምሳሌ ግሪኮች ብሉይ ኪዳንን ከሂብሩ ቋንቋ ወደ ግሪክ ሲተረጉሙ “ኩሽ” የሚለውን ወደ “ኢትዮጲስ” በመቀየር ስህተት ሰሩ።ኩሽ የጥቁር አፍሪካ ህዝብ ስም ነበር ወደ ኢትዮጲስ የተለወጠ ። ትርጉሙ “ፊቱ የተቃጠለ ህዝብ” ማለት ነው። ኩሽ በመሆንና የተቃጠለ ፊት በመሆን መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። ጥቁር ህዝቦች ፊታቸው የተቃጠለ አይደለም።ጥቁሮች ናቸው በቃ። ይህ አዲሱ በጀርመን ኢቫንጀሊካን ሉትራን ቸርች በ2017 የታተመው መጽሃፍ ቅዱስ እነዚያን ስህተቶች በማረም ነው ማለት ነው።

በአሮጌው የመጽሃፍ ቅዱስ ቅጾች ውስጥ “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል 45 ጊዜ ተጠቅሷል። እነዚህ ቃላት እንደ ስህተት ተወስደው ኩሽ ወደሚለው ወደቀድሞ ተክክለኛ ቃሉ ተለውጠዋል። ግልጽ ለመሆን የ2017 ትርጉም ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ብቻ አይደለም የቀየረው። ብዙ ቃላትና ያገባብ ስህተቶችን አርሞ ተርጉሟል።በተለይ “ኢትዮጵያ” የሚለው ወደ “ኩሽ” መቀየሩን የሚያስደስት ሆኖ አግኝቸዋለሁ።ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያ በመጽሃፍ ቅዱስ በመጠቀሷ የምንኮራ ነበርን። እውነታው ግን የግሪክ ተርጓሚዎች በስህተት የህዝብ ስም ነው ብለው አስበው ነበር።አሁን ያ አለመሆኑን አውቅን። ለኩሽ ህዝብ የተሰጠ ክብር የሚነካ የሚያዋርድ መጠሪያ ነበር(Derogatory)። በጀርመን ኢቫንጀሊካል ሉትራን ቸርች ይህ ተለይቶ መታወቁን በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ጥያቄ፤ ቤተክርስቲያንዋ ሌሎች ለውጦችንም ማድረጓን ጠቅሰዋል። ምንድናቸው?

መልስ፤ በአዲሱ እትም ወደ መዝሙረዳዊት 68 : 31 የሄድክ እንደሆነ “ኩሽ እጆቿን ወደ እግዜብሄር ትዘረጋለች” ይላል። በቀድሞው ትርጉም ውስጥ ግን ” ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዜብሄር ትዘረጋለች ” ነው የሚለው። ከኢትዮጵያ ወደ ኩሽ ከተለወጡት 44 አረፍተ ነገሮች አንዱ ነው። ተርጓሚዎቹ አንድ ወይም ሁለት “ኢትዮጵያ” የሚለው ቃል ያልተለወጠበት ሀረግ ረስተዋል።የሆነሆኖ ይህንንም ከነሱ ጋር ተወያይተናል። በቅርቡ ይታረማል።ለምሳሌ በኤርሜያስ 13:23 ውስጥ ያለው አንዱ ሳይተረጉሙ የረሱት ነው። በእንግሊዝኛው ትርጉም ” ኢትጵያዊ ቆዳውን ነብር ዥጉርጉርነቱን ይቀይራልን?” ይላል። እዚህ ላይ “ኢትዮጵያ ” የሚለው ቃል ፈጽሞ ሊጠቀሙበት የማይገባ ስድብ ነው(Insult).። የትርጉም ለውጡ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ብዙ የስም ለውጦችን ያጠቃልላል። አሁን ልነግራቸው የማልችል ቦታዎችን ጽንሰሃሳቦችን ሁሉ።
ጥያቄ ፤ በስነ መለኮትም ሆነ በሌላ ማናቸውም ከፍተኛ ትምህርታዊ ምሁራዊ ስራዎች ላይ ይህን መሰል ለውጦች ሲደረጉ ማጠቃለያ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት ጥናቶች መካሄድ አለባቸው።የጀርመን ኢቫንጀሊካል

ቤተክርስቲያን ቃላቶችንም ሆነ አገባባቸውን ከመቀየሯ በፊት በቂ ጥናት አካሂዳለች?

መልስ፤ እርግጥ። የጀርመን ኢቫንጀሊካን ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ያስተዳደር አካል ፤ የትርጉም ስራውን እንዲያካሂድ አንድ የምሁራን ቡድን መደበ።የቋንቋ ጠበብትንና የመጽሀፍ ቅዱስ ሊቃውንትን ያቀፈው ግብረሃይል በ2010 ተቋቋመ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ትርጉሙን ሲሰሩ ቆይተው የመጨረሻ ውጤታቸውን ለቤተክርስቲያን መሪዎች አቀረቡ።የቤተክርስቲያን መሪዎችና ጉባኤተኞች አዲሱን ትርጉም አነበቡ።አስተያየታቸውንና እንዲህ ቢሆን የሚል ሃሳባቸውን ሰጡ። እንግዲህ ለሰባት አመታት ቁጥራቸው የበዛ ኤክስፐርቶችና ምሁራን በዚህ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።ይህ አዲስ ቅጂ የታተመው የሉተርን ተሃድሶ 500 ኛ አመት ለማሰብ ነው።ከ ኦክቶበር 31 – 2016 እስከ ኦክቶበር 31-2017 የሚውለውን ክብረበአል ለመዘከር። በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት ሰዎች የበቁ የስነመለኮት ሰዎች፤ፈላስፎች፤የስነቋንቋ ጠበብት፤በሂብሩ፤ በግሪክ፤ በእንግሊዝኛ በጀርመንና በሌሎችም ቋንቋዎች የበቁና ከፍተኛ እውቀት ያካበቱ ናቸው።

ጥያቄ፤እስቲ ስለ ጥናቱ ሂደት ጥቂት ያብራሩልኛል? እና አጥኚዎቹ ምሁራን ግኝታቸውን ለማን እንዳቀረቡ?

መልስ፤አጥኒዎቹ ትርጉሙን የሰሩት አሮጌውን መጽሃፍ ቅዱስ መሰረት በማድረግ ነው።አዲሱ የትርጉም ስራ ይሁንታ ከማግኘቱ በፊት የሚያልፍባቸው በርካታ ደረጃዎች አሉ።መጀመሪያ ግለሰብ ኤክስፐርቶች የትርጉም ስራውን ያካሂዱና የሌሎች ኤክስፐርቶች እና የቤተክርስቲያን መሪዎችን ቡድን ላቀፈው ግብረሃይል አዲሱን ትርጉምና አሮጌውን መጽሃፍ ቅዱስ ያቀርባሉ። ይህ ግብረሃይል የራሱን አስተያየትና የእርምት ሃሳብ ከሰጠ በኋላ አዲሱም ጥንታዊውም መጽሃፍ ቅዱስ ለጳጳሱ ና በመላ ጀርመን የሚገኙ የኢቫንጀሊካን ቤተክርስቲያን ተወካዮች ለተሰየሙበት ጉባኤ ይቀርባል። ጉባኤውና ጳጳሱ አዲሱን መጽሀፍ ቅዱስ የሚያጸድቁ ፤የሚያሳትሙና የሚያሰራጩ ከፍተኛ አካላት ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ንብረት የማፍራት መብት መገለፅ ያለበት በብሔረሰብ ደረጃ ሳይሆን በግለሰብ ነው” (አቶ ተክሌ በቀለ)

ጥያቄ፤ይህ ትርጉም ይህ ለውጥ በኢቫንጀሊካን ቤተክርስቲያን ተከታዮች ዘንድ ምን አይነት ምልከታ ይኖረዋል ብለው ያስባሉ?

መልስ፤ በጀርመን ያሉ የፕሮቴስታንት ቤተክርስትያናት በአዲሱ ትርጉም ደስተኞች ናቸው።የተወሰኑ ስህተቶች ታርመዋል።ትክክለኛ ቋንቋ በመጠቀም ልዩነትን የሚፈጥሩ ቃላትን በመቀየር ቤተክርስቲያኗ መጽሀፍ ቅዱስን የተሻለ ለማድረግ ትሞክራለች።የፕሮተስታንት ቤተክርስቲያን ተከታዮች በጣም ደስተኞች ናቸው ።አሁን መጽሀፉን በየጉባኤው ላይ እንጠቀምበታለን።

ይህ አዲስ መጽሀፍ ቅዱስ የፕሮተስታንት ቤተክርስቲያን መጽሃፍ ቅዱስ ነው።የካቶሊክ ወይም የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አይደለም።ኦርቶዶክስና ካቶሊክ ቤተክርስቲያኖች የየራሳቸው መጽሃፍ ቅዱስ አላቸው። ፕሮተስታንቶች 66 መጽሃፍት አሏቸው በመጽሃፍ ቅዱስ ስውጥ፤ካቶሊኮች 73 እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን 81።እንግዲህ እኔ አሁን እዚህ የማወራው በመላው አለም ሁሉ ያሉ ክርስቲያኖች ስለሚጠቀሙበት የፕሮተስታንት ቤተክርስቲያን መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ነው።

ጥያቄ፤የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን”ኢትዮጵያ” የሚለውን ቃል ስህተት ሆኖ አግኝታው ከመጽሀፏ ውስጥ ስታስወግድና ስትቀይር ፥ የካቶሊኮችና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ የማመልከት የማሳሰብ ሙከራ ይኖራል?

መልስ፤መልካም። የፕሮተስታንት ቤተከርስቲያን የአለም ቤተክርስቲያናት ምክርቤት አካል ናት።ይህ ትርጉም ለክርስቲያኖች ሁሉ የጋራ መሆን እንዳለበት እናምናለን።ምክንያቱም መሰረታዊውን የክርስቲያን እምነት የሚቀበል ነው። እውነትን መሻት ነው።እውነት ይፋ ሆናለች። እውነትም ተጽፋለች።ስለዚህ ኦርቶዶክስና ካቶሊክ አቢያተክርስትያናት ፤የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያናት እንደ ትክክለኛ የመጽሀፍ ቅዱስ ትርጉም ይህን ይቀበላሉ ብለን እናምናለን።ምክንያቱም ለሁላችንም የጋራና መሰረታዊ በመሆኑ። እኔ ባመራር ደረጃ ያለ ስልጣን ላይ እይደለም ያለሁት። የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን እመራሮች ይህን ሀሳብ ለሌሎች ክርስቲያን ቸርቾች ሁሉ እንደሚያቀርቡ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ኦርቶዶክስና ካቶሊኮችን ጨምሮ።

ይህን አዲሱን ትርጉም ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል መወሰን የኦርቶዶክሶችም ሆነ የካቶሊክ ቤተክርስቲያናት የራሳቸው ጉዳይ ነው። እኛ በትክክለኛ ቋንቋ የተቀመጠ መጽሀፍቅዱስ ነው የምንጠቀመው። ለዚህም ነው ፕሮቴስታንት የተባልነው። እኛ ከሁሉም አቢያተክርስትያናት ጋር እንሰራለን ከሁሉም ጋር እንከባበራለንም። ግን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ እንበልና ኩሽ ህዝቦች ውስጥ ሄደው መስራት ከፈለጉ ኦሮሞ፤ሲዳማ ፤ከምባታ፤አገው ፤ሃዲያ፤ሶማሌ እና ሌሎችም፤ቤተክርስቲያኗ ይህን አዲሱን ትርጉም መቀበል አለባት።በሁለት ምክንያቶች ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ያን እንደምታደርግ ተስፋ አደርጋለሁ። አንደኛ ፤ ትክክለኛው ስም “ኩሽ” ነበር እንጂ “ኢትዮጵያ” አይደለም። ሁለተኛ ፡ ከአንድ ክፍለ ህዝብ ጋር ወይም ከአንድ ሀገር ህዝብ ጋር የምትሰራ ከሆነ የዛን ህዝብ ባህሉን፤ ማንነቱን ማክበር አለብህ። ስለዚህ ኩሽ ህዝብ ውስጥ ሄደው የሚሰሩ አብያተክርስትያናት ሀላፊነት ነው ያን ስህተት አውቆና አርሞ መገኘት።

ጥያቄ፡ ይህ ለውጥ ወይም ይህ ትርጉም በራሳቸው በኩሽ ህዝቦች ላይ ምን አይነት ስነመለኮታዊ ለውጥ ያመጣል ብለው ያስባሉ?

መልስ፡ መልካም። ትልቅ ለውጥ ይኖረዋል። ሰዎች ጥያቄ መጠየቅ አለባቸው።” ማነው እጆቹን ወደእግዚአብሄር የዘረጋ?” ኢትዮጵያ እይደለችም ። ግን ኩሽ ነው። በጭፍን ኢትዮጵያ ናት ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ሊቀበሉት ይፈታተናቸዋል። እውነት ትፈታተናለች። ነጻ ግን ታወጣለች።ክርስቲያን ሰባኪዎች ቃሉን እንዴት እንደሚተረጉሙና እንሚጠቀመበትም ለውጥ ይኖረዋል። እንደ ፓስተር እኔ ቆሜ ይህ ኩሽ ነው ስል ይህን ለመስማት የማይፈልጉ ላይቀበሉት ይችሉ ይሆናል ። ግን ምክንያትና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ለምን እንደማይቀበሉት አስረጅ። ስለዚህ ሰዎች ይህን ለመረዳትና ሊቀበሉት ጊዜ ይወስድባቸዋል። ከፊሉን ሊያወዛግበው ከፊሉን ነጻ ሊያወጣው ይችላል። አንዳንዶች በትርጉሙ ደስተኞች ሆነው ይጠቀሙበታል ሌሎች ደስተኛ አይደሉም ይሆናል። የኔ ተስፋ ሁሉም ክርስቲያን ቸርቾች አዲሱን ትርጉም በደስታ ይቀበሉታል ነው። የተደበቀው አውነት ይፋ ሆኗል። ስለ ዚህ ሁሉም ሰው ደስተኛ ሊሆን ይገባል። መጽሀፍ ቅዱስን ከሂብሩ ወደ ግሪክ የተረጎሙት ሰዎች ለምን “ኢትዮጲስ” አሉን? ፤ፊታቸው የተቃጠለ ሰዎች” “ የተቃጠለ ፊት” የሚለው መጠሪያ ክብረ ነክና አዋራጅ ስድብ ነው። ፊታችን የተቃጠለ አይደለም። ጥቁር ነው በቃ። ጥቁር መሆን ምንም ስህተት የለበትም።አግዚ እብሄር ነው የፈጠረን። ጥቁሮች ነን ። አንደጥቁርነታችን አራሳችንን አንቀበለዋለን። ማናቸውም ቤተክርስቲያን እኔን ቢሰድበኝ ቤተክርስቲያኔ አልለውም። ይህ የማንነት ጉዳይ ነው። አባትህ ያወጣልህ ስም በባእዳን ቢለወጥ ያናድድሀል ። ማንነትህን ባህልህን ሁሉ ያወድመዋል። አዚህ የሆነው ነገር በትክክል ይህ ነው። የኩሽ ህዝቦች አራሳቸውን የተቃጠለ ፊት ክብለው አይጠሩም።

ኦሮሞ ፤ ሶማሌ፤ አፋር፤ እና ሌሎችም የኩሽ ህዝብቦች መሆናቸውን ታሪክ ይነግረናል። አንድም የገባው ፤ የተገለጠለት የኩሽ ሰው ግሪኮች ለኛ በሰጡን ክብረነክ አዋራጅ ስም ደስተኛ አይደለም።የመጀመሪያው ስማችን ኩሽ መጠሪያችን እንዲሆን መልሰን ለመጠየቅ ደስተኞች ነን።ስለዚህ ለውጡ ይህ ነው።እንዳለ የኩሽ ህዝቦችን ታሪክ በትክክል ሊቀይረው ይችላል።የኩሽ ሰዎች ቋንቋዎች አሏቸው እና የሚኖሩበት መልክአምድራቸውም በደንብ የታወቀ ነው። ግን ኢትዮጵያ ከሚለው ቃል ጋር የሚዛመድ ህዝብም ፤ ቦታም ፤ ቋንቋም የለም። ባንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የኢትዮጵያ ጥናት እንዳለ እሰማለሁ።መጨረሻ ላይ ይሄም ይቀየራል።ምክንያቱም ጥያቄ ያስነሳል።ኢትዮጵያ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ እውነትና ፍትህ ከትቢያ የተሻለ ቦታ ቢኖራቸው ኖሮ….   አንዷለም አራጌ

ማነው?ኢትዮጵያ ምንድነው?

ጥያቄ፤ በኢትዮጵያ በትምህርት ላቅ ባሉ (elite) ክፍሎችም ሆነ በሌላው ማህበረሰብ ዘንድ ማንነትን በተመለከተ የተጋጋሉ ክርክሮች ይስተዋላሉ።ብቸኛው ማንነታችን “ኢትዮጵያዊነት” ነው ብለው የሚከረከሩ አሉ።በሌላው በኩል ደሞ ቀዳሚው የጎሳ ማንነታችን ነው ኢትዯጵያዊነት ሁለተኛ ደረጃ ነው ብለው የሚከራከሩ አሉ።ሌሎች ደሞ ጭራሽ ባጠቃላይ ትዮጵያዊ ማንነትን የማይቀበሉ አሉ። ለዚህ አነጋጋሪ ለሆነው የማንነትጉዳይ ይህ አዲሱ

ትርጉም አስተዋጾ ይኖረዋል ብለው ያስባሉ?

መልስ፤ እውነት ነጻ ያወጣሃል ብየ አስባለሁ።የመጀመቲያው ስም “ኩሽ” ለመሆኑ ማስረጃ እስካለ ድረስ ቃሉ “ኢትዮጵያ” ነው ብሎ የሚያከራክር ምክንያት የለም።”ኢትዮጵያ” ብለው ሊጠሩን ያስቻላቸው ሳይንሳዊ ማስረጃ አያገኙም ይሆናል።ሳይንሳዊ ስል የአርኪዎሎጂ የስነቋንቋ እንዲሁም የታሪክ ማስረጃዎችን ማለቴ ነው።አሁን ስላለችው ኢትዮጵያ ታሪክ እንድነግርህ ፍቀድለኝ። ከ1900-1908 እስከዚህ ጊዜ ድረስ የዛሬዪቱ ኢትዮያ ስነ መልክአምድር (ካርታ) አልነበረም።ከዚያ በፊት ህዝቡ ኦሮሞ፤አማራ፤ሲዳማ ፤ አፋር፤ትግሬ ወዘተ….ይባሉ ነበር።

አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ካርታ ዳር ድንበር የተቋቋመው ፤ የተመሰረተው ፤ በዳግማዊ ሚኒሊክ የአቢሲኒያው ንጉስ ነው።የደቡብን ኩሾችና ሌሎችንም በቅኝ የያዘውና አሁን ያለችውን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ግዛት የፈጠረ።እስከ 1931 ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ህጋዊ እውቅና አላገኘም ነበር።ከ1931 አም በፊት ሃገሪቱ አቢሲኒያ ነበር የምትባለው። እና አቢሲኒያውያን እራሳቸውን የሴም ህዝብ ብለው ነው የሚጠሩት።ንጉስ ሃይለስላሴ ናቸው በ1931 አም በመጀመሪያ ህገመንግስታቸው ውስጥ አቢሲኒያ የሚለውን ስም ጥለው ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ያጸደቁት።

ኩሽና ሌሎችም ህዝቦች በዚህ የአፍሪካ አህጉር ለሺዎች አመታት እየኖሩ በነበረበት እንግዲህ ጥያቄው እንደምን አንድ ሃገር እንዳለ ስሙ ተለውጦ “ኢትዮጵያ” ይባላል? መልካም ። ግሪኮች “ኢትዮጲስ” አሉ፤ ምክንያቱም ህዝብ ኢትዮጵያ ስለሚባል ግዛት አፈታሪክ ያወራ ነበርና። በትክክልም የኩሽ ስለነበረ ግዛት። ስለ ንግስት ሳባ ነበር የሚናገሩት። ኩሽ እንጂ ሴማዊት ስላልነበረች ሰው። ግዛቷም የኩሽ ግዛት እንጂ ኢትዮጵያ አልነበረችም። የአካዳሚክ ሰዎች ፤ ታሪክ አጥኚዎች፤ የስነመለኮት ሰዎች (የሀይማኖት ጠበብት) ይህን በደንብ መረዳት አለባቸው።ፖለቲከኞች ደግሞ እውነትን መያዝና ያለፉ ስህተቶችን ማረም ይገባቸዋል። በጣም ብርቱ ነገር ነው። ስሜ በንቲ ነው። ስለዚህ ድንገት ስሜ ወደ ጄምስ ቢለወጥ ደስ አይለኝም።

የዘር የጾታ እና ማናቸውም አይነት ልዩነት መታረም ነው ያለበት።ለምሳሌ “ባሪያ ለጌታህ ታዘዝ” የሚለው ነገር መቀየር አለበት። ጥቁር የተረገመ ነው ለማለት ካምና ትውልዱ ተረግመዋል የሚል ጽንሰ ሃሳብ አለ።ስለዚህ የጥቂር ህዝብ ችግር ሁሉ የእግዜብሄር እርግማን ነው። ይህ መቀየር መወገድ አለበትእንዳለ። ምክንያቱም እግዜብሄር ጥቁሩን ህዝብ ረግሞታል ብየ አላምንም። ይልቅስ ተርጓሚዎች የጥቁሮች አባት ካምን የተረገመ ብለው ሲጠቅሱ በስህተት የተሞላ አድሎአዊነታቸው ነው። ካምን የረገመው እግዜብሄር የክርስቲያን አምላክ ሊሆን እንደማይችል አምናለሁ።ይህ ስህተት ሆን ተብሎም ይሁን በሌላ ምክንያት ይደረግ ፤ የመጽሃፍ ቅዱስን ቅዱስነት ውድቅ አያደርገውም።ነገር ግን ስህተቶችን ማረምና እውነተኛ በሆነ አሉታዊ መንገድ ማቅረብ የበለጠ መጽሃፍ ቅዱስን ያበለጽገዋል።

ጥያቄ፥ ያሉኝ ጥያቄዎች እነዚሁ ናቸው ሌላ የሚጨምሩት ነገር ካለ?

መልስ፤ ለጥያቄዎችህ አመሰግናለሁ። እውነትን ለመናገር ደስተኛ ነኝ እናም አዲሱን ትርጉም የሚያነቡ ሰዎችን ሁሉ የምጠይቀው ነገር እርምቱ እውነት አከሆነ ደረስ እንዳይደነግጡ ነው። ገንቢ በሆነ ውይይት መሳተፍና አዲሱን ትርጉም በሰዎች መካከል በሰላም አብሮ መኖር እንዲቻል አርገን ጥቅም ላይ ለማዋል መሞከር አለብን።ለውጡ አሉታዊ እርምጃ ሆኖ እንዲታይና በክርስቲያኖች ሁሉ ጥቅም ላይ እንዲውል ተስፋ አደርጋለሁ።
በመላው አለም የመጽሃፍ ቅዱስ ተርጓሚ ማህበረሰቦችም እነዚህንና ሌሎችንም ስህተቶች አርመው ለወደፊት በትርጉም ስራ ወቅት መድሎአዊ ቃላትን ለማስወገድ እንደሚሰሩ ተስፋ አደርጋለሁ።ሁሉን አቀፍ እንዲሆኑም አበረታታቸዋለሁ።ምክንያቱም እግዜብሄር የፍቅር አምላክ ነውና የፈጠረውን ሁሉ የሚወድ። በራሱ ፍጡራን መካከል ልዩነትን የሚፈጥርበት ምክንያት የለውም።
አማኞችም ለለውጥ ልቦናቸው ክፍት መሆን አለበት። በግልጽም ሊወያዩበት ይገባል። አውቃለሁ ሀይማኖት በጣም ስሜትን የሚነካ ነገር ነው። በመላው አለም ያሉ ሀይማኖቶች በሰላም ተቻችለው አብረው እንዲኖሩ ለማድረግ ሲባል፤መነጋገር አንዳችን ሌላችንን የመረዳት ልምድ ማዳበርና አሉታዊ አስተሳሰብን ማራመድ የሰው ልጅ ባህል አንዱ ገጽታ ነው። ያም ምኞቴና ጸሎቴም ነው።

10 Comments

  1. Dear editor,
    Thank you for sharing this annoying politically motivated bible interpretation story. By the way this is not the first time the enemies of Ethiopia have tried and succeeded to blot out the name our country from the word of God but not from the heart of God. It has been done before but not from among ourselves, I believe. It surprises me a lot why on earth a born again Christian would want to remove the name of his country from the bible unless his has a political agenda (Dr Banti). I don’t believe the Dr Banti story up until I could hear the story of real version of the translation mistake (if one exists) of “Land of Cush” to “Ethiopia”. The best confirmation for this probably would come from a scholar with multilingual capacity who would be able to compare the translation from ancient Hebrew script (old testament) to modern bible version as well as from Greek version of new testament (because Ethiopia is also mentioned in New testaments Act section where the Ethiopian Eunuch was instructed and baptized by an Apostele in the Gospel of Jesus when he was reading Isaiah 53) to modern bible version.
    To me, in terms of mapping the current geography of the flow of ancient Jewish and Christian religious practices (the early spread of Christianity), it well fits the translation to Ethiopia where we have one of the most ancient Christian and Jewish religion in the world. You find this nowhere in Africa. Therefore it is befitting to believe the reference in the bible is no other than Ethiopia. It is true much of our African ancestors were idol/devil/pagan religion worshipers if you look it from Christian perspective (this is not exceptional to Africa though; Asia is even worse and this also is common in the Christian west too, although no acceptable from Christian perspective).
    The wrong concept of our dirty Ethnic politicians, specially unprincipled, unhinged, self-centered, non-nationalist some Oromo elites and other Narrow Ethnizes (current regime included), is equating our Amhara or northern relatives as the sole Ethiopian Christians, 100% sematic descendants and ascribing the concept Ethiopian nationality solely to them while the rest of the world refers the country multiethnic multilingual originally Christian dominant country. Whether we describe ourselves as Cushitic or having some gene flow from Middle East that is not an excuse good enough to destroy the earliest symbol we have as a nation which is the country name Ethiopia. Listen, from Christian perspective (excluding non-Christians, atheistic views), according to bible, the strict name of God is not even wako (Oromo, Gurage), goita (Gurage, Tigrigna), Allah (Arabic)…etc (refer to Old Testament how God himself wanted to be called!). Personally, I don’t know if the Amharic “Egziabeher” has pagan origin or typically geez translation from Biblical name of God. None of these names could be equated with the bible names of God which are documented in the Old Testament. Therefore, the ancient pagan religious practices to Wako, erecha … the northern region ashenda… etc.. could never be compared to close to Christianity as these were pagan practices hated by the Christian God. I am ashamed of Dr Banti who as born again Christian was supposed to preach the gospel of Jesus to lost souls is delving himself into the ethnic politics, usurping the opportunity he has. Erasing Ethiopia as Christian nation won’t erase the country from the heart of God-he knows how we love him. For the haters, if you think some Ethiopians (Amhara, Tigreans, adere, gurage….) have sematic descent, remember, still most of their gene pool is Cushitic and the land you call yours is home to them and you can’t imagine otherwise. The sematic percentage is not big enough to send them back to Middle East or elsewhere. They did not migrate to where they are as some haters want to think. May be the gene flew in. Shame on you, you narrow ethinocrats (usually among Oromo’s and Tigre group who instead of producing a national agenda that would prosper the country and get us stage on world stage, bickering in the mud of their ethnic and backdated pagan practice). This time “Judas rising among ourselves”!

  2. Stern; Cool down.
    It is not the first time that the term Ethiopia is absent from Bible translations. The Bible, especially the Old Testament was originally written in Hebrew. You can’t deny this fact. And the Hebrew version contained Cush not Ethiopia. In the New International Version of the Bible, published in 1978 by a transdenominational group of scholars, stands “Cush” not “Ethiopia” in Psalms 68:31 and many other texts. In ኤርሜያስ 13:23,it used “Ethiopia” with a footnote “Hebrew Cushite (probably a person from the upper Nile region)”.
    Whether the term “Ethiopia” or “Cush” is used, reference at the time was to black people, especially those south of Egypt. A specific country called Ethiopia did not exist then. One of the then known powerful states was Aksum, and was known only as such. The church, that established itself as state religion in Aksum after 330 AD, started to usurp that name. So the naming of the church and the gradual use of the name in the titles of the rulers is inspired by the scriptures translated from the Greek. The name “Ethiopia” was adopted as official name of the country only in Haile-Selassie’s 1931 constitution. The country was registered as Abyssinia in the League of Nations, for example.
    Truth must be upheld, and the Christian Church must be exemplary in this regard.

    • @Galaaa
      Don’t worry about my cool down! We have enough issues that keeps us hot enough in that country any way.

      I have read few posts on your suggestion of the country was named Ethiopia by Selassie in the 30s. That does not seem to be agreed on that easy. I am not of history background but will be making a reading on that. I very well understand the name changing will not change the spiritual content of the bible. However, what I, as many Ethiopians, am unhappy about is this being used as political motivation. The interview provided/hence the translated version does not go well with another publication appearing at: http://quatero.net/is-the-term-ethiopia-changed-to-cush-in-the-new-bible.( See publication in Quatero). Mr Banti seems to have played minor role while he is exaggeratedly used perhaps for political consumption by the interviewer (OPRID site).
      As you tried to say that we should upheld the truth, which I agree but I don’t think your suggestion of Ethiopia as nation name appearing in the League of nation time does not compare with other’s opinion and would be happy to learn from historians (as I stated, obviously I am going to try to get more information for my own)
      Thanks

    • My apology was for unfortunate unintentional error in copy pasting. I wanted to say @Galaana but it got pasted as @Galaa which I saw later. Sorry for that mistake in my response.

  3. ኢትዪጵያ የሚለውን ስም ኩሽ በሚለው የጥቁር በቤተሰቦች ሁሉ ግንድ በሆነው ስም ሙሉ በሙሉ ለመቀየር የጀርመን የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን በዶክተር በንቲ ኡጁሉ ጥናት በመታገዝ ያከብናወነችው የመፅሃፍ ቅዱስ የትርጉም ስራ ቅሬታንና አለመግባባትን ሊፈጥር እንደሚችል ምናልባትም የፖለቲካ ግብ ያለውእንደሆነ በአንዳንዶች ይገመታል::ኢትዩጵያ የሚለውን ስም መጀመሪያ የተጠቀመው የሰፕቱጀንት ትርጉም ነው::(ሰፕቱጀንት የመጀመሪያው በእብራይስጥ ተናጋሪ ግሪኮች ከእብራይስጥ ወደ ግሪክኛ ትርጉም ስራ 280 BC) ኢትዪጵያ የሚለው ስም በሴፕቱጀንት ይጠቀስ እንጂ ጥንታዊ ስም ለመሆኑ በሆሜር ኢልያድ ሁለት ጊዜ በኦዴሲ ሶስት ጊዜ ተጠቅሶ እናገኘዋለን::
    ኢትዩ የሚለው ግሪክኛ ቃል light up kindle ማለት ሲሆን ግሱም ማንፀባረቅ ማብረቅረቅ የሚል ትርጉም ይሰጣል ::ቃሉ በጥንቱ የግሪክ ገጣሚ ሄሶይድ ሜታፎሪካሊ ተጠቅሞበት እናገኛለን:: እንግዲህ ኩሽ ወይም ኢትዩጵያ የሚለው ቃል ከሁለት ሺህ አመታት በላይ ከግብፅ ደቡብ አቅጣጫ ለነበሩ ህዝቦች መጠሪያ ከነበረ ኢትዪጵያ የሚለውን ቃል ሙሉ ለምሉ ማውጣቱ የትርጉም ስራው ፍትህአዊነት ይጎድለዋል:: በንፅፅር ኩሽን መጥቀስ ግን ተገቢም እውነትን መግለፅ ይሆናል:: መፅሃፍ ቅዱስን ስናነብ ኢትዪጵያ ሲባል ከኤርትራ ደቡብወይም ከሱዳን መለስ እስከ ሱማሌ ያለ አገር ብቻ እድርገን የምንስልም ከሆነ የግንዛቤያችን አድማስ ሙሉነት ሊጎድለው ይችላል :: ኢትዪጵያ የሚለውን ቃል ሙሉ በሙሉ ማውጣት የመፅሃፍ ቅዱስን ተአማኒንእት አይጨምርለትም ::

  4. Well, if Ethiopia has no historians ( religious and secular) who are able to deafened her biblical story and as well as international scholars who can come forward in support of the case, then the other view or argument will win ( latter or sooner). So, do not simply decry what others are doing to Ethiopia . Get ready and tell those scholars or historians of Ethiopia to fight what has been , is and will be right. Do not simply cry and complain!

  5. In order to understand the words: Cush/Kush and Aethiops/Ethiopia – it is good to know their definitions. Cush in Hebrew means black in English. Aethiops(with various spellings)/Ethiopia in Greek means black. The first bible translation translation from the Hebrew/Aramaic to Greek language was the Septuagint, which was translated by Hellinstic Jews who had excellent knowledge of both languages. The word Ethiopia never appeared in the Old Testament before the Septuagint Greek Translation (from Hebrew/Aramaic). As God loves mankind equally, let us try to know the truth instead of having unnecessary arguments. About a month ago, I came across a well researched article on Cush by a former lecturer at Addis Ababa University. If anyone of you is interested to know more about it, I will post it as soon as possible.

  6. ዐይነ ሥዉር የፀሐይን ብርሃን ማየት ባለመቻሉ ምክንያት፤ ፀሓይ የሚባል ነገር የለም ብሎ ቢያምን፣ ከራሱ ኢ―ክሂሎተ ርእይ ወይም ኢ―ርእዮተ ዓለም በቀር፤ የፀሓይን አማናዊ ህልውናዋን ሊቀይረው እንደማይችል ኹሉ፤ በሥጋም በመንፈስም የኢትዮጵያዊነት ስሜት ለተለየው ሆድ አደር ግለ ሰብእ ይቅርና ለምዕራባውያንም ኾነ ለአውሮፓ ሉተራን በሙሉ፤ ኢትዮጵያ የሚለው ቅዱስ ስም በተጠራ ቁጥር የሚያንገበግባቸው፣ በመጽሓፍም ሞልቶ ባዩት ቁጥር የሚያቃጥላቸው መኾኑን በግልፅ ይመስክሩልን እንጂ፣ ግለሰቡም ኾነ እነርሱ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያጭበረብሩን እንኳ አይደለንም።

Comments are closed.

Share